ሉቃስ 2:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 ምክንያቱም ዓይኖቼ ሰዎችን የምታድንበትን መንገድ አይተዋል፤+ ዮሐንስ 1:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 በማግስቱ ኢየሱስ ወደ እሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ “የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግደው+ የአምላክ በግ+ ይኸውላችሁ!+ የሐዋርያት ሥራ 4:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ደግሞም መዳን በሌላ በማንም አይገኝም፤ ምክንያቱም ልንድንበት የምንችል ከሰማይ በታች ለሰዎች የተሰጠ ሌላ ስም የለም።”+ የሐዋርያት ሥራ 5:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 እስራኤል ንስሐ እንዲገባና የኃጢአት ይቅርታ እንዲያገኝ+ አምላክ እሱን “ዋና ወኪል”+ እና “አዳኝ”+ አድርጎ በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው።+ ኤፌሶን 1:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 በተትረፈረፈ ጸጋው መሠረት በልጁ ደም አማካኝነት ቤዛውን በመክፈሉ ነፃ ወጥተናል፤+ አዎ፣ ለበደላችን ይቅርታ አግኝተናል።+ ዕብራውያን 7:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 ስለሆነም ለእነሱ ለመማለድ ሁልጊዜ ሕያው ሆኖ ስለሚኖር በእሱ አማካኝነት ወደ አምላክ የሚቀርቡትን ፈጽሞ ሊያድናቸውም ይችላል።+ 1 ጴጥሮስ 2:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እሱ ራሱ በገዛ አካሉ ኃጢአታችንን በእንጨት* ላይ+ ተሸከመ።+ ደግሞም “በእሱ ቁስል እናንተ ተፈወሳችሁ።”+