የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የሐዋርያት ሥራ 11
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሥራ የመጽሐፉ ይዘት

      • ጴጥሮስ ለሐዋርያት ጉዳዩን በዝርዝር አብራራ (1-18)

      • በርናባስና ሳኦል በሶርያ አንጾኪያ (19-26)

        • ደቀ መዛሙርቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ክርስቲያኖች ተብለው ተጠሩ (26)

      • አጋቦስ ረሃብ እንደሚከሰት ተነበየ (27-30)

የሐዋርያት ሥራ 11:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ይሟገቱት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 10:45፤ ገላ 2:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2003፣ ገጽ 21-22

የሐዋርያት ሥራ 11:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 10:10-16

የሐዋርያት ሥራ 11:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 10:17-20

የሐዋርያት ሥራ 11:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 71

የሐዋርያት ሥራ 11:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 10:30-33

የሐዋርያት ሥራ 11:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 2:1, 4፤ 10:44, 45

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 8/2016፣ ገጽ 1

የሐዋርያት ሥራ 11:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 3:11፤ ማር 1:8፤ ሉቃስ 3:16፤ ሥራ 1:5
  • +ኢዩ 2:28፤ ዮሐ 1:33፤ ሥራ 2:17

የሐዋርያት ሥራ 11:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ማገድ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 10:47

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 72-73

የሐዋርያት ሥራ 11:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ዝም አሉ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 11:10፤ ሥራ 17:30፤ ሮም 10:12፤ 15:8, 9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/1996፣ ገጽ 16

የሐዋርያት ሥራ 11:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 8:1
  • +ማቴ 10:5, 6

የሐዋርያት ሥራ 11:20

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 74

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2000፣ ገጽ 25

የሐዋርያት ሥራ 11:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 2:47፤ 9:35

የሐዋርያት ሥራ 11:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 4:36, 37

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2000፣ ገጽ 25

የሐዋርያት ሥራ 11:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 13:43፤ 14:21, 22

የሐዋርያት ሥራ 11:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 2:47፤ 4:4፤ 5:14፤ 9:31

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2000፣ ገጽ 25

የሐዋርያት ሥራ 11:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 21:39

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2000፣ ገጽ 25

የሐዋርያት ሥራ 11:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 9:2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መመሥከር፣ ገጽ 74-76

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/2000፣ ገጽ 25-26

የሐዋርያት ሥራ 11:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 12:28፤ ኤፌ 4:11

የሐዋርያት ሥራ 11:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 21:10, 11
  • +ማቴ 24:7

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    4/2023፣ ገጽ 16

    መመሥከር፣ ገጽ 74-76

    ንቁ!፣

    4/2011፣ ገጽ 11

የሐዋርያት ሥራ 11:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 8:12
  • +ገላ 2:10

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/15/1998፣ ገጽ 21

የሐዋርያት ሥራ 11:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 12:25

ተዛማጅ ሐሳብ

ሥራ 11:2ሥራ 10:45፤ ገላ 2:12
ሥራ 11:5ሥራ 10:10-16
ሥራ 11:11ሥራ 10:17-20
ሥራ 11:13ሥራ 10:30-33
ሥራ 11:15ሥራ 2:1, 4፤ 10:44, 45
ሥራ 11:16ማቴ 3:11፤ ማር 1:8፤ ሉቃስ 3:16፤ ሥራ 1:5
ሥራ 11:16ኢዩ 2:28፤ ዮሐ 1:33፤ ሥራ 2:17
ሥራ 11:17ሥራ 10:47
ሥራ 11:18ኢሳ 11:10፤ ሥራ 17:30፤ ሮም 10:12፤ 15:8, 9
ሥራ 11:19ሥራ 8:1
ሥራ 11:19ማቴ 10:5, 6
ሥራ 11:21ሥራ 2:47፤ 9:35
ሥራ 11:22ሥራ 4:36, 37
ሥራ 11:23ሥራ 13:43፤ 14:21, 22
ሥራ 11:24ሥራ 2:47፤ 4:4፤ 5:14፤ 9:31
ሥራ 11:25ሥራ 21:39
ሥራ 11:26ሥራ 9:2
ሥራ 11:271ቆሮ 12:28፤ ኤፌ 4:11
ሥራ 11:28ሥራ 21:10, 11
ሥራ 11:28ማቴ 24:7
ሥራ 11:292ቆሮ 8:12
ሥራ 11:29ገላ 2:10
ሥራ 11:30ሥራ 12:25
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
የሐዋርያት ሥራ 11:1-30

የሐዋርያት ሥራ

11 በይሁዳ የነበሩት ሐዋርያትና ወንድሞች፣ አሕዛብም የአምላክን ቃል እንደተቀበሉ ሰሙ። 2 ስለዚህ ጴጥሮስ ወደ ኢየሩሳሌም በወጣ ጊዜ ግርዘትን የሚደግፉ ሰዎች+ ይተቹት* ጀመር፤ 3 “ወዳልተገረዙ ሰዎች ቤት ሄደህ ከእነሱ ጋር በልተሃል” አሉት። 4 በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ እንዲህ ሲል ጉዳዩን በዝርዝር አብራራላቸው፦

5 “በኢዮጴ ከተማ እየጸለይኩ ሳለ ሰመመን ውስጥ ሆኜ ራእይ አየሁ፤ አንድ ትልቅ ጨርቅ የሚመስል ነገር በአራቱም ጫፍ ተይዞ ከሰማይ ወረደና ወደ እኔ መጣ።+ 6 ይህን ነገር ትኩር ብዬ ስመለከት አራት እግር ያላቸው የምድር እንስሳት፣ የዱር አራዊት፣ በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትና የሰማይ ወፎች አየሁ። 7 በተጨማሪም አንድ ድምፅ ‘ጴጥሮስ፣ ተነሳና አርደህ ብላ!’ ሲለኝ ሰማሁ። 8 እኔ ግን ‘ጌታ ሆይ፣ በጭራሽ፤ ምክንያቱም ንጹሕ ያልሆነ ወይም የረከሰ ነገር ወደ አፌ ገብቶ አያውቅም’ አልኩ። 9 ለሁለተኛ ጊዜ ከሰማይ የመጣው ድምፅ ‘አምላክ ንጹሕ ያደረገውን ነገር ርኩስ ነው ማለትህን ተው’ ሲል መለሰልኝ። 10 ይህም ለሦስተኛ ጊዜ ተደገመ፤ ከዚያም ሁሉም ነገር እንደገና ወደ ሰማይ ተወሰደ። 11 ልክ በዚያው ሰዓት ደግሞ ከቂሳርያ ወደ እኔ የተላኩ ሦስት ሰዎች እኛ ወደነበርንበት ቤት ደረሱ።+ 12 በዚህ ጊዜ መንፈስ፣ ምንም ሳልጠራጠር አብሬያቸው እንድሄድ ነገረኝ። እነዚህ ስድስት ወንድሞችም አብረውኝ ሄዱ፤ ወደ ሰውየውም ቤት ገባን።

13 “እሱም በቤቱ ውስጥ መልአክ ቆሞ እንዳየና እንዲህ እንዳለው ነገረን፦ ‘ወደ ኢዮጴ ሰዎች ልከህ ጴጥሮስ ተብሎ የሚጠራውን ስምዖንን አስጠራ፤+ 14 እሱም አንተና መላው ቤተሰብህ መዳን ልታገኙ የምትችሉበትን ነገር ሁሉ ይነግርሃል።’ 15 እኔም መናገር ስጀምር መንፈስ ቅዱስ በመጀመሪያ በእኛ ላይ እንደወረደው ሁሉ በእነሱም ላይ ወረደ።+ 16 በዚህ ጊዜ፣ ‘ዮሐንስ በውኃ አጠመቀ፤+ እናንተ ግን በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ’+ እያለ ጌታ ይናገር የነበረውን ቃል አስታወስኩ። 17 እንግዲህ አምላክ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ላመንነው ለእኛ የሰጠውን ያንኑ ነፃ ስጦታ ለእነሱም ከሰጠ፣ ታዲያ አምላክን መከልከል* የምችል እኔ ማን ነኝ?”+

18 እነሱም ይህን በሰሙ ጊዜ መቃወማቸውን ተዉ፤* ደግሞም “እንዲህ ከሆነማ አምላክ አሕዛብም ሕይወት ማግኘት እንዲችሉ ንስሐ የሚገቡበት አጋጣሚ ሰጥቷቸዋል ማለት ነው” እያሉ አምላክን አከበሩ።+

19 ከእስጢፋኖስ ሞት በኋላ በተቀሰቀሰው ስደት የተነሳ የተበተኑት ደቀ መዛሙርት+ እስከ ፊንቄ፣ ቆጵሮስና አንጾኪያ ድረስ ሄዱ፤ ቃሉን ይናገሩ የነበረው ግን ለአይሁዳውያን ብቻ ነበር።+ 20 ይሁን እንጂ ከእነሱ መካከል የቆጵሮስና የቀሬና ሰዎች የሆኑ አንዳንዶች ወደ አንጾኪያ መጥተው ግሪክኛ ተናጋሪ የሆኑ ሰዎችን በማነጋገር የጌታ ኢየሱስን ምሥራች ይሰብኩላቸው ጀመር። 21 የይሖዋም* እጅ ከእነሱ ጋር ነበር፤ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎችም አማኝ በመሆን ጌታን መከተል ጀመሩ።+

22 በኢየሩሳሌም የሚገኘው ጉባኤ ስለ እነሱ የሚገልጸው ወሬ ደረሰው፤ በዚህ ጊዜ በርናባስን+ ወደ አንጾኪያ ላኩት። 23 እሱም እዚያ ደርሶ አምላክ ለደቀ መዛሙርቱ ያሳየውን ጸጋ ባስተዋለ ጊዜ በጣም ተደሰተ፤ ሁሉም በጽኑ ልብ ለጌታ ታማኞች ሆነው እንዲቀጥሉም አበረታታቸው፤+ 24 በርናባስ መንፈስ ቅዱስ የሞላበትና ጠንካራ እምነት ያለው ጥሩ ሰው ነበር። ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎችም በጌታ አመኑ።+ 25 በመሆኑም ሳኦልን ፈልጎ ለማግኘት ወደ ጠርሴስ ሄደ።+ 26 ካገኘውም በኋላ ወደ አንጾኪያ አመጣው። ከዚያም አንድ ዓመት ሙሉ ከእነሱ ጋር በጉባኤ አብረው እየተሰበሰቡ ብዙ ሕዝብ አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርቱም በመለኮታዊ አመራር ለመጀመሪያ ጊዜ ‘ክርስቲያኖች’ ተብለው የተጠሩት+ በአንጾኪያ ነበር።

27 በዚያን ጊዜ ነቢያት+ ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ወረዱ። 28 ከእነሱም መካከል አጋቦስ+ የተባለው ተነስቶ በምድሪቱ ሁሉ ታላቅ ረሃብ እንደሚከሰት መንፈስ አነሳስቶት ትንቢት ተናገረ፤+ ይህም በቀላውዴዎስ ዘመን ተፈጸመ። 29 ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ እያንዳንዳቸው አቅማቸው በፈቀደ መጠን+ አዋጥተው በይሁዳ ለሚኖሩ ወንድሞች እርዳታ ለመላክ ወሰኑ፤+ 30 እርዳታውንም በበርናባስና በሳኦል እጅ ለሽማግሌዎቹ ላኩ።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ