ዮሐንስ 12:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 ይህ ዓለም የሚፈረድበት ጊዜ አሁን ነው፤ የዚህ ዓለም ገዢ+ አሁን ይባረራል።+ ዮሐንስ 16:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ስለ ፍርድ የተባለው ደግሞ የዚህ ዓለም ገዢ ስለተፈረደበት ነው።+ ዕብራውያን 2:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ስለዚህ እነዚህ “ልጆች” ሥጋና ደም ስለሆኑ እሱም ሥጋና ደም ሆነ፤+ ይህም የሆነው ለሞት የመዳረግ አቅም ያለውን+ ዲያብሎስን በሞቱ አማካኝነት እንዳልነበረ ያደርገው ዘንድ ነው፤+ ራእይ 12:7-9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 በሰማይም ጦርነት ተነሳ፦ ሚካኤልና*+ መላእክቱ ከዘንዶው ጋር ተዋጉ፤ ዘንዶውና መላእክቱም ተዋጓቸው፤ 8 ነገር ግን አልቻሏቸውም፤* ከዚያ በኋላም በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም። 9 ስለሆነም ታላቁ ዘንዶ+ ይኸውም መላውን ዓለም እያሳሳተ ያለው+ ዲያብሎስና+ ሰይጣን+ ተብሎ የሚጠራው የጥንቱ እባብ+ ወደ ታች ተወረወረ፤ ወደ ምድር ተጣለ፤+ መላእክቱም ከእሱ ጋር ተወረወሩ።
14 ስለዚህ እነዚህ “ልጆች” ሥጋና ደም ስለሆኑ እሱም ሥጋና ደም ሆነ፤+ ይህም የሆነው ለሞት የመዳረግ አቅም ያለውን+ ዲያብሎስን በሞቱ አማካኝነት እንዳልነበረ ያደርገው ዘንድ ነው፤+
7 በሰማይም ጦርነት ተነሳ፦ ሚካኤልና*+ መላእክቱ ከዘንዶው ጋር ተዋጉ፤ ዘንዶውና መላእክቱም ተዋጓቸው፤ 8 ነገር ግን አልቻሏቸውም፤* ከዚያ በኋላም በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም። 9 ስለሆነም ታላቁ ዘንዶ+ ይኸውም መላውን ዓለም እያሳሳተ ያለው+ ዲያብሎስና+ ሰይጣን+ ተብሎ የሚጠራው የጥንቱ እባብ+ ወደ ታች ተወረወረ፤ ወደ ምድር ተጣለ፤+ መላእክቱም ከእሱ ጋር ተወረወሩ።