የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ሳሙኤል 12:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 በመጨረሻም ሳሙኤል እስራኤላውያንን ሁሉ እንዲህ አላቸው፦ “እንግዲህ እኔ ያላችሁኝን ሁሉ አድርጌአለሁ፤* የሚገዛችሁም ንጉሥ አንግሼላችኋለሁ።+

  • 1 ሳሙኤል 12:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 አሁንም ያለሁት በፊታችሁ ነው። እስቲ የምከሰስበት ነገር ካለ በይሖዋና እሱ በቀባው+ ፊት ንገሩኝ፦ የማንን በሬ ወይም የማንን አህያ ወስጃለሁ?+ ወይስ ማንን አታልያለሁ? ደግሞስ በማን ላይ ግፍ ፈጽሜአለሁ? አይቼ እንዳላየሁ ለመሆንስ ከማን እጅ ጉቦ ተቀብያለሁ?+ እንዲህ አድርጌ ከሆነ እመልስላችኋለሁ።”+

  • ማቴዎስ 10:8
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 8 የታመሙትን ፈውሱ፤+ የሞቱትን አስነሱ፤ የሥጋ ደዌ ያለባቸውን አንጹ፤ አጋንንትንም አስወጡ። በነፃ እንደተቀበላችሁ በነፃ ስጡ።

  • 1 ቆሮንቶስ 9:11, 12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 እኛ በእናንተ መካከል መንፈሳዊ ነገሮች ከዘራን ከእናንተ ሥጋዊ ነገሮች ብናጭድ ትልቅ ነገር መሆኑ ነው?+ 12 ሌሎች የእናንተን ድጋፍ የማግኘት መብት ካላቸው እኛ ከእነሱ የበለጠ መብት የለንም? ይሁንና እኛ በዚህ መብት* አልተጠቀምንም፤+ ከዚህ ይልቅ ስለ ክርስቶስ የሚሰበከውን ምሥራች የሚያደናቅፍ ምንም ነገር ላለመፍጠር ሁሉን ችለን እንኖራለን።+

  • 2 ቆሮንቶስ 7:2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 2 በልባችሁ ውስጥ ቦታ ስጡን።+ እኛ ማንንም አልበደልንም፤ ማንንም አላበላሸንም፤ ማንንም መጠቀሚያ አላደረግንም።+

  • ቲቶ 1:7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 ምክንያቱም የበላይ ተመልካች በአምላክ የተሾመ መጋቢ እንደመሆኑ መጠን ከክስ ነፃ መሆን አለበት፤ በራሱ ሐሳብ የሚመራ፣+ ግልፍተኛ፣+ ሰካራም፣ ኃይለኛና* አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት የሚስገበገብ ሊሆን አይገባም፤

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ