የኅዳር የአገልግሎት ስብሰባዎች
ኅዳር 3 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 3 (6)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። የአገሪቱንና የጉባኤውን የነሐሴ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርት በሚመለከት ሐሳብ ስጥ።
15 ደቂቃ፦ “ሥራ የሞላበት ትልቅ በር ተከፍቷል።” በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግርና ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት። አቅማቸውና ሁኔታቸው የሚፈቅድላቸው ሁሉ በስብከቱ ሥራ የሚያደርጉትን ተሳትፎ እንዲያሳድጉ አበረታታ። በነሐሴ 15, 1988 መጠበቂያ ግንብ (የእንግሊዝኛ) በገጽ 22 ላይ ያለውን ምክር ጨምረህ አቅርብ።
20 ደቂቃ፦ “የመንግሥት ዜና ተበርክቶላቸው ፍላጎት ያሳዩትን ተከታትላችሁ እርዱ።” ጥያቄና መልስ። በአንቀጽ 6 ላይ ያሉትን አቀራረቦች በሠርቶ ማሳያ አቅርብ። በአንደኛው ሠርቶ ማሳያ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሲጀመር አሳይ።
መዝሙር 61 (144) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ኅዳር 10 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 97 (217)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። በመንግሥት ዜና ቁ. 35 ገና መሸፈን ያለበት ክልል የትኛው እንደሆነ ለጉባኤው አሳውቅ። በዚህ የልዩ ዘመቻ የመጨረሻ ሳምንት ሁሉም ሙሉ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አበረታታ።
15 ደቂቃ፦ “መጽሔት ለማበርከት የሚያስችል አቀራረብ መዘጋጀት የሚቻልበት መንገድ።” ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ።
20 ደቂቃ፦ “የይሖዋ ምሥክር ያልሆኑ የትዳር ጓደኞችን መርዳት።” አማኝ ያልሆኑ የትዳር ጓደኞችን በይበልጥ በግለሰብ ደረጃ የማወቅ አስፈላጊነት ባሳሰባቸው ሁለት ሽማግሌዎች በውይይት የሚቀርብ። ከዚህም በተጨማሪ በመጠበቂያ ግንብ 10-110 በገጽ 17-18 ከአንቀጽ 6-9 ላይ በተሰጡት ሐሳቦች ይወያያሉ። ከጥቅምት 1, 1995 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 10-11 ከአንቀጽ 11-12 ላይ ያሉትን ተሞክሮዎች ጨምራችሁ አቅርቡ።
መዝሙር 63 (148) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ኅዳር 17 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 25 (53)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ኅዳር 27 ልዩ የመስክ አገልግሎት ስምሪት ዝግጅት መኖሩን ግለጽ። የመንግሥት ዜና ቁ. 35ን በማበርከቱ ዘመቻ ከጉባኤው የተገኙ አንዳንድ ተሞክሮዎች ተናገር።
20 ደቂቃ፦ “ይህ ተወዳዳሪ የማይገኝለት አጋጣሚ አያምልጥህ!” በኅዳር 15, 1996 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 21-3 ላይ የተመሰረተ ንግግር።
15 ደቂቃ፦ “ምንድን ነው የምለው?” ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። በማመራመር መጽሐፍ ገጽ 8 ላይ ያለውን የመጀመሪያ አንቀጽ በማንበብ መጽሐፉ በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ርዕሶች ላይ ውጤታማ የሆነ ምሥክርነት መስጠት እንድንችል እኛን ለመርዳት ታስቦ እንዴት እንደተዘጋጀ ግለጽ። ይህን ለማሳየት ጥሩ ዝግጅት የተደረገበት አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያ አቅርብ።
መዝሙር 64 (151) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ኅዳር 24 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 26 (56)
8 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ በጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት ወቅት ጥሩ ሥነ ምግባር ማሳየት። የመጽሐፍ ጥናት እንድናደርግበት ቤታቸውን የፈቀዱልን ቤተሰቦች የሚያሳዩትን የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ እናደንቃለን። ይህ ሁኔታ አንዳንድ ዝግጅት ማድረግ ሊጠይቅባቸው የሚችል ከመሆኑም በላይ በተወሰነ ደረጃ መሥዋዕትነት መክፈል ሊያስፈልጋቸው ይችላል። በጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት ስብሰባ ላይ ስንገኝ ጥሩ ሥነ ምግባርና አክብሮት እንዲሁም አሳቢነት ማሳየት ይገባናል፤ ይህም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ነገሮች ያጠቃልላል:- (1) ወለሉን ወይም ምንጣፉን ላለማቆሸሽ ቤት ውስጥ ከመግባታችን በፊት ጫማችንን ጥሩ አድርገን መጥረግ ይኖርብናል። (2) ወላጆች ልጆቻቸው ሥርዓታማ እንዲሆኑና የመጽሐፍ ጥናቱ ከሚካሄድበት ክፍል ውጪ እየሄዱ ችግር እንዳይፈጥሩ መቆጣጠር አለባቸው። (3) ምንም እንኳ በቡድን ትንሽ ሆነን የምንሰበሰብ ቢሆንና ዘና ያለ መንፈስ ቢኖርም የመጽሐፍ ጥናት የጉባኤ ስብሰባ እንደመሆኑ መጠን የመንግሥት አዳራሽ በምንሄድበት ጊዜ የምንለብሰው ዓይነት አለባበስ መልበስ ይኖርብናል። (4) ቤተሰቡ በግል የሚያሳልፈው ጊዜ እንዲኖረው ከስብሰባው በኋላ የምናደርገው ጭውውት አጭር መሆን አለበት። (5) ምንም እንኳ ጥናቱ የሚካሄድበት ቤት ባለቤት አልፎ አልፎ ከጥናቱ በኋላ ቀለል ያለ ምግብና መጠጥ ሊያቀርብ ቢችልም ይህ ነገር የሚጠበቅበት ወይም ግዴታው አለመሆኑን ሁሉም ሰው ማወቅ አለበት።
22 ደቂቃ፦ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው። አንድ ሽማግሌ ከሦስት ወይም ከአራት አስፋፊዎች ጋር በቡድን ሆኖ በውይይት ያቀርበዋል። አገልግሎታችን በተባለው መጽሐፍ ላይ ከገጽ 88-92 ላይ ባሉት ሐሳቦች ተመርኩዘው ቀጥሎ ያሉትን ጥያቄዎች ይመልሳሉ:- (1) ውጤታማ የሆነ አገልግሎት ለማከናወን ተመላልሶ መጠየቅ ማድረግ የግድ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ተፈታታኝ የሆነውን ተመላልሶ መጠየቅ የማድረግ ሥራ እንዴት መወጣት ይቻላል? (2) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች የማስጀመሩን ሥራ ከፍተኛ ትኩረት የምንሰጠው ለምንድን ነው? ጥናት በመምራት በኩል ጥሩ ችሎታ ማዳበር የምንችለው እንዴት ነው? (3) የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎችን ወደ ድርጅቱ መምራት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ይህንንስ እንዴት ማድረግ እንችላለን? በተጨማሪም አስፋፊዎቹ በቅርቡ በሰኔ 1996 እንዲሁም በመጋቢትና በሚያዝያ 1997 የመንግሥት አገልግሎታችን የወጡት አባሪ ገጾች በዚህ ረገድ እንዴት እንደረዷቸው ይገልጻሉ።
መዝሙር 69 (160) እና የመደምደሚያ ጸሎት።