የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፀአት 17
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘፀአት የመጽሐፉ ይዘት

      • በኮሬብ ውኃ ባለማግኘታቸው አማረሩ (1-4)

      • ከዓለት ውኃ ፈለቀ (5-7)

      • ከአማሌቃውያን ጋር ተዋግተው አሸነፉ (8-16)

ዘፀአት 17:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 33:12
  • +ዘኁ 33:2
  • +ዘኁ 33:14

ዘፀአት 17:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 5:19, 21፤ ዘኁ 14:2, 3፤ 20:3
  • +ዘኁ 14:22፤ መዝ 78:18, 22፤ 106:14

ዘፀአት 17:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 16:2, 3

ዘፀአት 17:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 7:20

ዘፀአት 17:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 20:8፤ ዘዳ 8:14, 15፤ ነህ 9:15፤ መዝ 78:15፤ 105:41፤ 1ቆሮ 10:1, 4

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    7/2018፣ ገጽ 13-14

ዘፀአት 17:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ፈተና፤ ፈታኝ ሁኔታ” የሚል ትርጉም አለው።

  • *

    “ጠብ” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 6:16፤ መዝ 95:8, 9፤ ዕብ 3:8, 9
  • +ዘዳ 9:22
  • +መዝ 81:7

ዘፀአት 17:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 36:12
  • +ዘዳ 25:17፤ 1ሳሙ 15:2

ዘፀአት 17:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 11:28

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    12/1/2002፣ ገጽ 9-10

ዘፀአት 17:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 11:15
  • +ዘፀ 24:13, 14

ዘፀአት 17:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 11:12

ዘፀአት 17:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ማስታወሻ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 24:20፤ ዘዳ 25:19፤ 1ዜና 4:42, 43

ዘፀአት 17:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ይሖዋ አርማዬ ነው” የሚል ትርጉም አለው።

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፣ ርዕስ 125

ዘፀአት 17:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ራእይ 19:1
  • +1ሳሙ 15:20፤ አስ 9:24

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘፀ. 17:1ዘኁ 33:12
ዘፀ. 17:1ዘኁ 33:2
ዘፀ. 17:1ዘኁ 33:14
ዘፀ. 17:2ዘፀ 5:19, 21፤ ዘኁ 14:2, 3፤ 20:3
ዘፀ. 17:2ዘኁ 14:22፤ መዝ 78:18, 22፤ 106:14
ዘፀ. 17:3ዘፀ 16:2, 3
ዘፀ. 17:5ዘፀ 7:20
ዘፀ. 17:6ዘኁ 20:8፤ ዘዳ 8:14, 15፤ ነህ 9:15፤ መዝ 78:15፤ 105:41፤ 1ቆሮ 10:1, 4
ዘፀ. 17:7ዘዳ 6:16፤ መዝ 95:8, 9፤ ዕብ 3:8, 9
ዘፀ. 17:7ዘዳ 9:22
ዘፀ. 17:7መዝ 81:7
ዘፀ. 17:8ዘፍ 36:12
ዘፀ. 17:8ዘዳ 25:17፤ 1ሳሙ 15:2
ዘፀ. 17:9ዘኁ 11:28
ዘፀ. 17:10ኢያሱ 11:15
ዘፀ. 17:10ዘፀ 24:13, 14
ዘፀ. 17:13ኢያሱ 11:12
ዘፀ. 17:14ዘኁ 24:20፤ ዘዳ 25:19፤ 1ዜና 4:42, 43
ዘፀ. 17:16ራእይ 19:1
ዘፀ. 17:161ሳሙ 15:20፤ አስ 9:24
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘፀአት 17:1-16

ዘፀአት

17 መላው የእስራኤል ማኅበረሰብም ከሲን ምድረ በዳ+ ተነስቶ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት+ ከቦታ ወደ ቦታ ሲጓዝ ከቆየ በኋላ በረፊዲም+ ሰፈረ። ሆኖም ሕዝቡ የሚጠጣው ውኃ አልነበረም።

2 በመሆኑም ሕዝቡ “የሚጠጣ ውኃ ስጠን” በማለት ከሙሴ ጋር ይጣላ ጀመር።+ ሙሴ ግን “ከእኔ ጋር የምትጣሉት ለምንድን ነው? ይሖዋንስ ለምን ትፈታተኑታላችሁ?”+ አላቸው። 3 ሆኖም ሕዝቡ ውኃ በጣም ተጠምቶ ስለነበር “እኛና ልጆቻችን እንዲሁም ከብቶቻችን በውኃ ጥም እንድናልቅ ከግብፅ ያወጣኸን ለምንድን ነው?” በማለት በሙሴ ላይ ማጉረምረሙን ቀጠለ።+ 4 በመጨረሻም ሙሴ “ይህን ሕዝብ ምን ባደርገው ይሻለኛል? ትንሽ ቆይተው እኮ ይወግሩኛል!” በማለት ወደ ይሖዋ ጮኸ።

5 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከእስራኤል ሽማግሌዎች መካከል የተወሰኑትን ምረጥና የአባይን ወንዝ የመታህበትን በትር+ ይዘህ ከሕዝቡ ፊት ፊት ሂድ። በትሩን በእጅህ ይዘህ ሂድ። 6 እኔም በዚያ በኮሬብ በሚገኘው ዓለት ላይ ፊትህ እቆማለሁ። አንተም ዓለቱን ትመታዋለህ፤ ውኃም ከውስጡ ይፈልቃል፤ ሕዝቡም ይጠጣሉ።”+ ሙሴም የእስራኤል ሽማግሌዎች እያዩ እንደተባለው አደረገ። 7 እሱም እስራኤላውያን ስለተጣሉትና “ለመሆኑ ይሖዋ በመካከላችን አለ ወይስ የለም?” በማለት ይሖዋን ስለተፈታተኑት+ የቦታውን ስም ማሳህ*+ እና መሪባ*+ አለው።

8 ከዚያም አማሌቃውያን+ መጥተው በረፊዲም እስራኤላውያንን ወጉ።+ 9 በዚህ ጊዜ ሙሴ ኢያሱን+ እንዲህ አለው፦ “ሰዎች ምረጥልንና ከአማሌቃውያን ጋር ለመዋጋት ውጣ። እኔም በነገው ዕለት የእውነተኛውን አምላክ በትር በእጄ ይዤ በኮረብታው አናት ላይ እቆማለሁ።” 10 ከዚያም ኢያሱ ልክ ሙሴ እንዳለው አደረገ፤+ ከአማሌቃውያንም ጋር ተዋጋ። ሙሴ፣ አሮንና ሁርም+ ወደ ኮረብታው አናት ወጡ።

11 ሙሴ እጆቹን ወደ ላይ አንስቶ በሚቆይበት ጊዜ ሁሉ እስራኤላውያን ያይሉ፣ እጆቹን በሚያወርድበት ጊዜ ግን አማሌቃውያን ያይሉ ነበር። 12 የሙሴ እጆች በዛሉ ጊዜ ድንጋይ ወስደው ከሥሩ አስቀመጡለት፤ እሱም በድንጋዩ ላይ ተቀመጠ። ከዚያም አሮንና ሁር አንዱ በአንደኛው በኩል፣ ሌላው ደግሞ በሌላኛው በኩል ሆነው እጆቹን ደገፉለት፤ በመሆኑም ፀሐይ እስከምትጠልቅበት ጊዜ ድረስ እጆቹ ባሉበት ጸኑ። 13 በዚህ መንገድ ኢያሱ አማሌቅንና ሕዝቦቹን በሰይፍ ድል አደረገ።+

14 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “መታሰቢያ* እንዲሆን ይህን በመጽሐፍ ጻፈው፤ ለኢያሱም ‘የአማሌቅን መታሰቢያ ከሰማይ በታች ሙሉ በሙሉ ጠራርጌ አጠፋለሁ’+ በማለት ይህን ደግመህ ንገረው።” 15 ከዚያም ሙሴ መሠዊያ ሠርቶ ስሙን ‘ይሖዋ ንሲ’* ብሎ ሰየመው፤ 16 እንዲህም ያለው “እጁ በያህ+ ዙፋን ላይ ስለተነሳ ይሖዋ ከአማሌቅ ጋር ከትውልድ እስከ ትውልድ ይዋጋል”+ በማለት ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ