የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማቴዎስ 17:14-17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 ወደ ሕዝቡ በመጡ ጊዜ+ አንድ ሰው ወደ እሱ ቀረበና ተንበርክኮ እንዲህ አለው፦ 15 “ጌታ ሆይ፣ ለልጄ ምሕረት አድርግለት፤ የሚጥል በሽታ ስላለበት በጠና ታሟል። አንዴ እሳት ውስጥ አንዴ ደግሞ ውኃ ውስጥ ይወድቃል።+ 16 ወደ ደቀ መዛሙርትህ አመጣሁት፤ እነሱ ግን ሊፈውሱት አልቻሉም።” 17 ኢየሱስም መልሶ “እምነት የለሽና ጠማማ ትውልድ ሆይ፣+ ከእናንተ ጋር እስከ መቼ መቆየት ሊኖርብኝ ነው? እስከ መቼስ እናንተን መታገሥ ሊኖርብኝ ነው? ልጁን ወደ እኔ አምጡት” አለ።

  • ሉቃስ 9:38-42
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 38 እነሆም ከሕዝቡ መካከል አንድ ሰው ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ “መምህር፣ ልጄን እንድታይልኝ እለምንሃለሁ፤ ምክንያቱም ያለኝ ልጅ አንድ እሱ ብቻ ነው።+ 39 እነሆም፣ ርኩስ መንፈስ ይይዘውና በድንገት ይጮኻል፤ ጥሎም በአፉ አረፋ እያስደፈቀ ያንፈራግጠዋል፤ ጉዳት ካደረሰበትም በኋላ በስንት መከራ ይለቀዋል። 40 ደቀ መዛሙርትህ እንዲያስወጡት ለመንኳቸው፤ እነሱ ግን አልቻሉም።” 41 ኢየሱስም መልሶ “እምነት የለሽና ጠማማ ትውልድ ሆይ፣+ እስከ መቼ ከእናንተ ጋር መቆየትና እናንተን መታገሥ ሊኖርብኝ ነው? እስቲ ልጅህን ወደዚህ አምጣው” አለ።+ 42 ሆኖም ወደ እሱ እየመጣ ሳለ ጋኔኑ መሬት ላይ ጥሎ በኃይል አንፈራገጠው። ይሁንና ኢየሱስ ርኩሱን መንፈስ ገሠጸውና ልጁን ፈወሰው፤ ከዚያም ለአባቱ መልሶ ሰጠው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ