5 በመጀመሪያው ወር ከወሩም በ14ኛው ቀን+ አመሻሹ ላይ ለይሖዋ ፋሲካ ይከበራል።+
6 “‘በዚህ ወር 15ኛ ቀን ላይ የቂጣ በዓል ለይሖዋ ይከበራል።+ ለሰባት ቀንም ቂጣ መብላት ይኖርባችኋል።+ 7 በመጀመሪያው ቀን ቅዱስ ጉባኤ ታከብራላችሁ።+ ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ መሥራት የለባችሁም። 8 ሆኖም ለሰባት ቀን ያህል ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ታቀርባላችሁ። በሰባተኛው ቀን ቅዱስ ጉባኤ ይሆናል። ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ መሥራት የለባችሁም።’”