የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 32
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘዳግም የመጽሐፉ ይዘት

      • የሙሴ መዝሙር (1-47)

        • ይሖዋ ዓለት ነው (4)

        • እስራኤል ዓለት የሆነለትን አምላክ ረሳ (18)

        • ‘በቀል የእኔ ነው’ (35)

        • “እናንተ ብሔራት ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ” (43)

      • ሙሴ በነቦ ተራራ ላይ እንደሚሞት ተነገረው (48-52)

ዘዳግም 32:2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    6/2020፣ ገጽ 10

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    4/2016፣ ገጽ 3-4

ዘዳግም 32:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 17:26
  • +1ዜና 29:11፤ መዝ 145:3

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    6/2020፣ ገጽ 10-11

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 10/2020፣ ገጽ 3

ዘዳግም 32:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 22:31፤ መዝ 18:2፤ 19:7፤ ያዕ 1:17
  • +መዝ 33:5
  • +ዘዳ 25:16
  • +ዘዳ 7:9፤ 1ጴጥ 4:19
  • +ዘፍ 18:25

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 125

    ወደ ይሖዋ ቅረብ፣ ገጽ 112

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/1/2009፣ ገጽ 14

    9/15/2004፣ ገጽ 27

ዘዳግም 32:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 31:27፤ መሳ 2:19፤ መዝ 14:1
  • +ኢሳ 1:4
  • +መዝ 78:8፤ ሉቃስ 9:41

ዘዳግም 32:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 4:22
  • +ኢሳ 1:2
  • +ዘፀ 4:22፤ ዘዳ 32:18፤ ኢሳ 63:16

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    9/1/2008፣ ገጽ 5

ዘዳግም 32:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 13:14፤ መዝ 44:1

ዘዳግም 32:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “የሰው ዘርን” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 10:5፤ መዝ 115:16
  • +ዘፍ 11:9
  • +ዘፍ 15:18፤ ዘፀ 23:31
  • +ዘዳ 2:5, 19፤ ሥራ 17:26

ዘዳግም 32:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 19:5፤ ዘዳ 7:6
  • +መዝ 78:71

ዘዳግም 32:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 8:14, 15
  • +ኤር 2:6
  • +ነህ 9:19, 20
  • +ዘካ 2:8

ዘዳግም 32:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 19:4

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/1/2001፣ ገጽ 9

    6/15/2001፣ ገጽ 26

    6/15/1996፣ ገጽ 11

ዘዳግም 32:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ያዕቆብን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 1:31
  • +ኢሳ 43:12

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/1/2001፣ ገጽ 9

    6/15/2001፣ ገጽ 26

ዘዳግም 32:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 33:29
  • +ዘዳ 8:7, 8

ዘዳግም 32:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ከበጉ ስብ።”

  • *

    ቃል በቃል “ከስንዴው ኩላሊት ስብ።”

  • *

    ወይም “ጭማቂ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 147:14

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    12/15/2015፣ ገጽ 15

    9/15/2004፣ ገጽ 27

ዘዳግም 32:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ቅን የሆነው” የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን ለእስራኤል የተሰጠ የማዕረግ ስም ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 31:20፤ ነህ 9:25
  • +ኢሳ 1:4፤ ሆሴዕ 13:6

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 9/2021፣ ገጽ 1

ዘዳግም 32:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 2:12፤ 1ነገ 14:22፤ 1ቆሮ 10:21, 22
  • +2ነገ 23:13፤ ሕዝ 8:17

ዘዳግም 32:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 17:7፤ መዝ 106:37፤ 1ቆሮ 10:20

ዘዳግም 32:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 106:21፤ ኢሳ 17:10፤ ኤር 2:32
  • +ዘዳ 4:34

ዘዳግም 32:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 2:14፤ መዝ 78:59

ዘዳግም 32:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 31:17
  • +ዘዳ 32:5፤ ኢሳ 65:2፤ ማቴ 17:17
  • +ኢሳ 1:2

ዘዳግም 32:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 96:5፤ 1ቆሮ 10:21, 22
  • +1ሳሙ 12:10, 21
  • +ሆሴዕ 2:23፤ ሮም 9:25፤ 11:11፤ 1ጴጥ 2:10
  • +ሮም 10:19

ዘዳግም 32:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሰቆ 4:11
  • +አሞጽ 9:2

ዘዳግም 32:24

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:53
  • +ዘዳ 28:21, 22
  • +ዘሌ 26:22

ዘዳግም 32:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 36:17፤ ሰቆ 2:21
  • +ሰቆ 1:20
  • +ሕዝ 7:15

ዘዳግም 32:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 12:22፤ ሕዝ 20:14
  • +ዘፀ 32:12፤ ዘኁ 14:15, 16
  • +መዝ 115:2

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 5/2017፣ ገጽ 3

ዘዳግም 32:28

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ምክር የማይሰማ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 13:15

ዘዳግም 32:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 81:13
  • +ሆሴዕ 14:9
  • +ኤር 2:19

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ትምህርት 35

    መጠበቂያ ግንብ፣

    9/1/2008፣ ገጽ 8-11

    7/1/1999፣ ገጽ 32

ዘዳግም 32:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 2:14፤ 1ሳሙ 12:9
  • +2ዜና 24:24

ዘዳግም 32:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 2:2
  • +ዘፀ 14:25፤ 1ሳሙ 4:8፤ ዕዝራ 1:2, 3

ዘዳግም 32:32

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ይሁዳ 7
  • +ኢሳ 5:4፤ ኤር 2:21

ዘዳግም 32:33

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    በእስያና በአፍሪካ የሚገኝ እጅግ መርዘኛ የሆነ እባብ፤ ኮብራ።

ዘዳግም 32:34

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 2:5

ዘዳግም 32:35

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ናሆም 1:2፤ ሮም 12:19፤ ዕብ 10:30
  • +መዝ 73:12, 18

ዘዳግም 32:36

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በእነሱ ይጸጸታል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕብ 10:30
  • +መሳ 2:18፤ መዝ 90:13፤ 106:45፤ 135:14

ዘዳግም 32:37

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 10:14

ዘዳግም 32:38

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ምርጥ የሆኑ መሥዋዕቶቻቸውን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሆሴዕ 2:8፤ 1ቆሮ 10:20, 21

ዘዳግም 32:39

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 41:4፤ 48:12
  • +ዘዳ 4:35
  • +1ሳሙ 2:6፤ መዝ 68:20
  • +2ዜና 21:16, 18
  • +ዘኁ 12:13፤ ኤር 17:14
  • +ኢሳ 43:13

ዘዳግም 32:40

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ጢሞ 1:17፤ ራእይ 10:5, 6

ዘዳግም 32:41

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ናሆም 1:3
  • +ኢሳ 1:24፤ 59:18

ዘዳግም 32:43

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሕዝቡንም ምድር ያነጻል።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 12:2, 3፤ 1ነገ 8:43፤ ሮም 3:29፤ 15:10
  • +2ነገ 9:7፤ ራእይ 6:10
  • +ሚክ 5:15

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    2/1/1998፣ ገጽ 12, 17

    4/15/1991፣ ገጽ 12

ዘዳግም 32:44

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የኢያሱ ዋነኛው ስም ነው። ሆሺአ የሆሻያህ አጭር አጠራር ሲሆን “ያህ ያዳነው፤ ያህ አድኗል” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 11:28፤ ዘዳ 31:22, 23
  • +ራእይ 15:3

ዘዳግም 32:46

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 6:6, 7
  • +ዘዳ 11:18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    10/15/2001፣ ገጽ 19

ዘዳግም 32:47

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 18:5፤ ዘዳ 30:19፤ ሮም 10:5

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    2/2023፣ ገጽ 3

    መጠበቂያ ግንብ፣

    4/15/2008፣ ገጽ 5-6

ዘዳግም 32:49

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 27:12
  • +ዘዳ 34:1
  • +ዘፍ 10:19፤ 15:18፤ ኢያሱ 1:3

ዘዳግም 32:50

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ይህ ሞትን የሚያመለክት ቅኔያዊ አነጋገር ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 20:28፤ 33:38

ዘዳግም 32:51

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 20:12, 13
  • +ዘሌ 22:32፤ ኢሳ 8:13

ዘዳግም 32:52

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 27:13, 14፤ ዘዳ 3:27፤ 34:4, 5

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘዳ. 32:3ዮሐ 17:26
ዘዳ. 32:31ዜና 29:11፤ መዝ 145:3
ዘዳ. 32:42ሳሙ 22:31፤ መዝ 18:2፤ 19:7፤ ያዕ 1:17
ዘዳ. 32:4መዝ 33:5
ዘዳ. 32:4ዘዳ 25:16
ዘዳ. 32:4ዘዳ 7:9፤ 1ጴጥ 4:19
ዘዳ. 32:4ዘፍ 18:25
ዘዳ. 32:5ዘዳ 31:27፤ መሳ 2:19፤ መዝ 14:1
ዘዳ. 32:5ኢሳ 1:4
ዘዳ. 32:5መዝ 78:8፤ ሉቃስ 9:41
ዘዳ. 32:6ኤር 4:22
ዘዳ. 32:6ኢሳ 1:2
ዘዳ. 32:6ዘፀ 4:22፤ ዘዳ 32:18፤ ኢሳ 63:16
ዘዳ. 32:7ዘፀ 13:14፤ መዝ 44:1
ዘዳ. 32:8ዘፍ 10:5፤ መዝ 115:16
ዘዳ. 32:8ዘፍ 11:9
ዘዳ. 32:8ዘፍ 15:18፤ ዘፀ 23:31
ዘዳ. 32:8ዘዳ 2:5, 19፤ ሥራ 17:26
ዘዳ. 32:9ዘፀ 19:5፤ ዘዳ 7:6
ዘዳ. 32:9መዝ 78:71
ዘዳ. 32:10ዘዳ 8:14, 15
ዘዳ. 32:10ኤር 2:6
ዘዳ. 32:10ነህ 9:19, 20
ዘዳ. 32:10ዘካ 2:8
ዘዳ. 32:11ዘፀ 19:4
ዘዳ. 32:12ዘዳ 1:31
ዘዳ. 32:12ኢሳ 43:12
ዘዳ. 32:13ዘዳ 33:29
ዘዳ. 32:13ዘዳ 8:7, 8
ዘዳ. 32:14መዝ 147:14
ዘዳ. 32:15ዘዳ 31:20፤ ነህ 9:25
ዘዳ. 32:15ኢሳ 1:4፤ ሆሴዕ 13:6
ዘዳ. 32:16መሳ 2:12፤ 1ነገ 14:22፤ 1ቆሮ 10:21, 22
ዘዳ. 32:162ነገ 23:13፤ ሕዝ 8:17
ዘዳ. 32:17ዘሌ 17:7፤ መዝ 106:37፤ 1ቆሮ 10:20
ዘዳ. 32:18መዝ 106:21፤ ኢሳ 17:10፤ ኤር 2:32
ዘዳ. 32:18ዘዳ 4:34
ዘዳ. 32:19መሳ 2:14፤ መዝ 78:59
ዘዳ. 32:20ዘዳ 31:17
ዘዳ. 32:20ዘዳ 32:5፤ ኢሳ 65:2፤ ማቴ 17:17
ዘዳ. 32:20ኢሳ 1:2
ዘዳ. 32:21መዝ 96:5፤ 1ቆሮ 10:21, 22
ዘዳ. 32:211ሳሙ 12:10, 21
ዘዳ. 32:21ሆሴዕ 2:23፤ ሮም 9:25፤ 11:11፤ 1ጴጥ 2:10
ዘዳ. 32:21ሮም 10:19
ዘዳ. 32:22ሰቆ 4:11
ዘዳ. 32:22አሞጽ 9:2
ዘዳ. 32:24ዘዳ 28:53
ዘዳ. 32:24ዘዳ 28:21, 22
ዘዳ. 32:24ዘሌ 26:22
ዘዳ. 32:252ዜና 36:17፤ ሰቆ 2:21
ዘዳ. 32:25ሰቆ 1:20
ዘዳ. 32:25ሕዝ 7:15
ዘዳ. 32:271ሳሙ 12:22፤ ሕዝ 20:14
ዘዳ. 32:27ዘፀ 32:12፤ ዘኁ 14:15, 16
ዘዳ. 32:27መዝ 115:2
ዘዳ. 32:28ማቴ 13:15
ዘዳ. 32:29መዝ 81:13
ዘዳ. 32:29ሆሴዕ 14:9
ዘዳ. 32:29ኤር 2:19
ዘዳ. 32:30መሳ 2:14፤ 1ሳሙ 12:9
ዘዳ. 32:302ዜና 24:24
ዘዳ. 32:311ሳሙ 2:2
ዘዳ. 32:31ዘፀ 14:25፤ 1ሳሙ 4:8፤ ዕዝራ 1:2, 3
ዘዳ. 32:32ይሁዳ 7
ዘዳ. 32:32ኢሳ 5:4፤ ኤር 2:21
ዘዳ. 32:34ሮም 2:5
ዘዳ. 32:35ናሆም 1:2፤ ሮም 12:19፤ ዕብ 10:30
ዘዳ. 32:35መዝ 73:12, 18
ዘዳ. 32:36ዕብ 10:30
ዘዳ. 32:36መሳ 2:18፤ መዝ 90:13፤ 106:45፤ 135:14
ዘዳ. 32:37መሳ 10:14
ዘዳ. 32:38ሆሴዕ 2:8፤ 1ቆሮ 10:20, 21
ዘዳ. 32:39ኢሳ 41:4፤ 48:12
ዘዳ. 32:39ዘዳ 4:35
ዘዳ. 32:391ሳሙ 2:6፤ መዝ 68:20
ዘዳ. 32:392ዜና 21:16, 18
ዘዳ. 32:39ዘኁ 12:13፤ ኤር 17:14
ዘዳ. 32:39ኢሳ 43:13
ዘዳ. 32:401ጢሞ 1:17፤ ራእይ 10:5, 6
ዘዳ. 32:41ናሆም 1:3
ዘዳ. 32:41ኢሳ 1:24፤ 59:18
ዘዳ. 32:43ዘፍ 12:2, 3፤ 1ነገ 8:43፤ ሮም 3:29፤ 15:10
ዘዳ. 32:432ነገ 9:7፤ ራእይ 6:10
ዘዳ. 32:43ሚክ 5:15
ዘዳ. 32:44ዘኁ 11:28፤ ዘዳ 31:22, 23
ዘዳ. 32:44ራእይ 15:3
ዘዳ. 32:46ዘዳ 6:6, 7
ዘዳ. 32:46ዘዳ 11:18
ዘዳ. 32:47ዘሌ 18:5፤ ዘዳ 30:19፤ ሮም 10:5
ዘዳ. 32:49ዘኁ 27:12
ዘዳ. 32:49ዘዳ 34:1
ዘዳ. 32:49ዘፍ 10:19፤ 15:18፤ ኢያሱ 1:3
ዘዳ. 32:50ዘኁ 20:28፤ 33:38
ዘዳ. 32:51ዘኁ 20:12, 13
ዘዳ. 32:51ዘሌ 22:32፤ ኢሳ 8:13
ዘዳ. 32:52ዘኁ 27:13, 14፤ ዘዳ 3:27፤ 34:4, 5
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
  • 36
  • 37
  • 38
  • 39
  • 40
  • 41
  • 42
  • 43
  • 44
  • 45
  • 46
  • 47
  • 48
  • 49
  • 50
  • 51
  • 52
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘዳግም 32:1-52

ዘዳግም

32 “ሰማያት ሆይ፣ ጆሯችሁን ስጡኝ፤ እኔም እናገራለሁ፤

ምድርም የአፌን ቃል ትስማ።

 2 ትምህርቴ እንደ ዝናብ ይወርዳል፤

ካፊያ ሣር ላይ እንደሚወርድ፣

የሚያረሰርስ ዝናብም ተክልን እንደሚያጠጣ፣

ቃሌም እንደ ጤዛ ይንጠባጠባል።

 3 የይሖዋን ስም አውጃለሁና።+

ስለ አምላካችን ታላቅነት ተናገሩ!+

 4 እሱ ዓለት፣ የሚያደርገውም ነገር ሁሉ ፍጹም ነው፤+

መንገዶቹ ሁሉ ፍትሕ ናቸውና።+

እሱ ፈጽሞ ፍትሕን የማያጓድል+ ታማኝ+ አምላክ ነው፤

ጻድቅና ትክክለኛ ነው።+

 5 ምግባረ ብልሹ የሆኑት እነሱ ናቸው።+

ልጆቹ አይደሉም፤ ጉድለቱ የራሳቸው ነው።+

ጠማማና ወልጋዳ ትውልድ ናቸው!+

 6 እናንተ ሞኞችና ጥበብ የጎደላችሁ ሰዎች ሆይ፣+

በይሖዋ ላይ እንዲህ ያለ ነገር ታደርጋላችሁ?+

ወደ ሕልውና ያመጣህ አባትህ እሱ አይደለም?+

የሠራህና አጽንቶ ያቆመህስ እሱ አይደለም?

 7 የጥንቱን ዘመን አስታውስ፤

ያለፉት ትውልዶች የኖሩባቸውን ዓመታት መለስ ብለህ አስብ።

አባትህን ጠይቅ፤ ሊነግርህ ይችላል፤+

ሽማግሌዎችህንም ጠይቅ፤ ይነግሩሃል።

 8 ልዑሉ ለብሔራት ርስታቸውን ሲሰጥ፣+

የአዳምን ልጆች* አንዱን ከሌላው ሲለያይ፣+

በእስራኤል ልጆች ቁጥር ልክ+

የሕዝቦችን ወሰን ደነገገ።+

 9 የይሖዋ ሕዝብ ድርሻው ነው፤+

ያዕቆብ ርስቱ ነው።+

10 እሱን ምድረ በዳ በሆነ ምድር፣+

ነፋስ በሚያፏጭበት ጭው ያለ በረሃ አገኘው።+

ሊጠብቀውም ዙሪያውን ከበበው፤ ተንከባከበው፤+

እንደ ዓይኑም ብሌን ጠበቀው።+

11 ንስር ጎጆዋን እንደምትነቀንቅና

ከጫጩቶቿ በላይ እንደምታንዣብብ፣

ክንፎቿን ዘርግታ እንደምትይዛቸው፣

በላባዎቿም እንደምትሸከማቸው ሁሉ+

12 ይሖዋ ብቻውን መራው፤*+

ከእሱም ጋር ምንም ባዕድ አምላክ አልነበረም።+

13 በምድር ላይ በሚገኙ ከፍ ያሉ ቦታዎች እንዲሄድ አደረገው፤+

ስለሆነም የእርሻውን ምርት በላ።+

ከዓለት ማር አበላው፤

ከባልጩትም ዘይት መገበው፤

14 የላሞቹን ቅቤና የመንጋውን ወተት

ምርጥ ከሆነው በግ* ጋር ሰጠው፤

የባሳንን አውራ በጎችና አውራ ፍየሎች

ከምርጥ ስንዴ* ጋር ሰጠው፤+

አንተም ከወይን ፍሬው ደም* የወይን ጠጅ ጠጣህ።

15 የሹሩን* ሲወፍር በዓመፀኝነት ተራገጠ።

ሰባህ፤ ፈረጠምክ፤ ደለብክ።+

ስለሆነም የሠራውን አምላክ ተወ፤+

አዳኝ የሆነለትን ዓለት ናቀ።

16 በባዕዳን አማልክት አስቆጡት፤+

በአስጸያፊ ነገሮችም አሳዘኑት።+

17 ለአምላክ ሳይሆን ለአጋንንት፣+

ለማያውቋቸው አማልክት፣

በቅርቡ ለተነሱ ለአዲሶች፣

አባቶቻችሁ ለማያውቋቸው አማልክት ይሠዉ ነበር።

18 አባት የሆነህን ዓለት ረሳኸው፤+

የወለደህንም አምላክ አላስታወስክም።+

19 ይሖዋ ይህን ሲያይ ተዋቸው፤+

ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ አሳዝነውት ነበርና።

20 ስለዚህ እንዲህ አለ፦ ‘ፊቴን ከእነሱ እሰውራለሁ፤+

ምን እንደሚሆኑም አያለሁ።

ምክንያቱም እነሱ ጠማማ ትውልድ ናቸው፤+

ታማኝነት የሚባል ነገር የማያውቁ ልጆች ናቸው።+

21 እነሱ አምላክ ባልሆነው አስቆጡኝ፤+

ከንቱ በሆኑ ጣዖቶቻቸው አሳዘኑኝ።+

በመሆኑም እኔ ሕዝብ ባልሆነው አስቀናቸዋለሁ፤+

ሞኝ በሆነ ብሔር አበሳጫቸዋለሁ።+

22 ምክንያቱም ቁጣዬ እሳት አቀጣጥሏል፤+

እሱም እስከ መቃብር* ጥልቀት ድረስ ዘልቆ ይነድዳል፤+

ምድርንና ምርቷን ይበላል፤

የተራሮችንም መሠረት ያቃጥላል።

23 መከራቸውን አበዛዋለሁ፤

ቀስቶቼን በእነሱ ላይ እጨርሳለሁ።

24 በረሃብ ይዳከማሉ፤+

በሚያቃጥል ትኩሳትና በመራራ ጥፋት ይበላሉ።+

የአራዊትን ጥርስ፣

በምድር ላይ የሚሳቡ እንስሳትንም መርዝ እልክባቸዋለሁ።+

25 ወጣቱንም ሆነ ልጃገረዲቱን፣

ጨቅላውንም ሆነ ሽማግሌውን፣+

በውጭ፣ ሰይፍ ለሐዘን ይዳርጋቸዋል፤+

በቤት ውስጥ ደግሞ ሽብር አለ።+

26 እኔም “እበትናቸዋለሁ፤

መታሰቢያቸውም ከሰዎች ዘንድ እንዲጠፋ አደርጋለሁ” ባልኩ ነበር፤

27 ነገር ግን የጠላትን ምላሽ ፈራሁ፤+

ምክንያቱም ባላጋራዎቼ በተሳሳተ መንገድ ሊረዱት ይችላሉ።+

“ክንዳችን የበላይ ሆነ፤+

ይህን ሁሉ ያደረገው ይሖዋ አይደለም” ሊሉ ይችላሉ።

28 እነሱ ማመዛዘን የጎደለው* ብሔር ናቸው፤

በመካከላቸውም ማስተዋል የሚባል ነገር የለም።+

29 ምነው ጥበበኛ በሆኑ ኖሮ!+ ይህን ሁሉ ያሰላስሉ ነበር።+

የሚደርስባቸውንም ያስቡ ነበር።+

30 ዓለታቸው ካልሸጣቸውና+

ይሖዋ ለምርኮ ካልዳረጋቸው በስተቀር

አንድ ሰው 1,000 ሊያሳድድ፣

ሁለት ሰው ደግሞ 10,000 ሊያባርር እንዴት ይችላል?+

31 የእነሱ ዓለት እንደ እኛ ዓለት አይደለም፤+

ጠላቶቻችንም እንኳ ይህን ተረድተዋል።+

32 ወይናቸው ከሰዶም የወይን ተክልና

ከገሞራ የእርሻ ቦታ የተገኘ ነው።+

የወይን ፍሬያቸው መርዛማ የወይን ፍሬ ነው፤

ዘለላቸው መራራ ነው።+

33 የወይን ጠጃቸው የእባቦች መርዝ፣

የጉበናም* ምሕረት የለሽ መርዝ ነው።

34 ይህ እኔ ጋ ያለ፣

በግምጃ ቤቴ ውስጥ ማኅተም ታትሞበት የተቀመጠ አይደለም?+

35 በቀልም ሆነ ቅጣት የእኔ ነው፤+

አስቀድሞ የተወሰነው ጊዜ ሲደርስ እግራቸው ይከዳቸዋል፤+

የሚጠፉበት ቀን ቀርቧልና፤

የሚጠብቃቸውም ነገር በፍጥነት ይመጣል።’

36 ይሖዋ ሕዝቡን ይዳኛል፤+

አገልጋዮቹ አቅም እንዳነሳቸው፣

ረዳት የለሽና ደካማ የሆኑት ብቻ እንደቀሩ ሲያይ

ለእነሱ ያዝንላቸዋል።*+

37 ከዚያም እንዲህ ይላል፦ ‘አማልክታቸው የት አሉ?+

መሸሸጊያ እንዲሆናቸው የተጠጉት ዓለትስ የት አለ?

38 የመሥዋዕቶቻቸውን ስብ* ይበላ፣

የመጠጥ መባዎቻቸውንም የወይን ጠጅ ይጠጣ የነበረው የት አለ?+

እስቲ ተነስተው ይርዷችሁ።

እስቲ መሸሸጊያ ስፍራ ይሁኑላችሁ።

39 እንግዲህ እኔ እሱ እንደሆንኩ እዩ፤+

ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት የሉም።+

እኔ እገድላለሁ፤ እኔ ሕያው አደርጋለሁ።+

እኔ አቆስላለሁ፤+ እኔው እፈውሳለሁ፤+

ከእጄም ማዳን የሚችል የለም።+

40 እጄን ወደ ሰማይ አንስቼ፣

“በዘላለማዊ ሕያውነቴ” ብዬ እምላለሁ፤+

41 የሚያብረቀርቅ ሰይፌን ከሳልኩና

እጄን ለፍርድ ካዘጋጀሁ፣+

ተቃዋሚዎቼን እበቀላለሁ፤+

የሚጠሉኝንም እቀጣለሁ።

42 በታረዱና በተማረኩ ሰዎች ደም፣

በጠላት መሪዎች ራስ፣

ቀስቶቼን በደም አሰክራለሁ፤

ሰይፌም ሥጋ ይበላል።’

43 እናንተ ብሔራት ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ፤+

እሱ የአገልጋዮቹን ደም ይመልሳልና፤+

ተቃዋሚዎቹንም ይበቀላል፤+

ለሕዝቡም ምድር ያስተሰርይለታል።”*

44 ሙሴም ከነዌ ልጅ ከሆሺአ*+ ጋር መጥቶ የዚህን መዝሙር ቃላት በሙሉ ሕዝቡ እየሰማ ተናገረ።+ 45 ሙሴ እነዚህን ቃላት በሙሉ ለመላው እስራኤል ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ 46 እንዲህ አላቸው፦ “የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ በጥንቃቄ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዟቸው+ እኔ በዛሬው ዕለት እናንተን ለማስጠንቀቅ የምነግራችሁን ቃል ሁሉ ልብ በሉ።+ 47 ይህ ቃል ለእናንተ ሕይወታችሁ እንጂ እንዲሁ ባዶ ቃል አይደለም፤+ ይህ ቃል ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር ላይ ዕድሜያችሁን ሊያረዝምላችሁ ይችላል።”

48 ይሖዋ በዚያው ዕለት ሙሴን እንዲህ አለው፦ 49 “በኢያሪኮ ትይዩ በሞዓብ ምድር ወደሚገኘው ወደዚህ የአባሪም ተራራ+ ይኸውም ወደ ነቦ ተራራ+ ወጥተህ ለእስራኤላውያን ርስት አድርጌ የምሰጣትን የከነአንን ምድር ተመልከት።+ 50 ወንድምህ አሮን በሆር ተራራ ላይ ሞቶ+ ወደ ወገኖቹ እንደተሰበሰበ* ሁሉ አንተም በምትወጣበት በዚህ ተራራ ላይ ትሞታለህ፤ ወደ ወገኖችህም ትሰበሰባለህ፤ 51 ምክንያቱም ሁለታችሁም በጺን ምድረ በዳ በሚገኘው በቃዴስ፣ በመሪባ ውኃዎች+ አጠገብ በእስራኤላውያን መካከል ለእኔ ታማኝ ሆናችሁ አልተገኛችሁም፤ እንዲሁም በእስራኤል ሕዝብ ፊት እኔን አልቀደሳችሁኝም።+ 52 ምድሪቱን ከሩቅ ታያታለህ፤ ሆኖም ለእስራኤል ሕዝብ ወደምሰጣት ምድር አትገባም።”+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ