-
ሕዝቅኤል 1:5-10አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 በመካከሉም የአራት ሕያዋን ፍጥረታት+ አምሳያ ነበር፤ የእያንዳንዳቸውም መልክ እንደ ሰው መልክ ነበር። 6 እያንዳንዳቸው አራት አራት ፊትና አራት አራት ክንፍ ነበራቸው።+ 7 እግሮቻቸው ቀጥ ያሉ ነበሩ፤ የእግራቸውም ኮቴ የጥጃ ኮቴ ይመስል ነበር፤ እግሮቻቸውም እንደተወለወለ መዳብ ያብረቀርቃሉ።+ 8 በአራቱም ጎኖቻቸው ከክንፎቻቸው ሥር የሰው እጆች ነበሯቸው፤ አራቱም ፊቶችና ክንፎች ነበሯቸው። 9 ክንፎቻቸውም እርስ በርሳቸው ይነካኩ ነበር። በሚሄዱበት ጊዜ አይዞሩም፤ እያንዳንዳቸውም ቀጥ ብለው ወደ ፊት ይሄዱ ነበር።+
10 የፊታቸው መልክ ይህን ይመስል ነበር፦ አራቱም የሰው ፊት ነበራቸው፤ በስተ ቀኝ የአንበሳ+ ፊት፣ በስተ ግራ የበሬ+ ፊት ነበራቸው፤ ደግሞም አራቱም የንስር+ ፊት ነበራቸው።+
-