የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 21
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘዳግም የመጽሐፉ ይዘት

      • ገዳዩ ስላልታወቀ ሰው የተሰጠ መመሪያ (1-9)

      • የተማረከችን ሴት ስለማግባት (10-14)

      • የበኩር ልጅ መብት (15-17)

      • እልኸኛና ዓመፀኛ ልጅ (18-21)

      • በእንጨት ላይ የሚሰቀል ሰው የተረገመ ነው (22, 23)

ዘዳግም 21:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 16:18

ዘዳግም 21:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ደረቅ ወንዝ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 35:33

ዘዳግም 21:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 6:23-27፤ 1ዜና 23:13
  • +ዘፀ 28:1
  • +ዘዳ 17:8, 9

ዘዳግም 21:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 26:6፤ ማቴ 27:24

ዘዳግም 21:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 7:23
  • +ኢሳ 26:21፤ ኤር 26:15

ዘዳግም 21:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 31:9፤ ዘዳ 20:13, 14

ዘዳግም 21:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 20:29፤ ዘዳ 34:8

ዘዳግም 21:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሷ ወዳሻት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 24:1

ዘዳግም 21:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “አንደኛዋ የምትወደድ፣ ሌላኛዋ የምትጠላ ብትሆን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 29:30, 33

ዘዳግም 21:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 25:31፤ 2ዜና 21:3

ዘዳግም 21:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 20:12፤ ዘዳ 27:16፤ ምሳሌ 1:8፤ ኤፌ 6:1
  • +ዘዳ 8:5፤ ምሳሌ 13:24፤ 19:18፤ 23:13፤ ዕብ 12:9

ዘዳግም 21:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 28:7
  • +ሮም 13:13፤ 1ቆሮ 6:10፤ ኤፌ 5:18

ዘዳግም 21:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 13:10, 11

ዘዳግም 21:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 25:5
  • +ኢያሱ 10:26፤ ሥራ 10:39

ዘዳግም 21:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 8:29፤ ዮሐ 19:31
  • +ገላ 3:13
  • +ዘኁ 35:34

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘዳ. 21:2ዘዳ 16:18
ዘዳ. 21:4ዘኁ 35:33
ዘዳ. 21:5ዘኁ 6:23-27፤ 1ዜና 23:13
ዘዳ. 21:5ዘፀ 28:1
ዘዳ. 21:5ዘዳ 17:8, 9
ዘዳ. 21:6መዝ 26:6፤ ማቴ 27:24
ዘዳ. 21:82ሳሙ 7:23
ዘዳ. 21:8ኢሳ 26:21፤ ኤር 26:15
ዘዳ. 21:10ዘኁ 31:9፤ ዘዳ 20:13, 14
ዘዳ. 21:13ዘኁ 20:29፤ ዘዳ 34:8
ዘዳ. 21:14ዘዳ 24:1
ዘዳ. 21:15ዘፍ 29:30, 33
ዘዳ. 21:17ዘፍ 25:31፤ 2ዜና 21:3
ዘዳ. 21:18ዘፀ 20:12፤ ዘዳ 27:16፤ ምሳሌ 1:8፤ ኤፌ 6:1
ዘዳ. 21:18ዘዳ 8:5፤ ምሳሌ 13:24፤ 19:18፤ 23:13፤ ዕብ 12:9
ዘዳ. 21:20ምሳሌ 28:7
ዘዳ. 21:20ሮም 13:13፤ 1ቆሮ 6:10፤ ኤፌ 5:18
ዘዳ. 21:21ዘዳ 13:10, 11
ዘዳ. 21:22ዘኁ 25:5
ዘዳ. 21:22ኢያሱ 10:26፤ ሥራ 10:39
ዘዳ. 21:23ኢያሱ 8:29፤ ዮሐ 19:31
ዘዳ. 21:23ገላ 3:13
ዘዳ. 21:23ዘኁ 35:34
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘዳግም 21:1-23

ዘዳግም

21 “አምላክህ ይሖዋ እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር አንድ ሰው ሜዳ ላይ ተገድሎ ቢገኝና ማን እንደገደለው ባይታወቅ 2 ሽማግሌዎችህና ዳኞችህ+ ወጥተው የሞተው ሰው ከተገኘበት ስፍራ አንስቶ በዙሪያው እስከሚገኙት ከተሞች ድረስ ያለውን ርቀት ይለኩ። 3 ከዚያም የሞተው ሰው ለተገኘበት ስፍራ ቅርብ የሆነችው ከተማ ሽማግሌዎች ምንም ሥራ ያልተሠራባትንና ቀንበር ተጭኖባት የማያውቅን ጊደር ከከብቶች መካከል ይውሰዱ፤ 4 የከተማዋም ሽማግሌዎች ጊደሯን ከዚህ ቀደም ታርሶ ወይም ዘር ተዘርቶበት ወደማያውቅ ወራጅ ውኃ ወዳለበት ሸለቆ* ይውሰዷት፤ በሸለቆውም ውስጥ የጊደሯን አንገት ይስበሩ።+

5 “ሌዋውያኑ ካህናት ይቅረቡ፤ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ እሱን እንዲያገለግሉና በይሖዋ ስም እንዲባርኩ+ የመረጠው እነሱን ነው።+ ደግሞም የኃይል ጥቃትን በተመለከተ ለሚነሳ ለማንኛውም ክርክር እልባት የሚሰጡት እነሱ ናቸው።+ 6 ከዚያም የሞተው ሰው ለተገኘበት ስፍራ ቅርብ የሆኑት የከተማዋ ሽማግሌዎች በሙሉ በሸለቆው ውስጥ አንገቷ በተሰበረው ጊደር ላይ እጃቸውን ይታጠቡ፤+ 7 እንዲህ ብለውም ይናገሩ፦ ‘እጆቻችን ይህን ደም አላፈሰሱም፤ ዓይኖቻችንም ይህ ደም ሲፈስ አላዩም። 8 ይሖዋ ሆይ፣ የታደግከውን+ ሕዝብህን እስራኤልን በዚህ ድርጊት ተጠያቂ አታድርገው፤ ንጹሕ ደም በማፍሰስ የተፈጸመ በደልም በሕዝብህ በእስራኤል መካከል እንዲኖር አትፍቀድ።’+ እነሱም በደም ዕዳው ተጠያቂ አይሆኑም። 9 በዚህ መንገድ ንጹሕ ደም በማፍሰስ የተፈጸመን በደል ከመካከልህ በማስወገድ በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አድርግ።

10 “ከጠላቶችህ ጋር ብትዋጋ፣ አምላክህ ይሖዋም እነሱን በእጅህ አሳልፎ ቢሰጥህ፣ አንተም ምርኮኛ አድርገህ ብትወስዳቸውና+ 11 ከምርኮኞቹ መካከል አንዲት የምታምር ሴት አይተህ ብትወዳት፣ ሚስትህም ልታደርጋት ብትፈልግ 12 ወደ ቤትህ ልትወስዳት ትችላለህ። እሷም ፀጉሯን ትላጭ፤ ጥፍሯንም ትቁረጥ፤ 13 የምርኮኛነት ልብሷን ታውልቅ፤ በቤትህም ትቀመጥ። ለአባቷና ለእናቷ አንድ ወር ሙሉ ታልቅስ፤+ ከዚህ በኋላ ከእሷ ጋር ግንኙነት መፈጸም ትችላለህ፤ አንተ ባሏ ትሆናለህ፤ እሷም ሚስትህ ትሆናለች። 14 በእሷ ካልተደሰትክ ግን ወደፈለገችበት* እንድትሄድ አሰናብታት።+ ሆኖም ለውርደት ስለዳረግካት በገንዘብ ልትሸጣት ወይም ግፍ ልትፈጽምባት አይገባም።

15 “አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ቢኖሩትና አንደኛዋን ከሌላኛዋ አስበልጦ የሚወዳት ቢሆን፣* ሁለቱም ወንዶች ልጆች ቢወልዱለትና በኩሩ የተወለደው ከማይወዳት ሚስቱ+ ቢሆን 16 ውርሱን ለወንዶች ልጆቹ በሚያስተላልፍበት ቀን ከማይወዳት ሚስቱ የተወለደውን በኩር የሆነውን ወንድ ልጅ ትቶ ከሚወዳት ሚስቱ የተወለደውን ወንድ ልጅ እንደ በኩር ልጁ አድርጎ መቁጠር የለበትም። 17 ከዚህ ይልቅ ከማይወዳት ሚስቱ ለተወለደው ወንድ ልጅ፣ ካለው ከማንኛውም ነገር ላይ ሁለት እጥፍ በመስጠት የልጁን ብኩርና መቀበል ይኖርበታል፤ ምክንያቱም የጎልማሳነቱ ብርታት መጀመሪያ ይህ ልጅ ነው። የብኩርና መብቱ የእሱ ነው።+

18 “አንድ ሰው እልኸኛና ዓመፀኛ ልጅ ቢኖረው ልጁም አባቱንም ሆነ እናቱን ለመታዘዝ አሻፈረኝ ቢል፣+ እነሱም እርማት ሊሰጡት ቢሞክሩና እሱ ግን ሊሰማቸው ፈቃደኛ ባይሆን+ 19 አባትና እናቱ እሱ ባለበት ከተማ በር ላይ ወዳሉት ሽማግሌዎች ያምጡት፤ 20 ሽማግሌዎቹንም ‘ይህ ልጃችን እልኸኛና ዓመፀኛ ነው፤ ሊታዘዘንም ፈቃደኛ አይደለም። ሆዳምና+ ሰካራም+ ነው’ ይበሏቸው። 21 ከዚያም የከተማዋ ሰዎች ሁሉ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩት። በዚህ መንገድ ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ፤ እስራኤላውያንም ሁሉ ይህን ሰምተው ይፈራሉ።+

22 “አንድ ሰው ለሞት የሚያበቃ ኃጢአት ሠርቶ ቢገደልና+ በእንጨት ላይ ብትሰቅለው+ 23 በድኑ በእንጨቱ ላይ አይደር።+ ከዚህ ይልቅ በዚያው ዕለት ቅበረው፤ ምክንያቱም እንጨት ላይ የሚሰቀለው፣ አምላክ የረገመው ነው፤+ አንተም አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ የሚሰጥህን ምድር አታርክስ።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ