ማርቆስ 11:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ስለዚህ እላችኋለሁ፣ በጸሎት የምትጠይቁትንና የምትለምኑትን ነገር ሁሉ እንዳገኛችሁት አድርጋችሁ እመኑ፤ ደግሞም ታገኙታላችሁ።+ ዮሐንስ 14:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 በተጨማሪም አብ በወልድ አማካኝነት እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ።+ ዮሐንስ 16:23, 24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 በዚያን ጊዜ እኔን ምንም ጥያቄ አትጠይቁኝም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ አብን ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትጠይቁት+ ይሰጣችኋል።+ 24 እስካሁን ድረስ በስሜ አንድም ነገር አልጠየቃችሁም። ደስታችሁ የተሟላ እንዲሆን ጠይቁ፤ ትቀበላላችሁ። 1 ዮሐንስ 3:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 እንዲሁም ትእዛዛቱን ስለምንጠብቅና በፊቱ ደስ የሚያሰኙትን ነገሮች ስለምናደርግ የምንጠይቀውን ሁሉ ከእሱ እንቀበላለን።+ 1 ዮሐንስ 5:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 በእሱ ላይ ያለን ትምክህት* ይህ ነው፤+ የምንጠይቀው ነገር ምንም ይሁን ምን ከፈቃዱ ጋር በሚስማማ ሁኔታ እስከለመንን ድረስ ይሰማናል።+
23 በዚያን ጊዜ እኔን ምንም ጥያቄ አትጠይቁኝም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ አብን ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትጠይቁት+ ይሰጣችኋል።+ 24 እስካሁን ድረስ በስሜ አንድም ነገር አልጠየቃችሁም። ደስታችሁ የተሟላ እንዲሆን ጠይቁ፤ ትቀበላላችሁ።