የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 6/99 ገጽ 4
  • ጊዜያችሁን በአግባቡ ተጠቀሙበት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጊዜያችሁን በአግባቡ ተጠቀሙበት
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
  • በአገልግሎት የምታሳልፉትን ጊዜ በተሻለ መንገድ ተጠቀሙበት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2015
  • በአገልግሎታችሁ ውጤታማ ሁኑ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
  • ውጤታማ የሆነ የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2015
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
km 6/99 ገጽ 4

ጊዜያችሁን በአግባቡ ተጠቀሙበት

1 ሁሉም ሰው በሳምንት ውስጥ ያለው ጊዜ እኩል ነው። በተለይ ምሥራቹን በማስፋፋት የምናሳልፈው ጊዜ ሕይወት አድን ለሆነ ሥራ የሚውል ስለሆነ ከፍ ያለ ግምት ይሰጠዋል። (ሮሜ 1:16) ለወጣው የአገልግሎት ፕሮግራም ጥሩ ዝግጅት በማድረግ፣ ለመስክ ስምሪት ስብሰባ በሰዓቱ በመገኘትና እንዳለቀ ወዲያውኑ ወደ ክልላችን በመሄድ ለዚህ ጊዜ ያለንን አድናቆት እናሳያለን። ወዲያው በስብከቱ ሥራ እንጠመዳለን እንጂ ጊዜ አናጠፋም። ይሖዋ ‘ለሁሉም ጊዜ እንዳለው’ ስላስተማረን ለአገልግሎቱ የመደብነውን ጊዜ በአግባቡ ልንጠቀምበት ያስፈልጋል።—መክ. 3:1 የ1980 ትርጉም

2 ጊዜያችሁን በጥበብ ማደራጀት፦ ዘወትር በመስክ አገልግሎት ተሳትፎ ለማድረግ የሚያስችለንን ፕሮግራም አውጥተን ያንን በጥብቅ የምንከተል ከሆነ ብዙ በረከቶች እናገኛለን። በአገልግሎት የምናገኛቸው ጥሩ ውጤቶች በዚህ ሥራ ከምናሳልፈው ጊዜ ጋር የሚመጣጠኑ መሆን እንዳለባቸው ጥርጥር የለውም። በተለመደው ፕሮግራማችን ላይ ጥቂት ማስተካከያዎችን በማድረግ የበለጠ ጊዜ ለመስክ አገልግሎት ማዋል እንችል ይሆን? ለምሳሌ ያህል ቅዳሜ መጽሔት ስናበረክት ከቆየን በኋላ ጥቂት ተመላልሶ መጠይቆችን ለማድረግ ተጨማሪ ጊዜ መመደብ እንችል ይሆን? እሁድ ቀን በመስክ አገልግሎት ተሰማርተን ጥቂት ካገለገልን በኋላ ተመላልሶ መጠይቅ በማድረግና ጥናት በመምራት ደግሞ የተወሰነ ጊዜ ማሳለፍ እንችላለን? በእነዚህ ወይም በሌሎች መንገዶች በአገልግሎታችን መሻሻል ማድረግ እንችል ይሆናል።

3 የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች በሰዓቱ መጀመራቸውና ማለቃቸው ጠቃሚ ነው። እንዲመራ የተመደበው ሰው በዚህ ረገድ ቁም ነገረኛ ሆኖ መገኘት ይኖርበታል። እሱ የሚያረፍድ ወይም መምጣት የማይችል ከሆነ እንዲረዳው የተመደበው ሰው ፕሮግራሙን መቀጠል ይኖርበታል። ምንም ጊዜ እንዳይባክን ሲባል የሚመራው ወንድም ሁልጊዜ የተዘጋጀ ክልል ሊኖረው ይገባል። ከጸሎትና ከአገልግሎት ምደባ በኋላ ወዲያ ወዲህ ከማለት ይልቅ ወዲያውኑ አገልግሎት መጀመሩ ከሁሉ የተሻለ ነው።

4 ጥንቃቄ ካላደረግን አገልግሎት ከወጣን በኋላ ውድ የሆነውን ጊዜያችንን ልናባክን እንችላለን። እርግጥ መጥፎ የአየር ሁኔታ ሲኖር አጭር እረፍት መውሰዱ ተነቃቅተን እንድንቀጥል ያደርገናል። ነገር ግን እነዚህ ዕረፍቶች ሁልጊዜ ላያስፈልጉ ስለሚችሉ ሚዛናዊ ሁኑ።

5 ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሰዎችን በቤታቸው ማግኘቱ አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል። ብዙ አስፋፊዎች ይህን ሁኔታ ለመቋቋም ከቤት ወደ ቤት የሚያደርጉትን ምሥክርነት በቀኑ ውስጥ ሌላ አመቺ ሰዓት መርጠው ያከናውናሉ። ከሰዓት በኋላ ወይም አመሻሹ ላይ ለመመሥከር ለምን አትሞክሩም?

6 በመንገድ ላይ ምሥክርነት ተሰማርተን እያለን እርስ በርሳችን በሌላ ወሬ ባንጠመድ የተሻለ ነው። ከዚህ ይልቅ አንዳችሁ ከሌላው ፈንጠር ብላችሁ በመቆም ሰዎችን አነጋግሩ። እንዲህ ከሆነ ጊዜውን ውጤታማ በሆነ መንገድ ልትጠቀሙበትና ከሥራውም የበለጠ ደስታ ልታገኙ ትችላላችሁ።

7 ለመመስከር የሚያስችሉ አጋጣሚዎችን ተጠቀሙባቸው፦ አንዲት ምሥክር በር የከፈተችላት ሴት ፍላጎት እንደሌላት በገለጸችላት ጊዜ በቤት ውስጥ ልታነጋግረው የምትችለው ሌላ ሰው ይኖር እንደሆነ ጠየቀቻት። ይህም ለብዙ ዓመታት ታምሞ ከነበረውና አብዛኛውን ጊዜውን ተኝቶ ከሚያሳልፈው የቤቱ ባለቤት ጋር ውይይት እንድትጀምር አስቻላት። በአምላክ ቃል ላይ ሰፍሮ የሚገኘው ተስፋ ለሕይወት ያለውን ፍላጎት አደሰለት። ብዙም ሳይቆይ ከአልጋው ተነስቶ በመንግሥት አዳራሽ በሚደረጉት ስብሰባዎች ላይ መገኘትና አዲስ ያገኘውን ተስፋ ለሌሎች ማካፈል ጀመረ!

8 በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የምትገኝ አንዲት እህት ከጉባዔ የመጽሐፍ ጥናት በፊት ባለው ሰዓት በአገልግሎት ስለመሠማራት የተሰጠውን ሐሳብ በሥራ ላይ አዋለች። የመጀመሪያውን በር ስታንኳኳ ያገኘቻት የ13ዓመት ልጃገረድ በጥሞና አዳምጣት ጽሑፍ ወሰደች። በሚቀጥለው ቀን ትምህርት ቤት ውስጥ ይህችኑ ልጅ አገኘቻት። ወዲያውኑ መጽሐፍ ቅዱስን እንድታጠና ጋበዘቻት፤ ልጅቷም ግብዣውን ተቀበለች።

9 በአገልግሎት የምታሳልፉትን ጊዜ በተሻለ መንገድ ተጠቀሙበት፦ በመስክ አገልግሎት ዘወትር መካፈላችን ምሥራቹን የማቅረብ ችሎታችን እያደገ እንዲሄድ ይረዳናል። የበለጠ ውጤታማ መግቢያ በመጠቀም ከቤት ወደ ቤት ውይይት የማስጀመር ችሎታችሁን ማሻሻል ትችላላችሁ? ‘የተተከለውን ለማጠጣት’ እና መጀመሪያ ምሥክርነት በሰጣችሁበት ወቅት ያገኛችሁትን ውጤት ጠላት መጥቶ እንዲነጥቀው ላለመፍቀድ ስትሉ ፍላጎት ያሳዩትን በጥሩ ሁኔታ በማስታወሻ በመያዝና ወዲያውኑ ተመልሳችሁ በመጠየቅ በኩል ንቁ ለመሆን ጥረት ማድረግ ትችላላችሁ? የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ስትመሩ ጥሩ ችሎታ ያለው አስተማሪ መሆን ትችሉ ይሆን? እንዲህ በማድረግ በአገልግሎት የምታሳልፉትን ጊዜ በአግባቡ ልትጠቀሙበትና አገልግሎታችሁን የበለጠ ፍሬያማ ልታደርጉት ትችላላችሁ።—1 ጢሞ. 4:16

10 የቀረው ‘ዘመን አጭር ስለሆነ’ ሕይወታችን በክርስቲያናዊ ሥራዎች የተሞላ መሆን አለበት። (1 ቆሮ. 7:29) ለስብከቱ ሥራ ጊዜ መመደብ ቅድሚያ ከምንሰጣቸው ነገሮች መካከል የመጀመሪያውን ቦታ ሊይዝ ይገባዋል። በአገልግሎቱ ጤናማ እና ቅንዓት የሞላበት ተሳትፎ እናድርግ። ጊዜ ይሖዋ የሰጠን አስደናቂ ሃብት ነው። ሁልጊዜ በጥበብና በአግባብ ተጠቀሙበት።

[በገጽ 1 ላይ የሚገኝ ሥዕል4]

እነዚህን ነጥቦች አስቡባቸው፦

◼ ለአገልግሎት ስምሪት ስብሰባ በሰዓቱ ድረሱ።

◼ የአገልግሎት ቡድኖቹን እንደ ሁኔታው ትናንሽ አድርጓቸው።

◼ ወደ አገልግሎት ክልሉ ለመግባት ጊዜ አታጥፉ።

◼ የአገልግሎት ክልሉን ብዙ ሰዎች በቤታቸው በሚገኙበት ጊዜ አንኳኩ።

◼ ምንም ችግር የማያስከትል ከሆነ አንዳንድ ጊዜ ብቻችሁን ሥሩ።

◼ ከቤት ወደ ቤት በምታገለግሉበት አካባቢ ላሉና ቀደም ሲል ፍላጎት ላሳዩ ሰዎች ተመላልሶ መጠይቅ አድርጉ።

◼ በቡድኑ ውስጥ ያሉ ሌሎች አንድ ቤት በር ላይ ሰው እያነጋገሩ ከዘገዩ እናንተ በአገልግሎት ቀጥሉ።

◼ የሚቻል ሲሆን እንደ ሁኔታው በአገልግሎት ከአንድ ሰዓት በላይ ቆዩ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ