ዘፀአት 20:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 “አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም+ አባትህንና እናትህን አክብር።+ ዘዳግም 5:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 “‘አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝምና መልካም እንዲሆንልህ+ አምላክህ ይሖዋ ባዘዘህ መሠረት አባትህንና እናትህን አክብር።+ ምሳሌ 20:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 አባቱንና እናቱን የሚረግም ሁሉጨለማ ሲሆን መብራቱ ይጠፋበታል።+ ምሳሌ 23:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 የወለደህን አባትህን ስማ፤እናትህንም ስላረጀች አትናቃት።+ ማቴዎስ 15:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ለምሳሌ አምላክ ‘አባትህንና እናትህን አክብር’+ እንዲሁም ‘አባቱን ወይም እናቱን የሚሳደብ* ይገደል’ ብሏል።+