የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 13:6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  6 የይሖዋ ቀን ቀርቧልና ዋይ ዋይ በሉ!

      በዚያ ቀን ሁሉን ቻይ ከሆነው አምላክ ዘንድ ጥፋት ይመጣል።+

  • ኤርምያስ 25:33
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 33 “‘በዚያም ቀን፣ ይሖዋ የገደላቸው ከምድር ዳር እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆናሉ። አይለቀስላቸውም፣ አይሰበሰቡም ወይም አይቀበሩም። በምድር ላይ እንደ ፍግ ይሆናሉ።’

  • ሕዝቅኤል 30:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  3 ቀኑ ቀርቧልና፤ አዎ፣ የይሖዋ ቀን ቀርቧል።+

      የደመናት ቀን፣+ በብሔራትም ላይ የሚፈረድበት ቀን ይሆናል።+

  • ኢዩኤል 1:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 ከቀኑ የተነሳ ወዮላችሁ!

      የይሖዋ ቀን ቀርቧልና፤+

      ሁሉን ከሚችለው አምላክ ዘንድ እንደ ጥፋት ይመጣል!

  • ኢዩኤል 2:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 2 “በጽዮን ቀንደ መለከት ንፉ!+

      በቅዱሱ ተራራዬ ላይ ቀረርቶ አሰሙ።

      የአገሪቱ* ነዋሪዎች በሙሉ ይንቀጥቀጡ፤

      የይሖዋ ቀን ቀርቧልና!+ ቀኑ ደፍ ላይ ነው!

  • ኢዩኤል 2:11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 ይሖዋ በሠራዊቱ+ ፊት ድምፁን በኃይል ያሰማል፤ ሠራዊቱ ስፍር ቁጥር የለውም።+

      ቃሉን የሚፈጽመው ኃያል ነውና፤

      የይሖዋ ቀን ታላቅና እጅግ የሚያስፈራ ነው።+

      ማንስ ሊቋቋመው ይችላል?”+

  • ሶፎንያስ 1:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 ያ ቀን የታላቅ ቁጣ ቀን፣+

      የጭንቀትና የሥቃይ ቀን፣+

      የአውሎ ነፋስና የጥፋት ቀን፣

      የጨለማና የጭጋግ ቀን፣+

      የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ይሆናል፤+

  • 2 ጴጥሮስ 3:11, 12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 እነዚህ ሁሉ ነገሮች በዚህ ሁኔታ የሚቀልጡ ከሆነ ቅዱስ ሥነ ምግባር በመከተልና ለአምላክ ያደራችሁ መሆናችሁን የሚያሳዩ ተግባሮች በመፈጸም ምን ዓይነት ሰዎች መሆን እንዳለባችሁ ልታስቡበት ይገባል! 12 ሰማያት በእሳት ተቃጥለው የሚጠፉበትንና+ ንጥረ ነገሮቹም በኃይለኛ ሙቀት የሚቀልጡበትን የይሖዋን* ቀን መምጣት* እየጠበቃችሁና በአእምሯችሁ አቅርባችሁ እየተመለከታችሁ* ልትኖሩ ይገባል!+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ