ኢሳይያስ 53:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ስለዚህ ከብዙዎች ጋር ድርሻውን እሰጠዋለሁ፤ምርኮውን ከኃያላን ጋር ይካፈላል፤ሕይወቱን* እስከ ሞት ድረስ አፍስሷልና፤+ከሕግ ተላላፊዎችም ጋር ተቆጥሯል፤+የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸክሟል፤+ስለ ሕግ ተላላፊዎችም ማልዷል።+ ፊልጵስዩስ 2:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ከዚህም በላይ ሰው ሆኖ በመጣ ጊዜ* ራሱን ዝቅ በማድረግ እስከ ሞት ድረስ ያውም በመከራ እንጨት*+ ላይ እስከ መሞት ድረስ ታዛዥ ሆኗል።+ ዕብራውያን 2:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ነገር ግን ከመላእክት በጥቂቱ እንዲያንስ ተደርጎ የነበረው ኢየሱስ+ እስከ ሞት ድረስ መከራ በመቀበሉ+ አሁን የክብርና የሞገስ ዘውድ ደፍቶ እናየዋለን፤ እሱ በአምላክ ጸጋ ለሰው ሁሉ ሲል ሞትን ቀምሷል።+ ዕብራውያን 12:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 የምንሮጠውም የእምነታችን “ዋና ወኪል”* እና “ፍጹም አድራጊ” የሆነውን ኢየሱስን በትኩረት በመመልከት ነው።+ እሱ ከፊቱ ለሚጠብቀው ደስታ ሲል፣ የሚደርስበትን ውርደት ከምንም ሳይቆጥር በመከራ እንጨት* ላይ እስከ መሞት ድረስ ጸንቷል፤ እንዲሁም በአምላክ ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል።+
12 ስለዚህ ከብዙዎች ጋር ድርሻውን እሰጠዋለሁ፤ምርኮውን ከኃያላን ጋር ይካፈላል፤ሕይወቱን* እስከ ሞት ድረስ አፍስሷልና፤+ከሕግ ተላላፊዎችም ጋር ተቆጥሯል፤+የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸክሟል፤+ስለ ሕግ ተላላፊዎችም ማልዷል።+
9 ነገር ግን ከመላእክት በጥቂቱ እንዲያንስ ተደርጎ የነበረው ኢየሱስ+ እስከ ሞት ድረስ መከራ በመቀበሉ+ አሁን የክብርና የሞገስ ዘውድ ደፍቶ እናየዋለን፤ እሱ በአምላክ ጸጋ ለሰው ሁሉ ሲል ሞትን ቀምሷል።+
2 የምንሮጠውም የእምነታችን “ዋና ወኪል”* እና “ፍጹም አድራጊ” የሆነውን ኢየሱስን በትኩረት በመመልከት ነው።+ እሱ ከፊቱ ለሚጠብቀው ደስታ ሲል፣ የሚደርስበትን ውርደት ከምንም ሳይቆጥር በመከራ እንጨት* ላይ እስከ መሞት ድረስ ጸንቷል፤ እንዲሁም በአምላክ ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል።+