ማቴዎስ 3:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ደግሞም “በጣም የምደሰትበት+ የምወደው ልጄ ይህ ነው”+ የሚል ድምፅ ከሰማያት ተሰማ።+ ማቴዎስ 17:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ገና እየተናገረ ሳለም ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ ከደመናውም “በጣም የምደሰትበት፣ የምወደው ልጄ ይህ ነው።+ እሱን ስሙት”+ የሚል ድምፅ ተሰማ። ማርቆስ 1:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ከዚያም “አንተ የምወድህ ልጄ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል” የሚል ድምፅ ከሰማያት መጣ።+ ማርቆስ 9:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ከዚያም ደመና መጥቶ ጋረዳቸው፤ ከደመናውም “የምወደው ልጄ ይህ ነው።+ እሱን ስሙት”+ የሚል ድምፅ መጣ።+ ሉቃስ 3:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 መንፈስ ቅዱስም አካላዊ ቅርጽ ይዞ በርግብ መልክ በእሱ ላይ ወረደ፤ ከዚያም “አንተ የምወድህ ልጄ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል” የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ።+ ሉቃስ 9:35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 35 ከዚያም ከደመናው “የመረጥኩት ልጄ ይህ ነው።+ እሱን ስሙት”+ የሚል ድምፅ መጣ።+ 2 ጴጥሮስ 1:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ከግርማዊው ክብር “እኔ ራሴ በጣም የምደሰትበት፣ የምወደው ልጄ ይህ ነው”+ የሚል ቃል* ለእሱ በተነገረ ጊዜ ከአባታችንና ከአምላካችን ክብርና ሞገስ ተቀብሏል።
17 ከግርማዊው ክብር “እኔ ራሴ በጣም የምደሰትበት፣ የምወደው ልጄ ይህ ነው”+ የሚል ቃል* ለእሱ በተነገረ ጊዜ ከአባታችንና ከአምላካችን ክብርና ሞገስ ተቀብሏል።