የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማቴዎስ 21:33-41
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 33 “ሌላም ምሳሌ ስሙ፦ የወይን እርሻ+ ያለማ አንድ ባለ ርስት ነበር፤ ዙሪያውንም አጠረው፤ በዚያም የወይን መጭመቂያ ቆፈረ እንዲሁም ማማ ሠራ፤+ ከዚያም ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ።+ 34 ፍሬው የሚሰበሰብበት ወቅት ሲደርስ ድርሻውን እንዲያመጡለት ባሪያዎቹን ወደ ገበሬዎቹ ላከ። 35 ገበሬዎቹ ግን ባሪያዎቹን ይዘው አንዱን ደበደቡት፤ ሌላውን ገደሉት፤ ሌላውን ደግሞ በድንጋይ ወገሩት።+ 36 ከበፊቶቹ የሚበዙ ሌሎች ባሪያዎች በድጋሚ ላከ፤ ይሁንና በእነሱም ላይ ተመሳሳይ ድርጊት ፈጸሙባቸው።+ 37 በመጨረሻም ‘መቼም ልጄን ያከብሩታል’ በማለት ልጁን ላከው። 38 ገበሬዎቹ ልጁን ሲያዩት እርስ በርሳቸው ‘ወራሹ ይሄ ነው።+ ኑ እንግደለው፤ ርስቱንም እንውረስ!’ ተባባሉ። 39 ስለዚህ ያዙትና ከወይን እርሻው ጎትተው በማውጣት ገደሉት።+ 40 እንግዲህ የወይኑ እርሻ ባለቤት ሲመጣ እነዚህን ገበሬዎች ምን የሚያደርጋቸው ይመስላችኋል?” 41 የካህናት አለቆቹና የሕዝቡ ሽማግሌዎችም “ክፉዎች ስለሆኑ ከባድ ጥፋት ያደርስባቸዋል፤ ከዚያም የወይን እርሻውን፣ ፍሬውን በወቅቱ ለሚያስረክቡት ለሌሎች ገበሬዎች ያከራያል” አሉት።

  • ማርቆስ 12:1-9
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 ከዚያም ምሳሌ በመጠቀም እንዲህ አላቸው፦ “አንድ ሰው የወይን እርሻ አለማ፤+ ዙሪያውንም አጠረው፤ ጉድጓድ ቆፍሮም የወይን መጭመቂያ አዘጋጀ፤ ማማም ሠራለት፤+ ከዚያም ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ።+ 2 ወቅቱ ሲደርስ ከወይኑ ፍሬ ድርሻውን ከገበሬዎቹ እንዲያመጣለት አንድ ባሪያ ወደ እነሱ ላከ። 3 እነሱ ግን ይዘው ደበደቡት፤ ባዶ እጁንም ሰደዱት። 4 በድጋሚ ሌላ ባሪያ ወደ እነሱ ላከ፤ እሱንም ራሱን ፈነከቱት፤ ደግሞም አዋረዱት።+ 5 ሌላም ባሪያ ላከ፤ እሱን ደግሞ ገደሉት፤ ሌሎች ብዙዎችንም ላከ፤ አንዳንዶቹን ደበደቡ፤ አንዳንዶቹን ደግሞ ገደሉ። 6 አሁን የቀረው የሚወደው ልጁ ነበር።+ ‘መቼም ልጄን ያከብሩታል’ በማለት በመጨረሻ እሱን ላከው። 7 እነዚያ ገበሬዎች ግን እርስ በርሳቸው ‘ወራሹ ይሄ ነው።+ ኑ እንግደለው፤ ርስቱም የእኛ ይሆናል’ ተባባሉ። 8 ስለዚህ ይዘው ገደሉት፤ ከወይን እርሻውም አውጥተው ጣሉት።+ 9 እንግዲህ የወይኑ እርሻ ባለቤት ምን የሚያደርግ ይመስላችኋል? ይመጣና ገበሬዎቹን ይገድላል፤ የወይን እርሻውንም ለሌሎች ይሰጣል።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ