የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/97 ገጽ 12
  • በጥድፊያ ስሜት ምስራቹን ማቅረብ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በጥድፊያ ስሜት ምስራቹን ማቅረብ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እንዴት ብለህ ትመልሳለህ?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • እንዲያስተውሉ እርዷቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • ለመስክ አገልግሎት የሚሆኑ መግቢያዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
  • የራእይ መጽሐፍ የእውነተኛ ደስታ ቁልፍ ነው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
km 2/97 ገጽ 12

በጥድፊያ ስሜት ምስራቹን ማቅረብ

 1 በክርስቲያናዊ አገልግሎት በሙሉ ልብ ስንካፈል በአምላክ መንግሥት ተስፋዎች ላይ ጥልቅ አድናቆት እንዳለን እናሳያለን። በዚህ ሥራ ላይ በጥድፊያ ስሜት መካፈል ይኖርብናል። ለምን? ሠራተኞቹ ጥቂቶች በመሆናቸው፣ የዚህ ክፉ ሥርዓት ፍፃሜ በጣም በመቅረቡና በአገልግሎት ክልላችን ውስጥ ያሉት ሰዎች ሕይወት አደጋ ላይ በመውደቁ ምክንያት ነው። (ሕዝ. 3:​19፤ ማቴ. 9:​37, 38) እንዲህ ያለው ከባድ ኃላፊነት በአገልግሎቱ ላይ በሙሉ ኃይላችን እንድንካፈል ይጠይቅብናል። የመስክ አገልግሎት እንቅስቃሴያችንን በተመለከተ የጥድፊያ ስሜት ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? ቀደም ብለን ጥሩ መግቢያ በማዘጋጀት፣ በሚኖሩበት ቦታ ሁሉ ሰዎችን ፈልገን ለማግኘት ትጉህ በመሆን፣ ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ስም በማስታወሻችን ላይ በትክክል አስፍረን ይህ ፍላጎታቸው ሳይቀዘቅዝ ወዲያው ተመላልሶ መጠየቅ በማድረግና ሕይወትን የሚመለከት ጉዳይ መሆኑን በማስታወስ አገልግሎታችንን በቁም ነገር መያዝ ይኖርብናል። በየካቲት ምሥራቹን በጥድፊያ ስሜት ለማቅረብ በምንዘጋጅበት ጊዜ ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡት ሐሳቦች ጠቃሚ ሆነው ልናገኛቸው እንችላለን። የምናበረክተው ጽሑፍ ራእይ —ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! የተሰኘው መጽሐፍ ይሆናል።

 2 በኅብረተሰቡ ፊት ስለተደቀኑ አንዳንድ ችግሮች በአጭሩ በመጥቀስ ውይይት መጀመር ትችል ይሆናል። ከዚያም እንዲህ ለማለት ትችላለህ:-

◼ “ብዙ ሰዎች አምላክ እንዳለ ያምናሉ። ይሁን እንጂ ‘ወደፊት ምን ዓይነት ሕይወት እንድንኖር ይፈልጋል?’ እያሉ ይጠይቃሉ። ይህን ጥያቄ ምን ብለው ይመልሳሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] አምላክ ለሰው ልጆች ያለውን ፈቃድና ይህንንም ፈቃዱን ዳር ለማድረስ ደረጃ በደረጃ ምን እያከናወነ እንዳለ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እንደሚናገር ያውቃሉ?” የራእይ መደምደሚያ የተሰኘውን መጽሐፍ ገጽ 301 ላይ አውጣ። አንቀጽ 1 ላይ ያለውን ራእይ 21:​1ን ካነበብክ በኋላ ለዚህ ጥቅስ የተሰጠውን ከአንቀጽ 2 አጋማሽ ጀምሮ ያለውን ማብራሪያ አንብብ። የወደፊቱ ጊዜ ምን እንደያዘልን ለማብራራት ገጽ 302 ላይ ያለውን ስዕል አውጣ። አንቀጽ 6 ላይ ያለውን ራእይ 21:​4ን አንብብ። መጽሐፉን አበርክት። ተመልሰህ ሄደህ ውይይታችሁን ለመቀጠል እንድትችሉ አመቺ ቀጠሮ ያዝ።

 3 ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርግ በዚህ አጭር መግቢያ ተጠቅመህ በራእይ 21:​1, 4 ላይ ያደረጋችሁትን ውይይት መቀጠል ትችላለህ:-

◼ “ባለፈው ጊዜ አምላክ ለሰው ዘር አዲስ ምድራዊ ኅብረተሰብ ለማቋቋም ዓላማ እንዳለው ተወያይተን ነበር። [የራእይ መደምደሚያ ከተሰኘው መጽሐፍ ገጽ 302 ላይ ባለው ስዕል እንደገና ትኩረት አድርግ።] ቤተሰብዎ እንዲህ በመሰለ አስደሳች ሁኔታ ውስጥ ሲኖር ማየት ይፈልጋሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ቀጥሎ የሚነሳው ጥያቄ አምላክ የገባው ተስፋ ተአማኒነቱ ምን ያህል ነው? የሚለው ነው። አምላክ ራሱ ምን ብሎ እንደተናገረ ልብ ይበሉ።” ገጽ 303 አንቀጽ 8 ላይ ያለውን ራእይ 21:​5, 6ሀን አንብብ። ገጽ 304 ላይ ያለውን የአንቀጽ 9ን ጥያቄ ጠይቅና የአንቀጹን የመጨረሻ አረፍተ ነገር አክለህ የጥያቄውን መልስ አንብብ። መጽሐፍ ቅዱስን በነፃ እንዲያጠኑ ጋብዝ። ጥናቱ እንዴት እንደሚከናወን በሌላ ጊዜ ለማሳየት ቀጠሮ ያዝ።

 4 በሰው ዘሮች ላይ እየጨመረ የሚሄደው ችግር ብዙዎቹን ስለሚያሳስባቸው ሰዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ ስታነጋግር ይህን የመሰለ ነገር መናገር ትችላለህ:-

◼ “አብዛኞቹ ያነጋገርኳቸው ሰዎች ኅብረተሰቡን ያጋጠሙት ችግሮች ያሳስባቸዋል። [ጥቂቶቹን ችግሮች ጥቀስ።] እነዚህ ሁኔታዎች እየተባባሱ እንዲሄዱ የሚያደርገው ምን ይመስልዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ሰዎች ከዚህ ቀደም አስበውበት የማያውቁትን ማብራሪያ ይሰጣል። የራእይ መጽሐፍ በሰማይ ተደርጎ ስለነበረ ጦርነት ይገልጻል። በራእይ 12:​9 ላይ እንደተገለጸው ይህ ያስከተለው ውጤት ምን እንደሆነ ልብ ይበሉ።” ጥቅሱን አንብብና የራእይ መደምደሚያ የተሰኘውን መጽሐፍ ገጽ 182 አውጣ። ሰይጣን በምድር ጉዳዮች ላይ ስለሚያሳድረው ተጽዕኖ ለማብራራት በስዕሉ ተጠቀም። መጽሐፉን አበርክትና ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርግ አምላክ በሰው ልጆች ላይ የደረሱትን ችግሮች የሚያስወግደው እንዴት እንደሆነ ለመወያየት ዝግጅት አድርግ።

 5 በአሁኑ ጊዜ ያሉት ችግሮች የሚወገዱት እንዴት እንደሆነ ለማብራራት ተመልሰህ እንደምትመጣ ቃል ገብተህ ከሆነ ይህን አቀራረብ ልትጠቀም ትችላለህ:-

◼ “በሰው ዘሮች ላይ የተደቀኑት ችግሮች እውነተኛ መፍትሄአቸው ምን እንደሆነ ለመወያየት እንድንችል ተመልሼ ለመምጣት ከፍተኛ ጥረት አድርጌአለሁ። ዓለሙን ሁሉ የሚያስተው ሰይጣን ዲያብሎስ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ለይቶ እንደሚያሳውቅ ባለፈው ጊዜ ተመልክተን ነበር። እርሱ ከሰው የበለጠ ኃይል ያለው ፍጡር እንደመሆኑ መጠን የሚያሳድራቸው ተፅዕኖዎች ሙሉ በሙሉ ሊወገዱ የሚችሉበት መንገድ ይኖራል ብለው ያስባሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] አስቲ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ልብ ይበሉ።” ራእይ 20:​1-3ን አንብብና አብራራ። እውቀት በተሰኘው መጽሐፍ ገጽ 4-5 ላይ ባለው ስዕል ተጠቅመህ የሰይጣን ተፅዕኖ በሚወገድበት ጊዜ ሁኔታዎች ምን እንደሚመስሉ አሳይ። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያጠና ጋብዘውና ጥናቱንም ወዲያው ለመጀመር ጥረት አድርግ።

 6 ብዙ ሰዎች የአካባቢ ሁኔታዎች ስለሚያሳስባቸው ውይይት ለመክፈት ይህን የመሰለ ነገር መናገር ትችላለህ:-

◼ “ቁጥራቸው እየጨመረ የሚሄድ ብዙ ሰዎች የአየር፣ የውኃና የምግብ ብክለት እንደሚያሳስባቸው ተረድተናል። እንዲያውም በአንዳንድ አገሮች ያለው የአካባቢ ሁኔታ ለሕይወት አደገኛ ወደመሆን ደረጃ ደርሷል። አምላክ የምድር ፈጣሪ እንደመሆኑ መጠን ስለዚህ ጉዳይ ምን ያደርጋል ብለው ያስባሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] አምላክ በምድር አጠቃቀማችን ላይ ፍርድ እንደሚሰጥ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። [ራእይ 11:​18ን አንብብ።] ከብክለት ነፃ በሆነ ምድር ላይ ኑሮ ምን ሊመስል እንደሚችል እስቲ ለአንድ አፍታ ያስቡ!” በራእይ 21:​3, 4 ላይ የሚገኘው አምላክ ገነትን አስመልክቶ የሰጠውን ተስፋ አብራራ። የራእይ መደምደሚያ በተሰኘው መጽሐፍ በገጽ 302 ላይ የሚገኘውን ስዕል አሳይ። ከዚያም መጽሐፉን አበርክትና ለተመላልሶ መጠየቅ ዝግጅት አድርግ።

 7 ገነት ስለምትሆነው ምድር ፍላጎት ካደረበት ሰው ጋር ውይይት ለማድረግ ተመልሰህ በምትሄድበት ጊዜ እንዲህ ልትል ትችላለህ:-

◼ “ባለፈው ጊዜ ባደረግነው ውይይት በምድር ላይ የተከሰተውን የብክለት ችግር ለማስወገድ አምላክ በሰው ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ መግባት እንደሚኖርበት ተስማምተን ነበር። ይሁን እንጂ ጥያቄው በሕይወት ተርፈን አምላክ ወዳዘጋጀው ጽድቅ የሰፈነበት አዲስ ዓለም ለመግባት ምን ማድረግ አለብን? የሚል ነው።” ዮሐንስ 17:​3ን አንብብ። የቤቱ ባለቤት ይህንን ልዩ የሆነ እውቀት ለማግኘት በነፃ ከምንሰጠው የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲጠቀም ጋብዘው።

 8 በዘመናችን እየተከናወነ ባለው የመከር ሥራና ሕይወት አድን በሆነው የስብከት ሥራ ተካፋይ መሆን እንዴት ያለ ውድ መብት ነው! ሁላችንም ‘ድካማችን በጌታ ዘንድ ከንቱ እንደማ​ይሆን አውቀን’ ምሥራቹን በጥድፊያ ስሜት በማቅረብ በሥራ የተጠመድን እንሁን።— 1 ቆ⁠ሮ. 15:​58

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ