2 ዜና መዋዕል 18:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 በዚህ ጊዜ ሚካያህ እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ የይሖዋን ቃል ስሙ፦ ይሖዋ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ፣+ የሰማያት ሠራዊትም+ ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው አየሁ።+ ኢዮብ 1:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 የእውነተኛው አምላክ ልጆች*+ በይሖዋ ፊት ለመቆም+ የሚገቡበት ቀን በደረሰ ጊዜ ሰይጣንም+ መጥቶ በመካከላቸው ቆመ።+ ዳንኤል 7:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ከፊቱ የእሳት ጅረት ይፈልቅና ይፈስ ነበር።+ ሺህ ጊዜ ሺዎች ያገለግሉት ነበር፤ እልፍ ጊዜ እልፍም* በፊቱ ቆመው ነበር።+ ችሎቱ+ ተሰየመ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ። ሉቃስ 1:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 መልአኩም መልሶ እንዲህ አለው፦ “እኔ በአምላክ አጠገብ በፊቱ የምቆመው+ ገብርኤል+ ነኝ፤ አንተን እንዳነጋግርህና ይህን ምሥራች እንዳበስርህ ተልኬአለሁ። ዕብራውያን 1:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 በተጨማሪም ስለ መላእክት ሲናገር “መላእክቱን መናፍስት፣ አገልጋዮቹን*+ ደግሞ የእሳት ነበልባል ያደርጋል”+ ይላል። ዕብራውያን 1:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ሁሉም መዳን የሚወርሱትን እንዲያገለግሉ የሚላኩ ቅዱስ አገልግሎት* የሚያከናውኑ መናፍስት አይደሉም?+
10 ከፊቱ የእሳት ጅረት ይፈልቅና ይፈስ ነበር።+ ሺህ ጊዜ ሺዎች ያገለግሉት ነበር፤ እልፍ ጊዜ እልፍም* በፊቱ ቆመው ነበር።+ ችሎቱ+ ተሰየመ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ።