የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/09 ገጽ 7-8
  • የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ውጤታማ የሆነ የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2015
  • ከመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች የተሟላ ጥቅም ማግኘት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
  • ከመስክ አገልግሎት ስምሪት ቡድናችሁ ጥቅም ማግኘት የምትችሉት እንዴት ነው?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
  • የጥያቄ ሣጥን
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
km 8/09 ገጽ 7-8

የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች

1. የመስክ አገልግሎታችን በተደራጀ መልኩ የመከናወኑ ጉዳይ የሚያሳስበን ለምንድን ነው?

1 ኢየሱስ የመንግሥቱን የስብከት ሥራ በተደራጀና ውጤታማ በሆነ መንገድ በማከናወን ረገድ ግሩም ምሳሌ ትቷል። በዛሬው ጊዜም ዓለም አቀፉን የስብከት ሥራ የመምራት ኃላፊነት ያለባቸው ወንድሞች ሥራው በተመሳሳይ መንገድ እንዲከናወን የማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ጉባኤዎች ከዚህ ጋር በሚስማማ መልኩ የመንግሥቱ ሰባኪ ቡድኖች አገልግሎታቸውን በተደራጀ መልክ እንዲያከናውኑ ለመርዳት የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎችን ይጠቀማሉ።—ማቴ. 24:45-47፤ 25:21፤ ሉቃስ 10:1-7

2. የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች እንዴት ሊከናወኑ ይገባል?

2 ግሩም የሆነ ዝግጅት፦ የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች የተዘጋጁት ወደ መስክ አገልግሎት ለሚወጡ አስፋፊዎች ማበረታቻና ተግባራዊ መመሪያ ለመስጠት ነው። የዕለት ጥቅሱ በመስክ አገልግሎት ላይ ልንጠቀምባቸው የምንችላቸውን ሐሳቦች ከያዘ በዚያ ላይ አጠር ያለ ውይይት ማድረግ ይቻላል። በስብሰባው ላይ የተገኙትን ሁሉ ለዕለቱ ሥራ ለማዘጋጀት አንዳንድ ጊዜ በመንግሥት አገልግሎታችን እንዲሁም በማመራመር መጽሐፍ ምናልባትም በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ላይ የሚገኙ ሐሳቦችን አንስቶ መወያየት ይቻላል። በተጨማሪም በወሩ የሚበረከተውን ጽሑፍ በተመለከተ አጠር ያለ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ ማድረግ ይቻላል። ስብሰባው በጸሎት ከመደምደሙ በፊት በዚያ የተገኙት ሁሉ ከማን ጋር እንደተመደቡና የትኛውን ክልል እንደሚሠሩ ሊያውቁ ይገባል። ከ15 ደቂቃ የማይበልጥ ጊዜ የሚወስደው ይህ ስብሰባ እንደተጠናቀቀ ሁሉም ወደየክልላቸው መሄድ ይኖርባቸዋል።

3. የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎችን የማደራጀት ኃላፊነት ያለባቸው እነማን ናቸው?

3 ስብሰባዎቹ እንዴት ሊደራጁ ይገባል? የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎችን በዋነኝነት የማቀናጀት ኃላፊነት ያለበት የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ነው። የቡድን የበላይ ተመልካቾች ወይም ረዳቶቻቸው ቅዳሜና እሁድ ቡድኖቻቸውን ወደ አገልግሎት ይዞ የመውጣት ኃላፊነት አለባቸው። አንዳንድ የበላይ ተመልካቾች አሊያም የጉባኤ አገልጋዮች ቡድናቸውን አገልግሎት ይዘው ለመውጣት የአዘቦቱን ቀናት መጠቀም ይችሉ ይሆናል። የቡድን የበላይ ተመልካቾች ቡድኖቻቸው ቅዳሜና እሁድ ከቤት ወደ ቤት ማገልገል እንዲችሉና በቂ ክልል እንዲኖራቸው ለማድረግ ከአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ጋር ተባብረው መሥራት ይኖርባቸዋል። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በአዘቦቱ ቀናት የመስክ አገልግሎት ስብሰባውን የሚመሩ ወንድሞች የሚመድብ ከመሆኑም ሌላ የስምሪት ስብሰባው ዝግጅት በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ይቆጣጠራል።

4-6. (ሀ) የጉባኤ ክልሎችን አጣርቶ መሸፈን እንዲቻል የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎችን በምን መልኩ ማደራጀት ያስፈልጋል? (ለ) የመስክ ስምሪት ስብሰባዎች የትና መቼ መደረግ እንዳለባቸው ለመወሰን ምን ነገሮችን ከግምት ማስገባት ይቻላል?

4 ስብሰባዎቹ መካሄድ ያለባቸው የትና መቼ ነው? የጉባኤው የስምሪት ስብሰባ በአንድ ቦታ ላይ ብቻ ከሚካሄድ ይልቅ ክልሎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመሸፈን እንዲቻል የስምሪት ስብሰባዎች አመቺ በሆኑ ቦታዎች (ብዙውን ጊዜ ወንድሞች ቤት ቢሆን ይመረጣል) ተሰበጣጥረው ቢደረጉ የተሻለ ነው። የመንግሥት አዳራሾችንም ለዚህ ዓላማ መጠቀም ይቻላል። በርካታ ጉባኤዎች እሁድ የሚያደርጉትን የሕዝብ ንግግር እና የመጠበቂያ ግንብ ጥናት እንዳጠናቀቁ የመስክ ስምሪት ስብሰባቸውን ለማድረግ የመንግሥት አዳራሹን ይጠቀማሉ። በተቻለ መጠን የስምሪት ስብሰባ የሚደረግበት ቦታና የአገልግሎት ክልሉ የተራራቁ እንዳይሆኑ ማድረጉ የተሻለ ነው። በመሆኑም አሁን ያሉት የስምሪት ስብሰባ የሚካሄድባቸው ቦታዎች ክልሎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ አጣርቶ ለመሸፈን የሚያስችሉ መሆን አለመሆናቸው በየተወሰነ ጊዜ መገምገም ይቻላል።

5 ስብሰባዎቹን ለማድረግ ከሁሉ የተሻለው ሰዓት የቱ እንደሆነና በሳምንት ውስጥ ምን ያህል ጊዜ መደረግ እንዳለባቸው የመወሰኑ ጉዳይ በክልሉ ሁኔታ ላይ የተመካ ነው። የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች የትና መቼ መደረግ እንዳለባቸው ለመወሰን የሚከተሉት ጥያቄዎች እንደ መመሪያ ሆነው ሊያገለግሉ ይችላሉ።

6 ከክልሎቻችሁ ውስጥ ይበልጥ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው የትኛው ነው? ከቤት ወደ ቤት ለማገልገል ከሁሉ የተሻለው ጊዜ የትኛው ነው? ከቤት ወደ ቤት ለማገልገል ወይም ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ የምሽቱን ጊዜ መጠቀም ያስፈልግ ይሆን? የስምሪት ስብሰባን በተመለከተ የተደረገው ማንኛውም ዝግጅት በጉባኤው የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መለጠፍ አለበት። የመንግሥቱ አስፋፊዎች የሆንን ሁላችን ልክ እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ እኛም “ያልሰበክሁበት ክልል የለም” ብለን መናገር እንድንችል የተሰጠንን ክልል በሚገባ መሸፈን እንፈልጋለን።—ሮም 15:23

7. የስምሪት ስብሰባውን የሚመራው ወንድም ምን ኃላፊነት አለበት?

7 የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎችን መምራት፦ ይህን ስብሰባ እንዲመራ የተመደበው ወንድም ጥሩ አድርጎ በመዘጋጀት ለዚህ ቲኦክራሲያዊ ዝግጅት ጥልቅ አክብሮት እንዳለው ማሳየት ይችላል። እነዚህ ስብሰባዎች በሰዓታቸው መጀመር ያለባቸው ሲሆን ትምህርት ሰጪና ከ10 እስከ 15 ደቂቃ ባለው ጊዜ ውስጥ በአጭሩ የሚቀርቡ ሊሆኑ ይገባል። ስብሰባውን የሚመራው ወንድም ለቡድኑ የሚሰጠው ክልል አስቀድሞ ሊኖረው ይገባል። የስምሪት ስብሰባው ካለቀ በኋላ የሚመጡ አስፋፊዎችን መጠበቁ አስፈላጊ ባይሆንም ቡድኑ የሚያገለግለው በየትኛው ክልል ውስጥ እንደሆነ መልእክት መተው ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። ሁሉም አስፋፊዎች ስብሰባው እንዳለቀ ጊዜ ሳያጠፉ ወደተመደቡበት ክልል መሄድ አለባቸው። የመስክ ስምሪት ስብሰባው በሚገባ የተደራጀና ትምህርት ሰጪ ከሆነ በዚያ የተገኙት በሙሉ በዕለቱ ለሚያከናውኑት አገልግሎት አስፈላጊውን መመሪያ እንደሚያገኙ ምንም ጥርጥር የለውም።—ምሳሌ 11:14

8. በመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ ላይ የሚገኙ አስፋፊዎች ስብሰባውን ከሚመራው ወንድም ጋር መተባበር የሚችሉት በምን መንገዶች ነው?

8 በመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ ላይ መገኘት፦ የትብብር መንፈስ ማሳየት አስፈላጊ ነው። (ዕብ. 13:17) የሚቻል ከሆነ ቡድኑን የሚያደራጀው ወንድም አስፋፊዎች አብረውት ማገልገል ከሚፈልጉት ወንድም ወይም እህት ጋር እንዲመደቡ ሊያደርግ ይችላል። ተሞክሮ ያካበቱ አስፋፊዎች በስብሰባው ላይ መገኘታቸው አዲሶችንና ልምድ የሌላቸውን አስፋፊዎች ለመርዳት ያስችላል። አልፎ አልፎ ከተለያዩ ሰዎች ጋር ለማገልገል ፈቃደኛ የሆኑ አስፋፊዎች ብዙ ጠቃሚ ነገር ማከናወን ይችሉ ይሆናል። (ምሳሌ 27:17፤ ሮም 15:1, 2) ሁሉም በሰዓቱ ለመገኘት የጋራ ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል። ለዚህ ቲኦክራሲያዊ ዝግጅት ያለን አክብሮትና ለእምነት ባልደረቦቻችን ያለን አሳቢነት በዚህ ረገድ አስፈላጊውን ማስተካከያ እንድናደርግ ያነሳሳናል።—2 ቆሮ. 6:3, 4፤ ፊልጵ. 2:4

9. አቅኚዎች ይህን ዝግጅት ሊደግፉ የሚችሉባቸው አንዳንድ ጠቃሚ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

9 አቅኚዎች የሚሰጡት ድጋፍ፦ አቅኚዎች የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎችን መደገፋቸው ጠቃሚ ከመሆኑም ሌላ ሁሉንም የሚያበረታታ ነው። አቅኚዎች ብዙ ኃላፊነት እንዳለባቸው ግልጽ ነው። አቅኚዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ከመምራትና ተመላልሶ መጠየቅ ከማድረግ ባሻገር ቤተሰባቸውን የመንከባከብና ሰብዓዊ ሥራ የመሥራት ኃላፊነት ሊኖርባቸው ይችላል። በዚህም ምክንያት በተለይ ጉባኤው የስምሪት ስብሰባውን የሚያደርገው በየዕለቱ ከሆነ አቅኚዎች በሁሉም ስብሰባዎች ላይ የመገኘት ግዴታ እንዳለባቸው ሊሰማቸው አይገባም። ይሁንና አቅኚዎች በሳምንት ውስጥ በሚደረጉት በተወሰኑት ስብሰባዎች ላይ በመገኘት ድጋፍ መስጠት ይችሉ ይሆናል። በተወሰነ መጠንም ቢሆን የመስክ ስምሪት ስብሰባዎች ሥልጠና የሚገኝባቸው ቦታዎች ናቸው፤ በመሆኑም አቅኚዎች ያካበቱትን እውቀትና ልምድ ተጠቅመው ለሌሎች ከፍተኛ እርዳታ መስጠት ይችላሉ። አቅኚዎች በተደጋጋሚ አገልግሎት መውጣታቸው በአገልግሎት ረገድ ጥሩ ልምድ እንዲያገኙ አስችሏቸዋል። ይህን ልምዳቸውን ደግሞ ማካፈል ይችላሉ። አቅኚዎች በአገልግሎትና በስምሪት ስብሰባዎች ላይ በቅንዓት መካፈላቸው ለሌሎች ግሩም ምሳሌ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። በመሆኑም በእነዚህ ስብሰባዎች ላይ ለሚያደርጉት ተሳትፎ ሊመሰገኑ ይገባል።

10. ሁሉም የመንግሥቱ ሰባኪዎች ይህን ዝግጅት ለመደገፍ ልባዊ ጥረት ማድረጋቸው ተገቢ የሆነው ለምንድን ነው?

10 ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ እንዳደረጉት ሁሉ የመንግሥቱን ስብከት ሥራችንን በአብዛኛው የምናከናውነው ከቤት ወደ ቤት በመመሥከር ነው። የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች ዓላማ እርስ በርስ እንድንበረታታ ማድረግና በዚህ ሥራ ላይ ውጤታማ ተሳትፎ እንዲኖረን መርዳት ነው። ሁሉም የምሥራቹ ሰባኪዎች ይህን ቲኦክራሲያዊ ዝግጅት ለመደገፍ አቅማቸው የፈቀደውን ያህል መጣር ይኖርባቸዋል። (ሥራ 5:42፤ 20:20) ሁላችንም ይህን ዝግጅት ለመደገፍ ልባዊ ጥረት እናድርግ። የምንሰብከው የአምላክን መንግሥት ምሥራች እንደመሆኑ መጠን ዝግጅቱን መደገፋችን ከይሖዋ ዘንድ የተትረፈረፈ በረከት የሚያስገኝልን ከመሆኑም ሌላ የመሪያችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ልብ ያስደስተዋል።—ማቴ. 25:34-40፤ 28:19, 20

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ