የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ቆሮንቶስ 8
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ቆሮንቶስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ለአይሁዳውያን ክርስቲያኖች መዋጮ ማሰባሰብ (1-15)

      • ቲቶን ወደ ቆሮንቶስ ለመላክ ታሰበ (16-24)

2 ቆሮንቶስ 8:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 15:26

2 ቆሮንቶስ 8:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የተትረፈረፈ።”

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2001፣ ገጽ 30

    11/1/1998፣ ገጽ 25-26

2 ቆሮንቶስ 8:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 11:29፤ 2ቆሮ 9:7
  • +ማር 12:43, 44

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/1/1998፣ ገጽ 25-26

2 ቆሮንቶስ 8:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 15:25, 26፤ 1ቆሮ 16:1፤ 2ቆሮ 9:1, 2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ፣

    5/2019፣ ገጽ 3

    የአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!፣ ገጽ 209-210

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2001፣ ገጽ 30

    11/1/1998፣ ገጽ 25-26

2 ቆሮንቶስ 8:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 12:18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    11/15/1998፣ ገጽ 30

2 ቆሮንቶስ 8:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ጢሞ 6:18

2 ቆሮንቶስ 8:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 8:20፤ ፊልጵ 2:7

2 ቆሮንቶስ 8:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 7:25

2 ቆሮንቶስ 8:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 16:10, 17፤ ምሳሌ 3:27, 28

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    12/15/2013፣ ገጽ 15

    12/1/2012፣ ገጽ 5

    11/1/2000፣ ገጽ 29

    11/1/1998፣ ገጽ 26

2 ቆሮንቶስ 8:13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመንግሥት አገልግሎት፣

    6/1998፣ ገጽ 4-5

2 ቆሮንቶስ 8:14

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የምታደርጉት መዋጮ ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው እንዴት ነው?፣ ርዕስ 5

    የመንግሥት አገልግሎት፣

    6/1998፣ ገጽ 4-5

2 ቆሮንቶስ 8:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 16:18

2 ቆሮንቶስ 8:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 12:18

2 ቆሮንቶስ 8:18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    7/15/1998፣ ገጽ 7

2 ቆሮንቶስ 8:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 16:1

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    3/15/2001፣ ገጽ 30-31

2 ቆሮንቶስ 8:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 3:4፤ 1ጴጥ 2:12

2 ቆሮንቶስ 8:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ጴጥ 1:22፤ 2:17

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ቆሮ. 8:1ሮም 15:26
2 ቆሮ. 8:3ሥራ 11:29፤ 2ቆሮ 9:7
2 ቆሮ. 8:3ማር 12:43, 44
2 ቆሮ. 8:4ሮም 15:25, 26፤ 1ቆሮ 16:1፤ 2ቆሮ 9:1, 2
2 ቆሮ. 8:62ቆሮ 12:18
2 ቆሮ. 8:71ጢሞ 6:18
2 ቆሮ. 8:9ማቴ 8:20፤ ፊልጵ 2:7
2 ቆሮ. 8:101ቆሮ 7:25
2 ቆሮ. 8:12ዘዳ 16:10, 17፤ ምሳሌ 3:27, 28
2 ቆሮ. 8:15ዘፀ 16:18
2 ቆሮ. 8:162ቆሮ 12:18
2 ቆሮ. 8:201ቆሮ 16:1
2 ቆሮ. 8:21ምሳሌ 3:4፤ 1ጴጥ 2:12
2 ቆሮ. 8:241ጴጥ 1:22፤ 2:17
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ቆሮንቶስ 8:1-24

ለቆሮንቶስ ሰዎች የተጻፈ ሁለተኛው ደብዳቤ

8 ወንድሞች፣ በመቄዶንያ+ ላሉት ጉባኤዎች ስለተሰጠው የአምላክ ጸጋ እንድታውቁ እንፈልጋለን። 2 ከባድ ፈተና ደርሶባቸው በመከራ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ታላቅ ደስታ የነበራቸው ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ* ልግስና አሳይተዋል፤ ይህን ያደረጉት በጣም ድሆች ሆነው ሳለ ነው። 3 እንደ አቅማቸው+ እንዲያውም ከአቅማቸው በላይ እንደሰጡ እመሠክርላቸዋለሁና፤+ 4 ምክንያቱም እነዚህ ወንድሞች ለቅዱሳን በልግስና በመስጠት፣ በእርዳታ አገልግሎቱ ለመካፈል መብት እንዲሰጣቸው በራሳቸው ፍላጎት ተነሳስተው ይለምኑን እንዲያውም ይማጸኑን ነበር።+ 5 ደግሞም ከጠበቅነው በላይ አድርገዋል፤ ምክንያቱም ራሳቸውን በመጀመሪያ ለጌታ ከዚያም በአምላክ ፈቃድ ለእኛ ሰጥተዋል። 6 ስለዚህ ቲቶ+ ቀደም ሲል በእናንተ መካከል የልግስና ስጦታችሁን የማሰባሰቡን ሥራ እንዳስጀመረ ሁሉ ይህንኑ ሥራ ወደ ፍጻሜ እንዲያደርስ አበረታታነው። 7 ስለዚህ በሁሉም ነገር ይኸውም በእምነት፣ በቃል፣ በእውቀት፣ በትጋት ሁሉና እኛ ለእናንተ ባለን ፍቅር ባለጸጋ እንደሆናችሁ ሁሉ በልግስና በመስጠት ረገድም ባለጸጋ ሁኑ።+

8 ይህን የምላችሁ እናንተን ለማዘዝ ሳይሆን ሌሎች የሚያሳዩትን ትጋት እንድታውቁ ለማድረግና የፍቅራችሁን እውነተኝነት ለመፈተን ነው። 9 የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ ታውቃላችሁና፤ በእሱ ድህነት እናንተ ባለጸጋ ትሆኑ ዘንድ እሱ ባለጸጋ ሆኖ ሳለ ለእናንተ ሲል ድሃ ሆኗል።+

10 በዚህ ረገድ የምሰጠው ሐሳብ አለ፦+ ይህን ሥራ መሥራታችሁ ይጠቅማችኋል፤ ምክንያቱም ከአንድ ዓመት በፊት ሥራውን መጀመር ብቻ ሳይሆን ዳር ለማድረስም ፍላጎት እንዳላችሁ አሳይታችኋል። 11 ስለዚህ የጀመራችሁትን ሥራ ዳር አድርሱት፤ ሥራውን ለመጀመር ጓጉታችሁ እንደነበር ሁሉ፣ አሁንም እንደ አቅማችሁ በመስጠት ከፍጻሜ እንዲደርስ አድርጉ። 12 ለመስጠት ፈቃደኝነቱ ካለ ስጦታው ይበልጥ ተቀባይነት የሚኖረው አንድ ሰው ባለው መጠን ሲሰጥ+ እንጂ በሌለው መጠን ሲሰጥ አይደለምና። 13 ይህን የምለውም ሌሎች እንዲቀላቸው አድርጌ እናንተ እንዲከብዳችሁ ለማድረግ አይደለም፤ 14 ከዚህ ይልቅ በአሁኑ ጊዜ የእናንተ ትርፍ የእነሱን ጉድለት እንዲሸፍን ነው፤ የእነሱ ትርፍ ደግሞ የእናንተን ጉድለት ይሸፍናል፤ ይህም ሸክሙን እኩል እንድትጋሩ ያስችላል። 15 ይህ ደግሞ “ብዙ የሰበሰበ ብዙ አላተረፈም፤ ጥቂት የሰበሰበም ምንም አልጎደለበትም” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።+

16 እኛ ለእናንተ ያለንን ዓይነት ልባዊ አሳቢነት በቲቶ+ ልብ ውስጥ ያሳደረ አምላክ የተመሰገነ ይሁን፤ 17 ምክንያቱም ቲቶ ወደ እናንተ የሚመጣው የእኛን ማበረታቻ በመቀበል ብቻ ሳይሆን በታላቅ ጉጉት፣ በራሱ ፈቃድ ተነሳስቶ ነው። 18 ይሁንና ከምሥራቹ ጋር በተያያዘ እያከናወነ ባለው ሥራ በጉባኤዎች ሁሉ የተመሰገነውን ወንድም ከእሱ ጋር እንልከዋለን። 19 ከዚህም በላይ ጌታን ለማስከበርና ሌሎችን ለመርዳት ዝግጁ መሆናችንን ለማሳየት ይህን የልግስና ስጦታ በምናከፋፍልበት ጊዜ ይህ ወንድም የጉዞ አጋራችን እንዲሆን በጉባኤዎች ተሹሟል። 20 ስለዚህ እኛ ከምናከፋፍለው የልግስና መዋጯችሁ ጋር በተያያዘ ማንም ሰው ምንም ዓይነት ስህተት እንዳያገኝብን እንጠነቀቃለን።+ 21 ምክንያቱም ‘በይሖዋ* ፊት ብቻ ሳይሆን በሰዎችም ፊት ሁሉንም ነገር በሐቀኝነት እናከናውናለን።’+

22 በተጨማሪም በተደጋጋሚ ጊዜ በብዙ ነገር ተፈትኖ ትጉ ሆኖ ያገኘነውን ወንድማችንን ከእነሱ ጋር እንልከዋለን፤ እንዲያውም አሁን በእናንተ ላይ ባለው ጠንካራ እምነት የተነሳ ትጋቱ እጅግ ጨምሯል። 23 ይሁን እንጂ ቲቶን በተመለከተ ጥያቄ የሚያነሳ ካለ እሱ ለእናንተ ጥቅም አብሮኝ የሚሠራ ባልደረባዬ ነው፤ ወይም ደግሞ ስለ ወንድሞቻችን ጥያቄ ካለ እነሱ የጉባኤዎች ሐዋርያትና የክርስቶስ ክብር ናቸው። 24 ስለሆነም ለእነሱ ያላችሁን ፍቅር እውነተኝነት በተጨባጭ አስመሥክሩ፤+ እንዲሁም በእናንተ የምንኮራው ለምን እንደሆነ ለጉባኤዎቹ አሳዩ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ