የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማቴዎስ 14
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ማቴዎስ የመጽሐፉ ይዘት

      • የመጥምቁ ዮሐንስ ራስ ተቆረጠ (1-12)

      • ኢየሱስ 5,000 ሰዎችን መገበ (13-21)

      • ኢየሱስ በውኃ ላይ ተራመደ (22-33)

      • በጌንሴሬጥ የተከናወነ ፈውስ (34-36)

ማቴዎስ 14:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የአራተኛው ክፍል ገዢ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 6:14፤ ሉቃስ 9:7-9፤ ሥራ 4:27

ማቴዎስ 14:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 16:13, 14፤ ማር 6:16

ማቴዎስ 14:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ሄሮድስ አንቲጳስን ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 6:17, 18፤ ሉቃስ 3:19, 20

ማቴዎስ 14:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 18:16፤ 20:21

ማቴዎስ 14:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 6:20፤ ሉቃስ 1:67, 76

ማቴዎስ 14:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 40:20-22
  • +ማር 6:21-29

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 44

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/1998፣ ገጽ 31

ማቴዎስ 14:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 6:25

ማቴዎስ 14:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 6:31-33፤ ሉቃስ 9:10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 128

ማቴዎስ 14:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 9:36፤ 15:32፤ ማር 1:41፤ 6:34፤ ሉቃስ 7:13፤ ዕብ 2:17፤ 5:2
  • +ሉቃስ 9:11

ማቴዎስ 14:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 6:35-44፤ ሉቃስ 9:12-17፤ ዮሐ 6:5-13

ማቴዎስ 14:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 15:36፤ ማር 6:41፤ ሉቃስ 9:16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 16

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 128

    የአምላክ ቃል፣ ገጽ 69-70

ማቴዎስ 14:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 4:42-44፤ ማር 6:42, 43፤ 8:8፤ ሉቃስ 9:17፤ ዮሐ 6:12, 13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 16

    የአምላክ ቃል፣ ገጽ 69-70

ማቴዎስ 14:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 6:44፤ ሉቃስ 9:14፤ ዮሐ 6:10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 16

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 128

    የአምላክ ቃል፣ ገጽ 69-70

ማቴዎስ 14:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 6:45-52፤ ዮሐ 6:16-21

ማቴዎስ 14:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 6:46፤ ሉቃስ 6:12፤ 9:18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    “ተከታዬ ሁን፣” ገጽ 134

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 9

ማቴዎስ 14:24

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ብዙ ስታዲዮን።” አንድ ስታዲዮን 185 ሜትር ነው።

ማቴዎስ 14:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከሌሊቱ 9 ሰዓት ገደማ አንስቶ 12 ሰዓት ገደማ ላይ ፀሐይ እስከምትወጣበት ጊዜ ድረስ ያለውን ሰዓት ያመለክታል።

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    9/2018፣ ገጽ 22

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 131

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/1/1995፣ ገጽ 3

    8/1/1991፣ ገጽ 21

ማቴዎስ 14:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 6:50፤ ዮሐ 6:20

ማቴዎስ 14:28

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2021፣ ገጽ 17-18

ማቴዎስ 14:29

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2021፣ ገጽ 17-18

ማቴዎስ 14:30

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2021፣ ገጽ 17-18

    መጠበቂያ ግንብ፣

    9/15/2015፣ ገጽ 14

    8/1/2012፣ ገጽ 29

ማቴዎስ 14:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 6:30፤ 8:26፤ 28:16, 17፤ ያዕ 1:6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ምሰሏቸው፣ ገጽ 185-186

    መጠበቂያ ግንብ፣

    8/1/2012፣ ገጽ 29

    10/1/2009፣ ገጽ 24-25

    9/15/2009፣ ገጽ 7-8

ማቴዎስ 14:33

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “እጅ ነሱት።”

ማቴዎስ 14:34

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማር 6:53-56

ማቴዎስ 14:36

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 9:20, 21፤ ማር 3:10፤ ሉቃስ 6:19

ተዛማጅ ሐሳብ

ማቴ. 14:1ማር 6:14፤ ሉቃስ 9:7-9፤ ሥራ 4:27
ማቴ. 14:2ማቴ 16:13, 14፤ ማር 6:16
ማቴ. 14:3ማር 6:17, 18፤ ሉቃስ 3:19, 20
ማቴ. 14:4ዘሌ 18:16፤ 20:21
ማቴ. 14:5ማር 6:20፤ ሉቃስ 1:67, 76
ማቴ. 14:6ዘፍ 40:20-22
ማቴ. 14:6ማር 6:21-29
ማቴ. 14:8ማር 6:25
ማቴ. 14:13ማር 6:31-33፤ ሉቃስ 9:10
ማቴ. 14:14ማቴ 9:36፤ 15:32፤ ማር 1:41፤ 6:34፤ ሉቃስ 7:13፤ ዕብ 2:17፤ 5:2
ማቴ. 14:14ሉቃስ 9:11
ማቴ. 14:15ማር 6:35-44፤ ሉቃስ 9:12-17፤ ዮሐ 6:5-13
ማቴ. 14:19ማቴ 15:36፤ ማር 6:41፤ ሉቃስ 9:16
ማቴ. 14:202ነገ 4:42-44፤ ማር 6:42, 43፤ 8:8፤ ሉቃስ 9:17፤ ዮሐ 6:12, 13
ማቴ. 14:21ማር 6:44፤ ሉቃስ 9:14፤ ዮሐ 6:10
ማቴ. 14:22ማር 6:45-52፤ ዮሐ 6:16-21
ማቴ. 14:23ማር 6:46፤ ሉቃስ 6:12፤ 9:18
ማቴ. 14:27ማር 6:50፤ ዮሐ 6:20
ማቴ. 14:31ማቴ 6:30፤ 8:26፤ 28:16, 17፤ ያዕ 1:6
ማቴ. 14:34ማር 6:53-56
ማቴ. 14:36ማቴ 9:20, 21፤ ማር 3:10፤ ሉቃስ 6:19
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
  • 36
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ማቴዎስ 14:1-36

የማቴዎስ ወንጌል

14 በዚያን ጊዜ የአውራጃ ገዢ* የነበረው ሄሮድስ ስለ ኢየሱስ ሲሰማ+ 2 አገልጋዮቹን “ይህ መጥምቁ ዮሐንስ ነው። ከሞት ተነስቷል ማለት ነው፤ እነዚህን ተአምራት መፈጸም የቻለውም ለዚህ ነው” አላቸው።+ 3 ሄሮድስ* የወንድሙ የፊልጶስ ሚስት በሆነችው በሄሮድያዳ ምክንያት ዮሐንስን ይዞ በሰንሰለት በማሰር ወህኒ አስገብቶት ነበር።+ 4 ዮሐንስ ሄሮድስን “እሷን እንድታገባ ሕግ አይፈቅድልህም” ይለው ነበር።+ 5 ሄሮድስ ሊገድለው ይፈልግ የነበረ ቢሆንም ሕዝቡ እንደ ነቢይ ይመለከተው ስለነበር ሕዝቡን ፈራ።+ 6 ሆኖም የሄሮድስ ልደት+ በተከበረበት ዕለት የሄሮድያዳ ልጅ በግብዣው ላይ በመጨፈር ሄሮድስን እጅግ ደስ አሰኘችው፤+ 7 በመሆኑም የጠየቀችውን ሁሉ ሊሰጣት በመሐላ ቃል ገባላት። 8 ከዚያም እናቷ በሰጠቻት ምክር መሠረት “የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ በዚህ ሳህን ስጠኝ” አለችው።+ 9 ንጉሡ ቢያዝንም ስለ መሐላዎቹና አብረውት ይበሉ ስለነበሩት ሲል የዮሐንስ ራስ እንዲሰጣት አዘዘ። 10 ሰው ልኮም የዮሐንስን ራስ በወህኒ ቤት አስቆረጠ። 11 ራሱን በሳህን አምጥተው ለልጅቷ ሰጧት፤ እሷም ለእናቷ ሰጠቻት። 12 በኋላም የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት መጡና አስከሬኑን ወስደው ቀበሩት፤ ከዚያም መጥተው ለኢየሱስ ነገሩት። 13 ኢየሱስ ይህን ሲሰማ ብቻውን ለመሆን በጀልባ ተሳፍሮ ገለል ወዳለ ስፍራ ሄደ። ሕዝቡ ግን መሄዱን ሰምተው ከየከተማው እየወጡ በእግር ተከተሉት።+

14 ኢየሱስ ወደ ባሕሩ ዳርቻ ሲመጣ እጅግ ብዙ ሕዝብ ተመለከተና በጣም አዘነላቸው፤+ በመካከላቸው የነበሩትንም ሕመምተኞች ፈወሰ።+ 15 በመሸ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እሱ ቀርበው “ቦታው ገለል ያለ ነው፤ ሰዓቱ ደግሞ ገፍቷል፤ ስለዚህ ሕዝቡ ወደ መንደሮቹ ሄደው ምግብ እንዲገዙ አሰናብታቸው” አሉት።+ 16 ይሁን እንጂ ኢየሱስ “መሄድ አያስፈልጋቸውም፤ እናንተ የሚበሉት ነገር ስጧቸው” አላቸው። 17 እነሱም “ከአምስት ዳቦና ከሁለት ዓሣ በስተቀር እዚህ ምንም ነገር የለንም” አሉት። 18 እሱም “ያለውን ወደ እኔ አምጡት” አላቸው። 19 ሕዝቡንም ሣሩ ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ። ከዚያም አምስቱን ዳቦና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ ቀና በማለት ባረከ፤+ ዳቦውን ከቆረሰ በኋላም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤ እነሱ ደግሞ ለሕዝቡ ሰጡ። 20 ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ ከዚያም የተረፈውን ቁርስራሽ ሰበሰቡ፤ ቁርስራሹም 12 ቅርጫት ሙሉ ሆነ።+ 21 የበሉትም ከሴቶችና ከትናንሽ ልጆች ሌላ 5,000 ወንዶች ነበሩ።+ 22 ወዲያውም፣ እሱ ሕዝቡን እያሰናበተ ሳለ ደቀ መዛሙርቱን ጀልባ ተሳፍረው ቀድመውት ወደ ማዶ እንዲሻገሩ ነገራቸው።+

23 ሕዝቡን ካሰናበተ በኋላ ለመጸለይ ብቻውን ወደ ተራራ ወጣ።+ በመሸም ጊዜ በዚያ ብቻውን ነበር። 24 በዚህ ጊዜ ጀልባው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሜትሮች* ከየብስ ርቆ የነበረ ሲሆን ነፋሱ ወደ እነሱ ይነፍስ ስለነበር ማዕበሉ በጣም አስቸገራቸው። 25 ሆኖም ኢየሱስ በአራተኛው ክፍለ ሌሊት* በባሕሩ ላይ እየተራመደ ወደ እነሱ መጣ። 26 ደቀ መዛሙርቱ በባሕሩ ላይ ሲራመድ ባዩት ጊዜ ደንግጠው “ምትሃት ነው!” አሉ። በፍርሃት ተውጠውም ጮኹ። 27 ሆኖም ኢየሱስ ወዲያውኑ “አይዟችሁ! እኔ ነኝ፤ አትፍሩ” አላቸው።+ 28 ጴጥሮስም መልሶ “ጌታ ሆይ፣ አንተ ከሆንክ በውኃው ላይ እየተራመድኩ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ” አለው። 29 እሱም “ና!” አለው። በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ ከጀልባው ላይ ወርዶ በውኃው ላይ እየተራመደ ወደ ኢየሱስ አመራ። 30 ሆኖም አውሎ ነፋሱን ሲያይ ፈራ። መስጠም ሲጀምርም “ጌታ ሆይ፣ አድነኝ!” ብሎ ጮኸ። 31 ወዲያው ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ያዘውና “አንተ እምነት የጎደለህ! ለምን ተጠራጠርክ?” አለው።+ 32 ጀልባው ላይ ከወጡ በኋላ አውሎ ነፋሱ ጸጥ አለ። 33 ከዚያም በጀልባው ውስጥ ያሉት “አንተ በእርግጥ የአምላክ ልጅ ነህ” ብለው ሰገዱለት።* 34 ባሕሩንም ተሻግረው ጌንሴሬጥ+ ወደተባለ ቦታ ደረሱ።

35 በዚያ የሚኖሩ ሰዎች ኢየሱስ መሆኑን ሲያውቁ በዙሪያው ወዳለው አካባቢ ሁሉ መልእክት ላኩ፤ ሰዎችም የታመሙትን ሁሉ ወደ እሱ አመጡ። 36 የልብሱን ዘርፍ ብቻ እንኳ ለመንካት ይማጸኑት ነበር፤+ የነኩትም ሁሉ ሙሉ በሙሉ ተፈወሱ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ