የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g99 1/8 ገጽ 3
  • ኤድስ ወረርሽኙ አሁንም አልተገታም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኤድስ ወረርሽኙ አሁንም አልተገታም
  • ንቁ!—1999
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኤድስ ለወደፊቱስ ምን ተስፋ አለ?
    ንቁ!—1999
  • ኤድስ የያዛቸውን ሰዎች መርዳት
    ንቁ!—1995
  • “በሰው ዘር ታሪክ ታይቶ የማያውቅ ቸነፈር”
    ንቁ!—2002
  • ኤድስን እንዴት መከላከል ይቻላል?
    ንቁ!—1999
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—1999
g99 1/8 ገጽ 3

ኤድስ ወረርሽኙ አሁንም አልተገታም

ካረን ያደገችው በምዕራባዊ ዩናይትድ ስቴትስ ነው።a የይሖዋ ምሥክር እንደመሆኗ መጠን በወጣትነት ዕድሜዋ በሙሉ ከፍተኛ የሥነ ምግባር ደንቦችን አክብራ ኖራለች። በ1984 ሃያ ሦስት ዓመት እንደሞላት የይሖዋ ምሥክር ከሆነ ገና ሁለት ዓመት የሆነውን ቢልን አገባች። አንድ ወንድና አንዲት ሴት ልጅ ወለዱ።

በ1991 ፍቅራቸው ሥር ከመስደዱም በላይ ትዳራቸው እርካታና ደስታ የሰፈነበት ሆኖ ነበር። ይሁን እንጂ በዚያው ዓመት መገባደጃ ላይ በቢል ምላስ ላይ ሊጠፋ ያልቻለ ነጭ ነገር መታየት ጀመረ። ወደ ሐኪም ቤት ሄደ።

ከዚህ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ካረንና ልጆችዋ ግቢያቸው ውስጥ የወደቁትን ቅጠላ ቅጠሎች ይጠራርጉ ነበር። ቢል ወደ ቤታቸው በረንዳ በሚያስወጣው ደረጃ ላይ ተቀምጦ ካረን መጥታ ከአጠገቡ እንድትቀመጥ ጠራት። ወገቧን እቅፍ አደረገና ዓይኑ እንባ እያቀረረ እንደሚወዳትና ለዘላለም አብሯት ለመኖር እንደሚፈልግ ነገራት። ታዲያ ምን አስለቀሰው? ቢል ኤድስ አምጪ በሆነው ቫይረስ ማለትም በኤች አይ ቪ እንደተለከፈ ሐኪሙ ጠርጥሯል።

ቤተሰቡ ተመረመረ። ቢልና ካረን በቫይረሱ እንደተለከፉ ታወቀ። ቢል የተለከፈው የይሖዋ ምሥክር ከመሆኑ በፊት ሲሆን እርሱም ቫይረሱን ወደ ካረን አስተላልፏል። ልጆቹ በበሽታው እንዳልተለከፉ ምርመራው አረጋገጠ። በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ቢል ሞተ። ካረን እንዲህ ትላለች:- “በአንድ ወቅት ቆንጆ ቁመና የነበረው፣ የምትወዱትና አብራችሁት ለዘላለም እንደምትኖሩ ተስፋ ያደረጋችሁት ሰው ቀስ በቀስ እየመነመነ ሄዶ አጥንትና ቆዳ ሲሆን ማየት የሚያሳድረውን ስሜት እንዴት መግለጽ እንደሚቻል አላውቅም። ብዙ ጊዜ ሌሊቱን በሙሉ አልቅሻለሁ። አሥረኛ የጋብቻ ቀናችንን ልናከብር ሦስት ወር ሲቀረን ሞተ። በጣም ጥሩ አባትና ጥሩ ባል ነበር።”

ካረን ብዙ ሳትቆይ ባልዋን እንደምትከተል ዶክተር ቢነግራትም አሁንም በሕይወት አለች። ኢንፌክሽኑ ወደ መጀመሪያው የኤድስ ደረጃ ደርሷል።

ካረን በአሁኑ ጊዜ በኤች አይ ቪ/ኤድስ ከተመረዙት 30 ሚልዮን ሰዎች መካከል አንዷ ብቻ ናት። የአውስትራሊያ፣ የአየርላንድና የፓራጉዋይ ሕዝቦች አንድ ላይ ቢደመሩ እንኳን እዚህ አኃዝ ላይ አይደርሱም። ከእነዚህ በኤች አይ ቪ ሰለባ ከሆኑት ሰዎች መካከል 21 ሚልዮን የሚያክሉት የሚኖሩት በአፍሪካ እንደሆነ አንዳንድ ግምቶች ይጠቁማሉ። በአዲሱ ምዕተ ዓመት መባቻ ላይ ይህ ቁጥር ወደ 40 ሚልዮን ሊያሻቅብ እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት ይገምታል። አንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዘገባ እንደሚለው ይህ በሽታ በታሪክ ዘመናት ከታዩት ትላልቅ ወረርሽኞች የሚመደብ ነው። በዓለም ዙሪያ ከ15 እስከ 49 ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙ 100 ሰዎች መካከል አንዱ በኤች አይ ቪ የተለከፈ ነው። ከእነዚህ መካከል መለከፋቸውን የሚያውቁት ከአሥሩ አንዱ ብቻ ናቸው። በአንዳንድ የአፍሪካ ክፍሎች አካለ መጠን ከደረሱ ሰዎች መካከል 25 በመቶ የሚሆኑት በበሽታው ተለክፈዋል።

የኤድስ ወረርሽኝ ከጀመረበት ከ1981 ወዲህ 11.7 ሚልዮን የሚያክሉ ሰዎች በዚህ በሽታ እንደሞቱ ይገመታል። በ1997 ብቻ 2.3 ሚልዮን የሚያክሉ ሰዎች እንደተቀጠፉ ይገመታል። ይሁን እንጂ ከኤድስ ጋር በሚደረገው ውጊያ አዲስ የተስፋ ጭላንጭል መታየት ጀምሯል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት በበለጸጉት አገሮች በኤድስ የሚለከፉ አዳዲስ ሰዎች ቁጥር ቀንሷል። በተጨማሪም ጤንነት እንደሚያሻሽሉና ዕድሜ እንደሚያራዝሙ ተስፋ የተደረገባቸው አዳዲስ መድኃኒቶች ተገኝተዋል።

ራስህን ከኤድስ እንዴት ልትጠብቅ ትችላለህ? በሕክምናና በክትባት ረገድ የተደረሰባቸው ምን አዳዲስ ግኝቶች አሉ? በሽታው ድል የሚደረግበት ጊዜ ይመጣ ይሆን? በሚቀጥሉት ርዕሶች ውስጥ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a ስሞቹ ተለውጠዋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ