የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • gf ትምህርት 14 ገጽ 22-23
  • የአምላክ ወዳጆች መጥፎ ከሆነ ነገር ይርቃሉ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአምላክ ወዳጆች መጥፎ ከሆነ ነገር ይርቃሉ
  • የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክ የሚጠላቸው ድርጊቶች
    አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?
  • አምላክን ለማስደሰት ምን ማድረግ ይኖርብናል?
    አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ
  • ክፍል 13
    አምላክን ስማ
  • “ለመውደድ ጊዜ አለው፤ ለመጥላትም ጊዜ አለው”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
ለተጨማሪ መረጃ
የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
gf ትምህርት 14 ገጽ 22-23

ትምህርት 14

የአምላክ ወዳጆች መጥፎ ከሆነ ነገር ይርቃሉ

ሰይጣን ሰዎች መጥፎ ነገሮችን እንዲያደርጉ ይፈትናቸዋል። የአምላክ ወዳጅ ለመሆን የሚፈልግ ሰው ይሖዋ የሚጠላቸውን መጥላት ይኖርበታል። (መዝሙር 97:10) የአምላክ ወዳጆች ሊርቋቸው ከሚገቧቸው ተግባሮች መካከል አንዳንዶቹ የሚከተሉት ናቸው:-

ይሖዋ ከሚጠላቸው ነገሮች መካከል የፆታ ብልግና፣ ስካር፣ ጽንስ ማስወረድ፣ ስርቆት፣ ውሸት፣ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ቁጣ እና ቁማር

የፆታ ብልግና። “አታመንዝር።” (ዘጸአት 20:14) ከጋብቻ በፊት የፆታ ግንኙነት መፈጸምም ስህተት ነው።—1 ቆሮንቶስ 6:18

ስካር። “ሰካሮች . . . የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።”—1 ቆሮንቶስ 6:10

መግደል፣ ጽንስ ማስወረድ። “አትግደል።”—ዘጸአት 20:13

ስርቆት። “አትስረቅ።”—ዘጸአት 20:15

ውሸት። ይሖዋ “ሐሰተኛ ምላስ” ይጠላል።—ምሳሌ 6:17

የኃይል ድርጊትና ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ቁጣ። “ዓመፃን የወደዳት ግን” ይሖዋ ይጠላዋል። (መዝሙር 11:5) ‘ከሥጋ ሥራዎች አንዱ ቁጣ ነው።’—ገላትያ 5:19, 20

ቁማር። “ከሚስገበገቡ . . . ጋር አትተባበሩ።”—1 ቆሮንቶስ 5:11 የ1980 ትርጉም

የዘርና የጎሳ ጥላቻ። “ጠላቶቻችሁን ውደዱ . . . ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ።”—ማቴዎስ 5:43, 44

አምላክ የሚነግረን የሚጠቅመንን ነገር ብቻ ነው። መጥፎ ከሆኑ ነገሮች መቆጠብ ሁልጊዜ ቀላል አይደለም። ከይሖዋና ከምሥክሮቹ በምታገኘው እርዳታ አምላክ የማይደሰትባቸውን ነገሮች ከማድረግ ልትቆጠብ ትችላለህ።—ኢሳይያስ 48:17፤ ፊልጵስዩስ 4:13፤ ዕብራውያን 10:24, 25

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ