35 ኤሊሁ እንዲህ ሲል መልስ መስጠቱን ቀጠለ፦
2 “ትክክል እንደሆንክ በጣም እርግጠኛ ከመሆንህ የተነሳ
‘እኔ ከአምላክ ይበልጥ ጻድቅ ነኝ’ ትላለህ?+
3 ደግሞም ‘ይህ ለአንተ ምን ለውጥ ያመጣል?
ኃጢአት ብሠራ ኖሮ ከዚህ የከፋ ነገር ይደርስብኝ ነበር?’ ብለሃልና።+
4 ለአንተና አብረውህ ላሉት ወዳጆችህ፣+
መልስ እሰጣለሁ።
5 ቀና ብለህ ወደ ሰማይ እይ፤
ከአንተ ከፍ ያሉትን ደመናት በጥሞና ተመልከት።+
6 ኃጢአት ብትሠራ እሱን ምን ትጎዳዋለህ?+
በደልህ ቢበዛ እሱን ምን ታደርገዋለህ?+
7 ጻድቅ ብትሆን ለእሱ ምን ትጨምርለታለህ?
ከአንተ እጅ ምን ይቀበላል?+
8 ክፋት ብትሠራ የምትጎዳው እንደ አንተ ያለውን ሰው ብቻ ነው፤
ጽድቅህም የሚጠቅመው የሰውን ልጅ ነው።
9 ሰዎች ከባድ ጭቆና ሲደርስባቸው ይጮኻሉ፤
ከኃያል ሰው የሥልጣን ቀንበር ለመገላገል ይጮኻሉ።+
10 ይሁንና ‘በሌሊት መዝሙር እንዲዘመር የሚያደርገው፣+
ታላቅ ፈጣሪዬ የሆነው አምላክ የት አለ?’ የሚል የለም።+
11 ከምድር እንስሳት+ ይበልጥ እኛን ያስተምረናል፤+
በሰማይ ከሚበርሩ ወፎችም በላይ ጥበበኞች አድርጎናል።
12 በክፉዎች ኩራት የተነሳ ሰዎች ይጮኻሉ፤
ሆኖም እሱ አይመልስላቸውም።+
13 በእርግጥ አምላክ ከንቱ ጩኸት አይሰማም፤+
ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ትኩረት አይሰጠውም።
14 አላየሁትም ብለህ ቅሬታ እያሰማህ፣ አንተንማ እንዴት ይስማህ!+
ጉዳይህ በእሱ ፊት ነው፤ ስለዚህ እሱን በትዕግሥት ተጠባበቅ።+
15 ተቆጥቶ ተጠያቂ አላደረገህምና፤
በችኮላ ያደረግከውንም አልያዘብህም።+
16 ኢዮብ አፉን የሚከፍተው በከንቱ ነው፤
እውቀት ሳይኖረው ብዙ ይናገራል።”+