ሮም 12:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር በእናንተ በኩል የተቻላችሁን ሁሉ አድርጉ።+ ዕብራውያን 12:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር ጥረት አድርጉ፤+ ቅድስናንም ፈልጉ፤+ ያለቅድስና ማንም ሰው ጌታን ማየት አይችልም። ያዕቆብ 3:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ከዚህም በላይ የጽድቅ ፍሬ ሰላም ፈጣሪ ለሆኑ ሰዎች*+ ሰላማዊ በሆኑ ሁኔታዎች+ ይዘራል።