የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፀአት 33
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘፀአት የመጽሐፉ ይዘት

      • አምላክ ሕዝቡን ገሠጸ (1-6)

      • የመገናኛ ድንኳኑ ከሰፈሩ ውጭ ተተከለ (7-11)

      • ሙሴ የይሖዋን ክብር ለማየት ጠየቀ (12-23)

ዘፀአት 33:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 12:7፤ 26:3

ዘፀአት 33:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 23:20፤ 32:34
  • +ዘዳ 7:1, 22፤ ኢያሱ 24:11

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የዳንኤል ትንቢት፣ ገጽ 204-205

ዘፀአት 33:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “አንገተ ደንዳና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 3:8፤ ዘዳ 8:7-9
  • +ዘፀ 32:9፤ ዘዳ 9:6፤ ሥራ 7:51
  • +ዘፀ 32:10፤ ዘኁ 16:21

ዘፀአት 33:5

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “አንገተ ደንዳና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 34:9፤ ዘዳ 9:6፤ ሥራ 7:51
  • +ዘኁ 16:45

ዘፀአት 33:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 18:25, 26፤ ዘኁ 27:1-5

ዘፀአት 33:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 11:16, 17፤ 12:5
  • +ዘፀ 13:21፤ መዝ 99:7

ዘፀአት 33:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 33:22, 23፤ ዘኁ 12:8፤ ዘዳ 34:10፤ ዮሐ 1:18፤ 6:46፤ ሥራ 7:38
  • +ዘፀ 17:9፤ 24:13
  • +ዘኁ 11:28፤ ዘዳ 1:38፤ ኢያሱ 1:1

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 83

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2004፣ ገጽ 27

    12/1/2002፣ ገጽ 10

    10/1/1997፣ ገጽ 4-5

ዘፀአት 33:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “መርጬሃለሁ።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 10/2020፣ ገጽ 3

ዘፀአት 33:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 25:4፤ 27:11፤ 86:11፤ 119:33፤ ኢሳ 30:21
  • +ዘዳ 9:26

ዘፀአት 33:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ፊቴ ከአንተ ጋር ይሄዳል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 13:21፤ 40:34፤ ኢያሱ 1:5, 17፤ ኢሳ 63:9
  • +ኢያሱ 21:44፤ 23:1

ዘፀአት 33:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ፊትህ ከእኛ ጋር የማይሄድ።”

ዘፀአት 33:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 4:34፤ 2ሳሙ 7:23፤ መዝ 147:20
  • +ዘኁ 14:13, 14

ዘፀአት 33:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 3:13፤ 6:3፤ 34:6
  • +ሮም 9:15

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    3/2019፣ ገጽ 26

ዘፀአት 33:20

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ወደ ይሖዋ ቅረብ፣ ገጽ 12-13

    ጠለቅ ብሎ ማስተዋል፣

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/15/1999፣ ገጽ 19-20

ዘፀአት 33:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 1:18

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘፀ. 33:1ዘፍ 12:7፤ 26:3
ዘፀ. 33:2ዘፀ 23:20፤ 32:34
ዘፀ. 33:2ዘዳ 7:1, 22፤ ኢያሱ 24:11
ዘፀ. 33:3ዘፀ 3:8፤ ዘዳ 8:7-9
ዘፀ. 33:3ዘፀ 32:9፤ ዘዳ 9:6፤ ሥራ 7:51
ዘፀ. 33:3ዘፀ 32:10፤ ዘኁ 16:21
ዘፀ. 33:5ዘፀ 34:9፤ ዘዳ 9:6፤ ሥራ 7:51
ዘፀ. 33:5ዘኁ 16:45
ዘፀ. 33:7ዘፀ 18:25, 26፤ ዘኁ 27:1-5
ዘፀ. 33:9ዘኁ 11:16, 17፤ 12:5
ዘፀ. 33:9ዘፀ 13:21፤ መዝ 99:7
ዘፀ. 33:11ዘፀ 33:22, 23፤ ዘኁ 12:8፤ ዘዳ 34:10፤ ዮሐ 1:18፤ 6:46፤ ሥራ 7:38
ዘፀ. 33:11ዘፀ 17:9፤ 24:13
ዘፀ. 33:11ዘኁ 11:28፤ ዘዳ 1:38፤ ኢያሱ 1:1
ዘፀ. 33:13መዝ 25:4፤ 27:11፤ 86:11፤ 119:33፤ ኢሳ 30:21
ዘፀ. 33:13ዘዳ 9:26
ዘፀ. 33:14ዘፀ 13:21፤ 40:34፤ ኢያሱ 1:5, 17፤ ኢሳ 63:9
ዘፀ. 33:14ኢያሱ 21:44፤ 23:1
ዘፀ. 33:16ዘዳ 4:34፤ 2ሳሙ 7:23፤ መዝ 147:20
ዘፀ. 33:16ዘኁ 14:13, 14
ዘፀ. 33:19ዘፀ 3:13፤ 6:3፤ 34:6
ዘፀ. 33:19ሮም 9:15
ዘፀ. 33:23ዮሐ 1:18
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘፀአት 33:1-23

ዘፀአት

33 በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከግብፅ መርተህ ካወጣኸው ሕዝብ ጋር ከዚህ ተነስተህ ሂድ። ‘ለዘርህ እሰጠዋለሁ’ በማለት ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደማልኩላቸውም ምድር ተጓዝ።+ 2 እኔም ከአንተ አስቀድሜ መልአክ በመላክ+ ከነአናውያንን፣ አሞራውያንን፣ ሂታውያንን፣ ፈሪዛውያንን፣ ሂዋውያንንና ኢያቡሳውያንን አስወጣለሁ።+ 3 ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር+ ሂዱ። ሆኖም እናንተ ግትር* ሕዝብ ስለሆናችሁ+ በመንገድ ላይ እንዳላጠፋችሁ+ በመካከላችሁ ሆኜ አብሬያችሁ አልሄድም።”

4 ሕዝቡም ይህን ኃይለኛ ንግግር ሲሰሙ በሐዘን ተዋጡ፤ ከመካከላቸውም ማንም ጌጡን አላደረገም። 5 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘እናንተ ግትር* ሕዝብ ናችሁ።+ ለአንድ አፍታ በመካከላችሁ አልፌ ላጠፋችሁ እችል ነበር።+ በእናንተ ላይ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እስክወስን ድረስ ጌጣጌጣችሁን አውልቁ።’” 6 ስለዚህ እስራኤላውያን ከኮሬብ ተራራ አንስቶ ጌጣጌጣቸውን ማድረግ ተዉ።

7 ሙሴም የራሱን ድንኳን ወስዶ ከሰፈሩ ውጭ ማለትም ከሰፈሩ ትንሽ ራቅ አድርጎ ተከለው፤ ድንኳኑንም የመገናኛ ድንኳን ብሎ ጠራው። ይሖዋን የሚጠይቅ+ ማንኛውም ሰው ከሰፈሩ ውጭ ወዳለው የመገናኛ ድንኳን ይሄድ ነበር። 8 ሙሴ ወደ ድንኳኑ ሲሄድ ሕዝቡ በሙሉ ተነስተው በየድንኳናቸው መግቢያ ላይ በመቆም ሙሴ ወደ ድንኳኑ እስኪገባ ድረስ ትክ ብለው ይመለከቱት ነበር። 9 ሙሴ ወደ ድንኳኑ ገብቶ አምላክ ከሙሴ ጋር በሚነጋገርበት+ ጊዜ የደመናው ዓምድ+ ወርዶ በድንኳኑ መግቢያ ላይ ይቆማል። 10 ሕዝቡም ሁሉ የደመናው ዓምድ በድንኳኑ መግቢያ ላይ ቆሞ ሲመለከት እያንዳንዳቸው ተነስተው በየድንኳናቸው መግቢያ ላይ ይሰግዱ ነበር። 11 አንድ ሰው ከሌላ ሰው ጋር እንደሚነጋገር ይሖዋ ከሙሴ ጋር ፊት ለፊት ይነጋገር ነበር።+ ሙሴ ወደ ሰፈሩ በሚመለስበት ጊዜ አገልጋዩና ረዳቱ+ የነበረው የነዌ ልጅ ኢያሱ+ ከድንኳኑ አይለይም ነበር።

12 ሙሴም ይሖዋን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ ‘ይህን ሕዝብ ምራ’ እያልከኝ ነው፤ ሆኖም ከእኔ ጋር ማንን እንደምትልክ አላሳወቅከኝም። ከዚህም በላይ ‘በስም አውቄሃለሁ፤* ደግሞም በፊቴ ሞገስ አግኝተሃል’ ብለኸኝ ነበር። 13 እባክህ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ እንዳውቅህና በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንድኖር መንገድህን አሳውቀኝ።+ እንዲሁም ይህ ብሔር ሕዝብህ እንደሆነ አስብ።”+ 14 በመሆኑም እሱ “እኔ ራሴ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፤*+ እረፍትም እሰጥሃለሁ” አለው።+ 15 ከዚያም ሙሴ እንዲህ አለው፦ “አንተ ራስህ ከእኛ ጋር የማትሄድ* ከሆነ ይህን ቦታ ለቅቀን እንድንሄድ አታድርገን። 16 ታዲያ እኔም ሆንኩ ሕዝብህ በፊትህ ሞገስ እንዳገኘን የሚታወቀው እንዴት ነው? እኔም ሆንኩ ሕዝብህ በምድር ላይ ካሉ ሌሎች ሕዝቦች ሁሉ የተለየን እንድንሆን+ ስትል አብረኸን በመሄድህ አይደለም?”+

17 ይሖዋም ሙሴን “በፊቴ ሞገስ ስላገኘህና በስም ስላወቅኩህ የጠየቅከውን ይህን ነገር እፈጽማለሁ” አለው። 18 እሱም በዚህ ጊዜ “እባክህ ክብርህን አሳየኝ” አለው። 19 ሆኖም እሱ እንዲህ አለው፦ “እኔ ራሴ ጥሩነቴ ሁሉ በፊትህ እንዲያልፍ አደርጋለሁ፤ ይሖዋ የተባለውንም ስሜን በፊትህ አውጃለሁ።+ ሞገስ ላሳየው የምፈልገውን ሞገስ አሳየዋለሁ፤ ልምረው የምፈልገውን ደግሞ እምረዋለሁ።”+ 20 ሆኖም “ማንም ሰው አይቶኝ በሕይወት መኖር ስለማይችል ፊቴን ማየት አትችልም” አለው።

21 በተጨማሪም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “ይኸው አጠገቤ ቦታ አለ። አንተም በዓለቱ ላይ ቁም። 22 ክብሬ በዚያ በሚያልፍበትም ጊዜ በዓለቱ ዋሻ ውስጥ አስቀምጥሃለሁ፤ እስከማልፍም ድረስ በእጄ እጋርድሃለሁ። 23 ከዚያም እጄን አነሳለሁ፤ አንተም ጀርባዬን ታያለህ። ፊቴ ግን አይታይም።”+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ