ማቴዎስ 6:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 አንተ ግን ስትጸልይ ወደ ክፍልህ ግባ፤ በርህንም ዘግተህ በስውር ወዳለው አባትህ ጸልይ።+ በስውር የሚያይ አባትህም መልሶ ይከፍልሃል። ማቴዎስ 14:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ሕዝቡን ካሰናበተ በኋላ ለመጸለይ ብቻውን ወደ ተራራ ወጣ።+ በመሸም ጊዜ በዚያ ብቻውን ነበር። ማርቆስ 1:35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 35 ኢየሱስ በማለዳ ገና ጎህ ሳይቀድ ተነስቶ ከቤት ወጣና ገለል ወዳለ ስፍራ ሄደ፤ እዚያም መጸለይ ጀመረ።+ ሉቃስ 6:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 በዚያው ሰሞን ኢየሱስ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ፤+ ሌሊቱንም ሙሉ ወደ አምላክ ሲጸልይ አደረ።+