የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/96 ገጽ 2
  • የነሐሴ የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የነሐሴ የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ነሐሴ 5 የሚጀምር ሳምንት
  • ነሐሴ 12 የሚጀምር ሳምንት
  • ነሐሴ 19 የሚጀምር ሳምንት
  • ነሐሴ 26 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
km 8/96 ገጽ 2

የነሐሴ የአገልግሎት ስብሰባዎች

ነሐሴ 5 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 215

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የተመረጡ ማስታወቂያዎች።

20 ደቂቃ፦ “ምሥራቹን ያለማሰለስ ማወጅ።” ንግግርና ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት። ቅዱሳን ጽሑፎችን ጠለቅ ብሎ ማስተዋል በተባለው መጽሐፍ ጥራዝ 2፣ ገጽ 673፣ አንቀጽ 1 ላይ ያለውን ሐሳብ ጨምረህ አቅርብ።

15 ደቂቃ፦ “በብሮሹሮች ተጠቅማችሁ የመንግሥቱን ምሥራች አውጁ።” (አንቀጽ 1-5) የመጀመሪያውን አንቀጽ አንድ መግቢያ አድርገህ ተጠቀም። በደስታ ኑር! የተሰኘውን ብሮሹር በአገልግሎት መጠቀም ያለውን ጠቀሜታ በተመለከተ አዎንታዊ የሆኑ ሐሳቦችን ተናገር። እነዚህን ብሮሹሮች በመጠቀም ውይይት መጀመርና ተመላልሶ መጠየቅ ማድረግ የሚቻለው እንዴት እንደሆነ የሚያሳዩ በደንብ ታስቦባቸው የተዘጋጁ አራት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። አንድ ወጣት በደስታ ኑር! የተሰኘውን ብሮሹር በመጠቀም ከወላጆቹ ጋር ሆኖ አቀራረቡን በሠርቶ ማሳያ መልክ እንዲያቀርብ አድርግ። አስፋፊዎች እዚህ ላይ ያሉትን አቀራረቦች በመከተል ለሌሎች ብሮሹሮች የራሳቸውን መግቢያ ማዘጋጀት ይፈልጉ ይሆናል።

መዝሙር 136 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 12 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 191

15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። ታኅሣሥ 1, 1993 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 29-31 ድረስ ያለውን “የምንካፈልባቸው መንገዶች” በሚለው ርዕስ ላይ አዎንታዊ የሆኑ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።

15 ደቂቃ፦ “በብሮሹሮች ተጠቅማችሁ የመንግሥቱን ምሥራች አውጁ።” (አንቀጽ 6-8) መንግሥት የተሰኘውን ብሮሹር ጠቅላላ ይዘት ምን እንደሆነ አጠር ባለ መልኩ ግለጽ። ለመጀመሪያ ጊዜ ውይይት ሲደረግና ተመላልሶ መጠየቅ ሲደረግ የሚያሳይ በተሰጡት አቀራረቦች በሠርቶ ማሳያ አቅርብ። ሁሉም ላበረከቱላቸው ሰዎች ክትትል እንዲያደርጉ አበረታታቸው።

15 ደቂቃ፦ ጉባኤው በመስክ አገልግሎት ረገድ የሚያስፈልጉት ነገሮች። ጥር 15, 1991 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 10-20 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ መሠረት በማድረግ ከቤት ወደ ቤት የሚደረገውን አገልግሎት ከቆላስይስ 4:5 ጋር በሚስማማ መልኩ የመንገድ ላይ ምሥክርነት መስጠትን ጨምረህ ማቅረብ ትችላለህ። “ለአጋጣሚዎች ንቁ ሁኑ” የሚለውን (በሐምሌ 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 3) ላይ የወጣውን ትምህርት ልትከልስ ትችላለህ። በዚህ ትምህርት ላይ ውጤታማ ሊሆኑ የሚችሉ ሌሎች ሁኔታዎችንም ልታክል ትችላለህ። ሁሉም መጽሐፍ ቅዱስንና የሚበረከቱ ጽሑፎችን እንዲጠቀሙ አበረታታቸው።

መዝሙር 19 እና የመደምደሚያ ጸሎት

ነሐሴ 19 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 174

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የጥያቄ ሣጥኑን ከልስ።

15 ደቂቃ፦ “ለመስበክ ብቁ የሆነው ማን ነው?” አንድ ሽማግሌ ከሁለት ወይም ከሦስት አስፋፊዎች ጋር ይወያያል። የአምላክ አገልጋዮች እንድንሆን የሚያስታጥቀንን ከሁሉ የተሻለ ሥልጠና እንዳገኘን ጠበቅ አድርገህ ግለጽ። ለመስበክ ብቃቱ የለኝም የምንልበት ምንም ምክንያት የለም።

20 ደቂቃ፦ “እውቀት በተባለው መጽሐፍ አማካኝነት ደቀ መዛሙርት ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?” የሰኔ 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ሆኖ በወጣው ርዕስ ከአንቀጽ 17-26 ላይ የተመሠረተ ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት። በጉባኤው ውስጥ እውቀት በተባለው መጽሐፍ ጥናት ከሚመሩ የተገኙ ተሞክሮዎችን ቀደም ብለህ አዘጋጅ። አባሪ ሆኖ በወጣው ክፍል ላይ የተጠቀሱትን ምክሮች እንዴት እንደተጠቀሙና የበለጠ እድገት የሚያሳዩ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለመምራት እንዴት እንደረዳቸው አዎንታዊ የሆኑ ማብራሪያዎችን ሊሰጡ ይችላሉ። ሁሉም አባሪ የሆነውን ጽሑፍ ቅርብ ቦታ እንዲያስቀምጡትና አዲስ ጥናት ሲያገኙ በግል እንዲከልሱት አበረታታቸው።

መዝሙር 175 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 26 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 85

15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በመስከረም የሚበረከቱት ዘላለም መኖር እና ቤተሰብ የተሰኙት መጽሐፎች እንደሆኑ ግለጽ። ሁሉም አስፋፊዎች እነዚህን መጽሐፎች አመቺ በሆኑ አጋጣሚዎች ሁሉ በግለት የማበርከት ግብ እንዲያወጡ አበረታታ። በመንግሥት አገልግሎታችን ታኅሣሥ 1995 ገጽ 10 እና ጥር 1996 ገጽ 4 አንቀጽ 2 ላይ የወጡትን ሐሳቦች ከልሳቸው።

15 ደቂቃ፦ ለልጆቻችሁ ትምህርት ትኩረት ስጡ። በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ትምህርት ቤትና የይሖዋ ምሥክሮች ከተሰኘው ብሮሹር ገጽ 3 ላይ ያለውን ሐሳብ በመከለስ በትምህርት ቤት ውስጥ የሚሰጡት ጠቃሚ ሥልጠናዎች በአድናቆት የምንመለከትበት ምክንያት ምን እንደሆነ ግለጽ። ዓለማዊ ሥራዎችን ከማስቀደም ይልቅ መንፈሳዊ ግቦችን የምንከታተለው ለምን እንደሆነ ለአስተማሪዎች በዘዴ እንዴት መግለጽ እንደሚቻል አብራራ። በገጽ 24 ላይ “ከትምህርት ቤቱ ሥርዓት ጋር መተባበር” ከሚለው የመደምደሚያ ሐሳብ ውስጥ የተወሰዱ ተጨማሪ ነጥቦችን ጨምረህ አቅርብ። በመስከረም 8, 1988 የእንግሊዝኛ ንቁ! ገጽ 11 ላይ የተሰጡትን ሐሳቦች ወላጆች እንዲጠቀሙባቸው አበረታታ።

15 ደቂቃ፦ “‘የአምላካዊ ሰላም መልእክተኞች’ የ1996 የአውራጃ ስብሰባ።” ከ1-9 ያሉትን አንቀጾች በጥያቄና መልስ መሸፈን።

መዝሙር 113 እና የመደምደሚያ ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ