የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሚልክያስ 1
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ሚልክያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • ይሖዋ ለሕዝቡ ያለው ፍቅር (1-5)

      • እንከን ያለበት መሥዋዕት ያቀረቡ ካህናት (6-14)

        • የአምላክ ስም በብሔራት መካከል ታላቅ ይሆናል (11)

ሚልክያስ 1:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “መልእክተኛዬ” የሚል ትርጉም አለው።

ሚልክያስ 1:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 10:15
  • +ዘፍ 25:25, 26

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/1/2002፣ ገጽ 10

ሚልክያስ 1:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 9:13
  • +ኤር 49:20፤ ኢዩ 3:19
  • +ኢሳ 34:10, 13

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/1/2002፣ ገጽ 10-11

ሚልክያስ 1:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ዘፍ 25:30 እና ዘፍ 36:1 ላይ በተገለጸው መሠረት ኤዶም የኤሳው ሁለተኛ ስም ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 34:5፤ አብ 18

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ጥራዝ 15፣ ገጽ 17

ሚልክያስ 1:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ታላቅ ጌታስ።”

  • *

    ወይም “መከበሬ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 22:26
  • +ዘፀ 20:12
  • +ዘፀ 4:22
  • +ኢሳ 1:2

ሚልክያስ 1:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ዳቦ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 41:21, 22፤ 1ቆሮ 10:21

ሚልክያስ 1:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 22:20, 22፤ ዘዳ 15:21

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/1/2002፣ ገጽ 11-12

    11/15/2000፣ ገጽ 22

ሚልክያስ 1:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ኃላፊነት ወስዶ የቤተ መቅደሱን በሮች ለመዝጋት ፈቃደኛ መሆንን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 23:4
  • +ኤር 6:13፤ ሚክ 3:11
  • +ኢሳ 1:11፤ ኤር 6:20

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    12/15/2007፣ ገጽ 26-27

    5/1/2002፣ ገጽ 12

ሚልክያስ 1:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 113:3፤ ኢሳ 45:6፤ 59:19
  • +መዝ 22:27፤ ሶፎ 3:9፤ ማቴ 28:19፤ ራእይ 15:4

ሚልክያስ 1:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “እኔን ታረክሳላችሁ” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሕዝ 22:26፤ ሚል 1:7

ሚልክያስ 1:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 22:20, 22፤ ዘዳ 15:21፤ 17:1

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/1/2002፣ ገጽ 12-13

ሚልክያስ 1:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 47:2፤ ኤር 10:10
  • +ራእይ 15:4

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    5/1/2002፣ ገጽ 13

ተዛማጅ ሐሳብ

ሚል. 1:2ዘዳ 10:15
ሚል. 1:2ዘፍ 25:25, 26
ሚል. 1:3ሮም 9:13
ሚል. 1:3ኤር 49:20፤ ኢዩ 3:19
ሚል. 1:3ኢሳ 34:10, 13
ሚል. 1:4ኢሳ 34:5፤ አብ 18
ሚል. 1:6ሕዝ 22:26
ሚል. 1:6ዘፀ 20:12
ሚል. 1:6ዘፀ 4:22
ሚል. 1:6ኢሳ 1:2
ሚል. 1:7ሕዝ 41:21, 22፤ 1ቆሮ 10:21
ሚል. 1:8ዘሌ 22:20, 22፤ ዘዳ 15:21
ሚል. 1:102ዜና 23:4
ሚል. 1:10ኤር 6:13፤ ሚክ 3:11
ሚል. 1:10ኢሳ 1:11፤ ኤር 6:20
ሚል. 1:11መዝ 113:3፤ ኢሳ 45:6፤ 59:19
ሚል. 1:11መዝ 22:27፤ ሶፎ 3:9፤ ማቴ 28:19፤ ራእይ 15:4
ሚል. 1:12ሕዝ 22:26፤ ሚል 1:7
ሚል. 1:13ዘሌ 22:20, 22፤ ዘዳ 15:21፤ 17:1
ሚል. 1:14መዝ 47:2፤ ኤር 10:10
ሚል. 1:14ራእይ 15:4
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ሚልክያስ 1:1-14

ሚልክያስ

1 የፍርድ መልእክት፦

በሚልክያስ* በኩል ለእስራኤል የተነገረው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦

2 “እኔ ፍቅር አሳይቻችኋለሁ”+ ይላል ይሖዋ።

እናንተ ግን “ፍቅር ያሳየኸን እንዴት ነው?” አላችሁ።

“ኤሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረም?”+ ይላል ይሖዋ። “እኔ ግን ያዕቆብን ወደድኩ፤ 3 ኤሳውንም ጠላሁ፤+ ተራሮቹን ባድማ አደረግኩ፤+ ርስቱንም ለምድረ በዳ ቀበሮዎች ሰጠሁ።”+

4 “ኤዶም* ‘ተደምስሰናል፤ ሆኖም ተመልሰን የፈራረሱትን ዳግመኛ እንገነባለን’ ቢልም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሱ ይገነባሉ፤ እኔ ግን አፈርሳለሁ፤ ቦታዎቹ “የክፋት ምድር፣” እነሱ ደግሞ “ይሖዋ ለዘላለም ያወገዘው ሕዝብ” ተብለው ይጠራሉ።+ 5 የገዛ ዓይናችሁ ይህን ያያል፤ እናንተም “ይሖዋ በእስራኤል ምድር ከፍ ከፍ ይበል” ትላላችሁ።’”

6 “እናንተ ስሜን የምታቃልሉ ካህናት ሆይ፣+ ‘ልጅ አባቱን፣ አገልጋይም ጌታውን ያከብራል።+ እኔ አባት ከሆንኩ+ ለእኔ የሚገባው ክብር የት አለ?+ ጌታስ* ከሆንኩ መፈራቴ* የት አለ?’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።

“‘እናንተ ግን “ስምህን ያቃለልነው እንዴት ነው?” ትላላችሁ።’

7 “‘በመሠዊያዬ ላይ የረከሰ ምግብ* በማቅረብ ነው።’

“‘ደግሞም “ያረከስንህ እንዴት ነው?” ትላላችሁ።’

“‘“የይሖዋ ገበታ+ የተናቀ ነው” በማለታችሁ ነው። 8 ዕውሩን እንስሳ መሥዋዕት አድርጋችሁ ስታቀርቡ “ምንም ችግር የለውም” ትላላችሁ። ደግሞም አንካሳ ወይም የታመመ እንስሳ ስታቀርቡ “ምንም ችግር የለውም” ትላላችሁ።’”+

“እነዚህን እንስሳት እስቲ ለገዢህ ለማቅረብ ሞክር። በአንተ ደስ ይለዋል? ወይስ በሞገስ ዓይን ይቀበልሃል?” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።

9 “አሁንም እባካችሁ፣ ሞገስ እንዲያሳየን አምላክን ተማጸኑ። እንዲህ ያሉ መባዎች በገዛ እጃችሁ ስታቀርቡ ከእናንተ መካከል የእሱን ሞገስ የሚያገኝ ይኖራል?” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።

10 “ከእናንተ መካከል በሮቹን ለመዝጋት ፈቃደኛ የሚሆን ማን ነው?*+ በመሠዊያዬ ላይ እሳት ለማንደድ እንኳ ክፍያ ትጠይቃላችሁና።+ በእናንተ ፈጽሞ ደስ አልሰኝም” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ “ስጦታ አድርጋችሁ በምታቀርቡት በየትኛውም መባ አልደሰትም።”+

11 “ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ* ድረስ ስሜ በብሔራት መካከል ታላቅ ይሆናል።+ በየቦታው ለስሜ የሚጨስ መሥዋዕትና መባ ተቀባይነት ያለው ስጦታ ሆኖ ይቀርባል፤ ምክንያቱም ስሜ በብሔራት መካከል ታላቅ ይሆናል”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።

12 “እናንተ ግን ‘የይሖዋ ገበታ የረከሰ ነው፤ ፍሬው ይኸውም ምግቡ የተናቀ ነው’ በማለት ታረክሱታላችሁ።*+ 13 በተጨማሪም እናንተ ‘እንዴት አድካሚ ነው!’ ትላላችሁ፤ ደግሞም ትጸየፉታላችሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። “የተሰረቀን፣ አንካሳውንና የታመመውን እንስሳ ታመጣላችሁ። አዎ፣ እንዲህ ያሉ ነገሮችን ስጦታ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ! ታዲያ ይህን ከእጃችሁ ልቀበል ይገባል?”+ ይላል ይሖዋ።

14 “በመንጎቹ መካከል ተባዕት እንስሳ እያለው፣ ስእለት ተስሎ እንከን ያለበትን ለይሖዋ መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብ የሚያታልል የተረገመ ነው። እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ “ስሜም በብሔራት መካከል የተፈራ ይሆናል።”+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ