-
ማርቆስ 12:1-9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 ከዚያም ምሳሌ በመጠቀም እንዲህ አላቸው፦ “አንድ ሰው የወይን እርሻ አለማ፤+ ዙሪያውንም አጠረው፤ ጉድጓድ ቆፍሮም የወይን መጭመቂያ አዘጋጀ፤ ማማም ሠራለት፤+ ከዚያም ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ።+ 2 ወቅቱ ሲደርስ ከወይኑ ፍሬ ድርሻውን ከገበሬዎቹ እንዲያመጣለት አንድ ባሪያ ወደ እነሱ ላከ። 3 እነሱ ግን ይዘው ደበደቡት፤ ባዶ እጁንም ሰደዱት። 4 በድጋሚ ሌላ ባሪያ ወደ እነሱ ላከ፤ እሱንም ራሱን ፈነከቱት፤ ደግሞም አዋረዱት።+ 5 ሌላም ባሪያ ላከ፤ እሱን ደግሞ ገደሉት፤ ሌሎች ብዙዎችንም ላከ፤ አንዳንዶቹን ደበደቡ፤ አንዳንዶቹን ደግሞ ገደሉ። 6 አሁን የቀረው የሚወደው ልጁ ነበር።+ ‘መቼም ልጄን ያከብሩታል’ በማለት በመጨረሻ እሱን ላከው። 7 እነዚያ ገበሬዎች ግን እርስ በርሳቸው ‘ወራሹ ይሄ ነው።+ ኑ እንግደለው፤ ርስቱም የእኛ ይሆናል’ ተባባሉ። 8 ስለዚህ ይዘው ገደሉት፤ ከወይን እርሻውም አውጥተው ጣሉት።+ 9 እንግዲህ የወይኑ እርሻ ባለቤት ምን የሚያደርግ ይመስላችኋል? ይመጣና ገበሬዎቹን ይገድላል፤ የወይን እርሻውንም ለሌሎች ይሰጣል።+
-
-
ሉቃስ 20:9-16አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 ከዚያም ለሕዝቡ የሚከተለውን ምሳሌ ይነግራቸው ጀመር፦ “አንድ ሰው የወይን እርሻ+ አለማና ለገበሬዎች አከራየ፤ ወደ ሌላ አገር ሄዶም ረዘም ላለ ጊዜ ቆየ።+ 10 ወቅቱ ሲደርስ ከወይኑ ፍሬ ድርሻውን እንዲልኩለት አንድ ባሪያ ወደ ገበሬዎቹ ላከ። ይሁንና ገበሬዎቹ ባሪያውን ከደበደቡት በኋላ ባዶ እጁን ሰደዱት።+ 11 እሱ ግን በድጋሚ ሌላ ባሪያ ወደ እነሱ ላከ። ይሄኛውንም ደብድበውና አዋርደው* ባዶ እጁን ሰደዱት። 12 አሁንም ሦስተኛ ባሪያ ላከ፤ እሱንም ካቆሰሉት በኋላ አውጥተው ጣሉት። 13 በዚህ ጊዜ የወይን እርሻው ባለቤት ‘ምን ባደርግ ይሻላል? የምወደውን ልጄን+ እልካለሁ። መቼም እሱን ያከብሩታል’ አለ። 14 ገበሬዎቹ ልጁን ባዩት ጊዜ እርስ በርሳቸው ‘ወራሹ ይሄ ነው። ርስቱ የእኛ እንዲሆን እንግደለው’ ተባባሉ። 15 ከዚያም ከወይን እርሻው ጎትተው በማውጣት ገደሉት።+ ታዲያ የወይኑ እርሻ ባለቤት ምን የሚያደርጋቸው ይመስላችኋል? 16 ይመጣና እነዚህን ገበሬዎች ይገድላል፤ የወይን እርሻውንም ለሌሎች ይሰጣል።”
ሕዝቡም ይህን ሲሰሙ “ይህስ ከቶ አይሁን!” አሉ።
-