የ2002 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም
መመሪያዎች
በ2002 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት በሚከተሉት ዝግጅቶች መሠረት ይከናወናል።
ትምህርቶቹ የተወሰዱባቸው ጽሑፎች፦ ክፍሎቹ በሚከተሉት ጽሑፎች ላይ የተመሠረቱ ይሆናሉ:- መጽሐፍ ቅዱስ [1954]፣ መጠበቂያ ግንብ [wAM]፣ “ ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ በአምላክ መንፈስ አነሣሽነት የተጻፈና ጠቃሚ ነው” (የ1990 እትም) [si ]፣ እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው? እና ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር [rsAM]።
ትምህርት ቤቱ ልክ በሰዓቱ በመዝሙር፣ በጸሎትና አጠር ባለ ሰላምታ ይከፈታል። በፕሮግራሙ ውስጥ የተካተቱትን ክፍሎች አስቀድሞ መናገር አስፈላጊ አይደለም። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች እያንዳንዱን ክፍል ሲያስተዋውቅ ማብራሪያ የሚሰጥበትን ርዕስ ይናገራል። ክፍሎቹ በሚከተለው መንገድ ይከናወናሉ፦
ክፍል ቁ. 1፦ 15 ደቂቃ። ይህ ክፍል በአንድ ሽማግሌ ወይም በአንድ የጉባኤ አገልጋይ መቅረብ ይኖርበታል። ክፍሉ በመጠበቂያ ግንብ ወይም “ ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ በአምላክ መንፈስ አነሣሽነት የተጻፈና ጠቃሚ ነው” በተባለው መጽሐፍ ላይ የተመሠረተ ይሆናል። ክፍሉ ከመጠበቂያ ግንብ በሚቀርብበት ጊዜ ለ15 ደቂቃ እንደ ማስተማሪያ ንግግር ሆኖ ይቀርባል። የክለሳ ጥያቄ አይኖረውም። “ ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ” ከተባለው መጽሐፍ በሚቀርብበት ጊዜ ከ10 እስከ 12 ደቂቃ እንደ ማስተማሪያ ንግግር ይቀርብና በጽሑፉ ላይ ባሉት ጥያቄዎች በመጠቀም ከ3 እስከ 5 ደቂቃ የክለሳ ጥያቄ ይቀርባል። ዓላማው የተመደበውን ክፍል መሸፈን ብቻ ሳይሆን ለጉባኤው በጣም ጠቃሚ የሆነውን ሐሳብ እያጎሉ በትምህርቱ ተግባራዊ ጠቀሜታ ላይ ማተኮር ሊሆን ይገባል። በፕሮግራሙ ላይ የተጠቀሰውን ጭብጥ መጠቀም ይገባል።
ይህንን ክፍል እንዲያቀርቡ የተመደቡት ወንድሞች በተወሰነው ጊዜ ለመጨረስ ንቁ መሆን አለባቸው። አስፈላጊ ከሆነ ወይም ተናጋሪው ከጠየቀ በግል ምክር መስጠት ይቻላል።
ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የተገኙ ጎላ ያሉ ነጥቦች፦ 6 ደቂቃ። ይህ ክፍል ትምህርቱን ጉባኤው ከሚያስፈልጉት ነገሮች ጋር በጥሩ ሁኔታ አዛምዶ ማቅረብ በሚችል ሽማግሌ ወይም የጉባኤ አገልጋይ ሊቀርብ ይገባል። ጭብጥ መስጠት አያስፈልግም። የተመደቡትን ምዕራፎች ሐሳብ በመከለስ ብቻ መቅረብ የለበትም። የተመደቡትን ምዕራፎች አጠቃላይ ሐሳብ ከ30 እስከ 60 ሴኮንድ ውስጥ መከለስ ይቻላል። ቢሆንም ዋናው ዓላማ አድማጮች ትምህርቱ ለምን እና እንዴት ሊጠቅመን እንደሚችል እንዲገነዘቡ መርዳት ነው። ከዚህ በኋላ ተማሪዎቹ ወደየክፍላቸው መሄድ እንደሚችሉ የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ያስታውቃል።
ክፍል ቁ. 2፦ 5 ደቂቃ። ይህ ክፍል አንድ ወንድም የሚያቀርበው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ነው። ትምህርት ቤቱ በሚካሄድበት በዋናው አዳራሽም ይሁን በተጨማሪዎቹ ክፍሎች በዚሁ መንገድ ይቀርባል። ምንባቡ ብዙውን ጊዜ አጠር ያለ ስለሚሆን ተማሪው በመግቢያውና በመደምደሚያው ላይ መጠነኛ ማብራሪያ ለመስጠት ያስችለዋል። ከበስተኋላ ያለውን ታሪካዊ አመጣጥ፣ ትንቢታዊ ወይም መሠረተ ትምህርታዊ ትርጉሙንና የመሠረታዊ ሥርዓቶቹን ተግባራዊነት መጥቀስ ይቻላል። የተመደቡት ጥቅሶች በሙሉ ሳይቆራረጡ መነበብ ይኖርባቸዋል። የሚነበቡት ጥቅሶች ተከታታይ ካልሆኑ ግን ተማሪው ቀጥሎ የሚያነበውን ጥቅስ ቁጥር መናገር ይችላል።
ክፍል ቁ. 3፦ 5 ደቂቃ። ይህ ክፍል ለአንዲት እህት ይሰጣል። የዚህ ክፍል ትምህርት የተመሠረተው እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው ወይም ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር ከተባሉት መጻሕፍት ላይ ነው። ከአገልግሎት ክልሉ ጋር ተስማሚ የሆነ ማንኛውንም መቼት መጠቀም ይቻላል፤ እንዲሁም በክፍሉ ውስጥ የሚሳተፉ ክፍሉን ሲያቀርቡ መቀመጥ ወይም መቆም ይችላሉ። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በተለይ ተማሪዋ የተሰጣትን ጭብጥ የምታዳብርበትንና የቤቱ ባለቤት የጥቅሶቹን ትርጉም እንዲገነዘብ የምትረዳበትን መንገድ ለማየት ይፈልጋል። ይህን ክፍል እንድታቀርብ የተመደበችው ማንበብ የምትችል መሆን አለባት። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች አንድ ረዳት ይመድብላታል፤ ሆኖም ተጨማሪ ረዳት ማዘጋጀት ይቻላል። በአንደኛ ደረጃ ሊታሰብበት የሚገባው መቼቱ ሳይሆን ትምህርቱ ውጤታማ በሆነ መንገድ መቅረቡ ነው።
ክፍል ቁ. 4፦ 5 ደቂቃ። የዚህ ክፍል ትምህርት ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር በተባለው መጽሐፍ ላይ የተመሠረተ ነው። ይህ ክፍል ለአንድ ወንድም ወይም ለአንዲት እህት ይሰጣል። ክፍሉ ለአንድ ወንድም በሚሰጥበት ጊዜ ለጠቅላላው ጉባኤ በንግግር መልክ መቅረብ ይኖርበታል። ክፍሉ ለእህት ከተሰጠ ለሦስተኛው ክፍል በተሰጠው መመሪያ መሠረት መቅረብ ይኖርበታል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም፦ በጉባኤው ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ግለሰብ በቀን አንድ ገጽ እንዲያነብ ሆኖ የተዘጋጀውን ሳምንታዊውን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ በወጣው ፕሮግራም መሠረት ተከትሎ እንዲያነብ ይበረታታል።
ማሳሰቢያ፦ ምክር መስጠትን፣ ጊዜ መጠበቅን፣ የክለሳ ጥያቄዎችንና ክፍሎች መዘጋጀትን በሚመለከት ተጨማሪ ሐሳብ ወይም መመሪያ ለማግኘት የጥቅምት 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 3ን ተመልከቱ።
ፕሮግራም
ጥር 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መክብብ 1-6
መዝሙር ቁ. 78 (175)
ቁ. 1፦የመክብብ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (si ገጽ 112-13 አን. 1-8)
ቁ. 2፦መክብብ 4:1-16
ቁ. 3፦ጲላጦስ ኢየሱስን የፈራው ለምንድን ነው? (gt ምዕ. 124)
ቁ. 4፦ሰው ሆነን ከመወለዳችን በፊት በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ እንኖር ነበርን? (rs ገጽ 162 አን. 1–ገጽ 163 አን. 1)
ጥር 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦መክብብ 7-12
መዝሙር ቁ. 35 (79)
ቁ. 1፦መክብብ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 114 አን. 15-19)
ቁ. 2፦መክብብ 8:1-17
ቁ. 3፦ኢየሱስ ለሰው ዘር ፍቅር እንዳለው የሚያረጋግጥ ማስረጃ (gt ምዕ. 125)
ቁ. 4፦አንድ ሰው እውነተኛ ደስታ ያለበት ሕይወት እንዲያገኝ ወደ ሰማይ መሄድ ይኖርበታልን? (rs ገጽ 163 አን. 4-6)
ጥር 2 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦መኃልየ መኃልይ 1-8
መዝሙር ቁ. 83 (187)
ቁ. 1፦የመኃልየ መኃልይ ማስተዋወቂያ እና ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 115-17 አን. 1-4, 16-18)
ቁ. 2፦መኃልየ መኃልይ 5:1-16
ቁ. 3፦ኢየሱስ እስከ ፍጻሜ ድረስ ምሳሌ የሆነው እንዴት ነው? (gt ምዕ. 126)
ቁ. 4፦የ1 ጴጥሮስ 4:6 ትርጉም ምንድን ነው? (rs ገጽ 164 አን. 2)
ጥር 28 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ኢሳይያስ 1-6
መዝሙር ቁ. 90 (204)
ቁ. 1፦የኢሳይያስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (si ገጽ 118-19 አን. 1-8)
ቁ. 2፦ኢሳይያስ 2:1-17
ቁ. 3፦የኢየሱስ መቀበርና የመቃብሩ ባዶ ሆኖ መገኘት ትኩረታችንን የሚስበው ለምንድን ነው? (gt ምዕ. 12)
ቁ. 4፦“አዲስ ኪዳን” በምድር ላይ ለዘላለም ስለመኖር ምን ይገልጻል? (rs ገጽ 165 አን 3–ገጽ 166 አን. 3)
የካቲት 4 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ኢሳይያስ 7-11
መዝሙር ቁ. 41 (89)
ቁ. 1፦የይሖዋ ድርጅት ያስፈልገናል (w00 1/1 ገጽ 30-1)
ቁ. 2፦ኢሳይያስ 8:1-22
ቁ. 3፦የኢየሱስ ትንሣኤ የፈጠረው ደስታ (gt ምዕ. 128)
ቁ. 4፦144, 000ዎቹ ከሥጋዊ አይሁዳውያን ብቻ የተውጣጡ ናቸውን? (rs ገጽ 167 አን. 1-4)
የካቲት 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ኢሳይያስ 12-19
መዝሙር ቁ. 79 (177)
ቁ. 1፦ስለ ራስህ ያለህ አመለካከት ምን ይመስላል? (w00 1/15 ገጽ 20-2)
ቁ. 2፦ኢሳይያስ 17:1-14
ቁ. 3፦በትንሣኤ ላይ ያላቸው እምነት ጠነከረ (gt ምዕ. 129)
ቁ. 4፦ወደ ሰማይ የሚሄዱት በዚያ ምን ያደርጋሉ? (rs ገጽ 168 አን. 3-7)
የካቲት 18 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ኢሳይያስ 20-26
መዝሙር ቁ. 97 (217)
ቁ. 1፦ከይሖዋ ጋር ያላችሁን ወዳጅነት አጎልብቱ (w00 1/15 ገጽ 23-6)
ቁ. 2፦ኢሳይያስ 22:1-19
ቁ. 3፦ኢየሱስ ፍቅር እንዴት ማሳየት እንደሚቻል ገለጸ (gt ምዕ. 130)
ቁ. 4፦መጽሐፍ ቅዱስ ሲኦል ብሎ ወደሚጠራው ሥፍራ የሚሄዱት ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው? (rs ገጽ 170 አን. 2-4)
የካቲት 25 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ኢሳይያስ 27-31
መዝሙር ቁ. 64 (151)
ቁ. 1፦አሳዳጁ ሰው ታላቅ ብርሃን አየ (w00 1/15 ገጽ 27-9)
ቁ. 2፦ኢሳይያስ 29:1-14
ቁ. 3፦ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ያበረታታው እንዴት ነው? (gt ምዕ. 131)
ቁ. 4፦ክፉዎች ለዘላለም ይቀጣሉን? (rs ገጽ 172 አን. 1-3)
መጋቢት 4 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ኢሳይያስ 32-37
መዝሙር ቁ. 43 (98)
ቁ. 1፦በመጽናት የሚገኝ ስኬት (w00 2/1 ገጽ 4-6)
ቁ. 2፦ኢሳይያስ 33:1-16
ቁ. 3፦ኢየሱስ በአምላክ ቀኝ ተቀምጦ ምን ያደርጋል? (gt ምዕ. 132)
ቁ. 4፦ኢየሱስ የጠቀሰው ‘ገሃነመ እሳት’ ምንድን ነው? (rs ገጽ 173 አን. 2–ገጽ 174 አን. 1)
መጋቢት 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ኢሳይያስ 38-42
መዝሙር ቁ. 54 (132)
ቁ. 1፦አንዲት እናት የሰጠችው ጥበብ ያዘለ ምክር (w00 2/1 ገጽ 30-1)
ቁ. 2፦ኢሳይያስ 42:1-16
ቁ. 3፦ኢየሱስ በምድር ላይ ከኖሩት ሁሉ ታላቅ ሰው የተባለው ለምንድን ነው? (gt ምዕ. 133)
ቁ. 4፦ኢየሱስ ክፉዎች ከሞቱ በኋላ እንደሚሠቃዩ አስተምሯልን? (rs ገጽ 175 አን. 1)
መጋቢት 18 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ኢሳይያስ 43-47
መዝሙር ቁ. 69 (160)
ቁ. 1፦ከአደጋ ቀጣናው ራቁ (w00 2/15 ገጽ 4-7)
ቁ. 2፦ኢሳይያስ 44:6-20
ቁ. 3፦ሁሉም ሰው ታላቅ ሰው የተባለውን መጽሐፍ ማንበብ የሚኖርበት ለምንድን ነው? (gt—ከመጽሐፉ መግቢያ ላይ ተዘጋጅ)
ቁ. 4፦የገና በዓል በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ነውን? (rs ገጽ 176 አን. 2–ገጽ 177 አን. 1)
መጋቢት 25 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ኢሳይያስ 48-52
መዝሙር ቁ. 20 (45)
ቁ. 1፦ጸሎት ያለው ኃይል (w00 3/1 ገጽ 3-4)
ቁ. 2፦ኢሳይያስ 49:1-13
ቁ. 3፦ኮከብ ኢየሱስ ወደሚገኝበት የመራቸው ጠቢባን ወይም ሰብአ ሰገል እነማን ነበሩ? (rs ገጽ 177 አን. 2-4)
ቁ. 4፦የገናን በዓል አከባበር ስንመረምር የትኞቹን ልማዶች ግምት ውስጥ ማስገባት ይገባናል? (rs ገጽ 178 አን. 1-3)
ሚያዝያ 1 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ኢሳይያስ 53-59
መዝሙር ቁ. 17 (38)
ቁ. 1፦ልብን አዘጋጅቶ ይሖዋን መፈለግ (w00 3/1 ገጽ 29-31)
ቁ. 2፦ኢሳይያስ 54:1-17
ቁ. 3፦ክብረ በዓሎችን በተመለከተ ልንመራባቸው የሚገቡ መሠረታዊ ሥርዓቶች የትኞቹ ናቸው? (rs ገጽ 178 አን. 4-ገጽ 179 አን. 3)
ቁ. 4፦በዓለ ትንሣኤንና ዘመን መለወጫን በተመለከተ ልናውቃቸው የሚገቡ ነገሮች ምንድን ናቸው? (rs ገጽ 179 አን. 4-ገጽ 180 አን. 4)
ሚያዝያ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ኢሳይያስ 60-66
መዝሙር ቁ. 30 (63)
ቁ. 1፦ኢሳይያስ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 123 አን. 34-9)
ቁ. 2፦ኢሳይያስ 61:1-11
ቁ. 3፦“የሙታንን መናፍስት” ለማስታወስ የሚከበሩት በዓላት ምንጫቸው ምንድን ነው? (rs ገጽ 181 አን. 1–ገጽ 182 አን. 1)
ቁ. 4፦ ስለ ቫለንቲን ቀን፣ ስለ እናቶች ቀን እና ስለ ብሔራዊ በዓላት ምን የምናውቀው ነገር አለ? (rs ገጽ 182 አን.3–ገጽ 183 አን. 2)
ሚያዝያ 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ኤርምያስ 1-4
መዝሙር ቁ. 32 (70)
ቁ. 1፦የኤርምያስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (si ገጽ 124 አን. 1-5)
ቁ. 2፦ኤርምያስ 2:4-19
ቁ. 3፦ምስሎችን ለአምልኮ መጠቀምን በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? (rs ገጽ 183 አን. 3–ገጽ 184 አን. 3)
ቁ. 4፦ምስሎች እውነተኛውን አምላክ ለማምለክ የሚረዱ መሣሪያዎች ሆነው ሊያገለግሉ ይችላሉን? (rs ገጽ 184 አን. 4-8)
ሚያዝያ 22 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ኤርምያስ 5-8
መዝሙር ቁ. 34 (77)
ቁ. 1፦የሰው ዘር ረዳት የሚያስፈልገው ለምንድን ነው? (w00 3/15 ገጽ 3-4)
ቁ. 2፦ኤርምያስ 7:1-20
ቁ. 3፦“ቅዱሳን” አምላክን ያማልዳሉ ብለን ልዩ አክብሮት ልንሰጣቸው ይገባልን? (rs ገጽ 184 አን. 9–ገጽ 185 አን. 5)
ቁ. 4፦የሚሰገድላቸውን ምስሎች አምላክ እንዴት ይመለከታቸዋል? (rs ገጽ 186 አን. 1-4)
ሚያዝያ 29 የጽሑፍ ክለሳ። የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኤርምያስ 9-13
መዝሙር ቁ. 21 (46)
ግንቦት 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኤርምያስ 14-18
መዝሙር ቁ. 67 (156)
ቁ. 1፦ኢየሱስ ክርስቶስ ሊረዳን የሚችለው እንዴት ነው? (w00 3/15 ገጽ 5-9)
ቁ. 2፦ኤርምያስ 17:1-18
ቁ. 3፦በፊት እንደ ቅዱስ አድርገን እናያቸው ስለነበሩት ምስሎች ምን ሊሰማን ይገባል? (rs ገጽ 186 አን. 5-ገጽ 187 አን. 2)
ቁ. 4፦ምስሎችን ለአምልኮ መጠቀም በወደፊት ሕይወታችን ላይ ምን ውጤት ይኖረዋል? (rs ገጽ 187 አን. 3-6)
ግንቦት 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ኤርምያስ 19-23
መዝሙር ቁ. 57 (136)
ቁ. 1፦ልክን ማወቅ—ሰላምን ለማስፈን የሚረዳ ባሕርይ (w00 3/15 ገጽ 21-4)
ቁ. 2፦ኤርምያስ 19:1-15
ቁ. 3፦ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን የአቋም ደረጃዎች ወደጎን ገሸሽ በሚያደርጉበት ጊዜ እውነተኛ ነፃነት ያገኛሉን? (rs ገጽ 188 አን. 1-3)
ቁ. 4፦መጽሐፍ ቅዱስ ቁሳዊ ሀብት ስለማሳደድና አልኮል ያለልክ ስለመጠጣት ምን ምክር ይሰጣል? (rs ገጽ 188 አን. 4–ገጽ 189 አን. 1)
ግንቦት 20 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ኤርምያስ 24-28
መዝሙር ቁ. 61 (144)
ቁ. 1፦እርማት በመቀበል ረገድ ምሳሌ የሚሆን ሰው (w00 3/15 ገጽ 25-8)
ቁ. 2፦ኤርምያስ 25:1-14
ቁ. 3፦ከይሖዋ ጋር የመሠረትከውን ዝምድና ከፍ አድርገህ በመመልከት ከመጥፎ ጓደኝነት ራቅ (rs ገጽ 189 አን. 3)
ቁ. 4፦ሰዎች የአምላክን ትእዛዛት ቸል እንዲሉ የሚገፋፋቸው ማን ነው? (rs ገጽ 190 አን. 1-2)
ግንቦት 27 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ኤርምያስ 29-31
መዝሙር ቁ. 18 (42)
ቁ. 1፦የአምላክ መንፈስ በአሁኑ ጊዜ የሚሠራው እንዴት ነው? (w00 4/1 ገጽ 8-11)
ቁ. 2፦ኤርምያስ 30:1-16
ቁ. 3፦የትኞቹን ዝንባሌዎች ማስወገድ ይገባናል? (rs ገጽ 190 አን. 3–ገጽ 191 አን. 3)
ቁ. 4፦አንድ ሰው በራስ የመመራት ፍላጎቱ ዓለምን እንዲመስል ካደረገው በማን ቁጥጥር ሥር መሆኑ ነው? (rs ገጽ 191 አን. 4-5)
ሰኔ 3 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ኤርምያስ 32-35
መዝሙር ቁ. 38 (85)
ቁ. 1፦ይሖዋ በሚሰጠው ብርታት ማጽናኛ ማግኘት (w00 4/15 ገጽ 4-7)
ቁ. 2፦ኤርምያስ 34:1-16
ቁ. 3፦ዛሬ በብዙ ቦታዎች በሚሠራባቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ውስጥ የአምላክ ስም የት ላይ ይገኛል? (rs ገጽ 191 አን. 6–ገጽ 193 አን. 10)
ቁ. 4፦ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች በአምላክ የግል ስም የማይጠቀሙት ለምንድን ነው? (rs ገጽ 194 አን. 1–ገጽ 195 አን. 2)
ሰኔ 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ኤርምያስ 36-40
መዝሙር ቁ. 71 (163)
ቁ. 1፦ለዓመፀኞች ያለህ አመለካከት ከአምላክ አመለካከት ጋር ይስማማልን? (w00 4/15 ገጽ 26-9)
ቁ. 2፦ኤርምያስ 37:1-17
ቁ. 3፦መለኮታዊው ስም ትክክለኛ አጠራሩ የትኛው ነው—ይሖዋ ወይም ያህዌህ? (rs ገጽ 195 አን. 3–ገጽ 198 አን. 3)
ቁ. 4፦በ“ብሉይ ኪዳን” ውስጥ ይሖዋ የተባለው በ“አዲስ ኪዳን” ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ የተባለው ነውን? (rs ገጽ 198 አን. 4–7)
ሰኔ 17 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ኤርምያስ 41-45
መዝሙር ቁ. 9 (26)
ቁ. 1፦“አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ” (w00 5/15 ገጽ 20-4)
ቁ. 2፦ኤርምያስ 41:1-15
ቁ. 3፦አንድ ሰው ይሖዋን መፍራት ካለበት እንዴት ሊወደው ይችላል? (rs ገጽ 199 አን. 1-2)
ቁ. 4፦የይሖዋ ምሥክሮችን ከሌሎች ሃይማኖቶች የተለዩ የሚያደርጓቸው እምነቶች ምንድን ናቸው? (rs ገጽ 199 አን. 3–ገጽ 201 አን. 3)
ሰኔ 24 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ኤርምያስ 46–49
መዝሙር ቁ. 100 (222)
ቁ. 1፦ፍጹም የሆነ ሕይወት ሕልም አይደለም! (w00 6/15 ገጽ 5-7)
ቁ. 2፦ኤርምያስ 49:1-13
ቁ. 3፦የይሖዋ ምሥክሮች እምነት የአሜሪካ ሃይማኖት ነውን? (rs ገጽ 201 አን. 4–ገጽ 202 አን. 4)
ቁ. 4፦የይሖዋ ምሥክሮች ኑፋቄ ናቸውን? (rs ገጽ 202 አን. 5–ገጽ 204 አን. 1)
ሐምሌ 1 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ኤርምያስ 50-52
መዝሙር ቁ. 84 (190)
ቁ. 1፦ኤርምያስ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 129 አን. 36-9)
ቁ. 2፦ኤርምያስ 50:1-16
ቁ. 3፦የይሖዋ ምሥክሮች የእነርሱ ሃይማኖት ብቻ ትክክለኛ ነው ብለው ያምናሉን? (rs ገጽ 204 አን. 2-3)
ቁ. 4፦እውነተኛው ሃይማኖት መጽሐፍ ቅዱስን በጥብቅ ይከተላል (rs ገጽ 204 አን. 4)
ሐምሌ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ሰቆቃወ ኤርምያስ 1-2
መዝሙር ቁ. 4 (8)
ቁ. 1፦የሰቆቃወ ኤርምያስ ማስተዋወቂያ (si ገጽ 130-1 አን. 1-7)
ቁ. 2፦ሰቆቃው ኤርምያስ 1:1-14
ቁ. 3፦የይሖዋ ምሥክሮች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጧቸውን ማብራሪያዎች የሚያገኙት እንዴት ነው? (rs ገጽ 205 አን. 1–ገጽ 206 አን. 2)
ቁ. 4፦በይሖዋ ምሥክሮች ትምህርት ላይ ለውጦች የተደረጉት ለምንድን ነው? (rs ገጽ 206 አን. 3)
ሐምሌ 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ሰቆቃወ ኤርምያስ 3-5
መዝሙር ቁ. 12 (32)
ቁ. 1፦ሰቆቃው ኤርምያስ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 132 አን. 13-15)
ቁ. 2፦ሰቆቃው ኤርምያስ 3:1-30
ቁ. 3፦የይሖዋ ምሥክሮች ከቤት ወደ ቤት እየሄዱ የሚሰብኩት ለምንድን ነው? (rs ገጽ 206 አን. 4–ገ 207 አን. 3)
ቁ. 4፦የይሖዋ ምሥክሮች የሚሰደዱት ለምንድን ነው? (rs ገጽ 207 አን. 5–ገጽ 208 አን. 1)
ሐምሌ 22 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ሕዝቅኤል 1-6
መዝሙር ቁ. 13 (33)
ቁ. 1፦የሕዝቅኤል መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (si ገጽ 132-3 አን. 1-6)
ቁ. 2፦ሕዝቅኤል 4:1-17
ቁ. 3፦‘እናንተ የዓለምን ኑሮ ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት የማትካፈሉት ለምንድን ነው?’ (rs ገጽ 208 አን. 2–ገጽ 209 አን. 2)
ቁ. 4፦‘ክርስቲያኖች ምሥክሮች መሆን የሚኖርባቸው ለይሖዋ ሳይሆን ለኢየሱስ ነው’ (rs ገጽ 209 አን. 3)
ሐምሌ 29 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ሕዝቅኤል 7-12
መዝሙር ቁ. 99 (221)
ቁ. 1፦ጥሩ ምሳሌ የሚሆኑ ሰዎች ከተዉት አርአያ ጥቅም አግኝ (w00 7/1 ገጽ 19-21)
ቁ. 2፦ሕዝቅኤል 10:1-19
ቁ. 3፦ኢየሱስ ክርስቶስ በእርግጥ በሕይወት የኖረ ሰው ነውን? (rs ገጽ 210 አን. 1–ገጽ 211 አን. 1)
ቁ. 4፦ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያው ጥሩ ሰው ብቻ ነበርን? (rs ገጽ 211 አን. 2)
ነሐሴ 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ሕዝቅኤል 13-16
መዝሙር ቁ. 45 (106)
ቁ. 1፦በሥነ ምግባር በረከሰ ዓለም ውስጥ ንጽህናህን ጠብቀህ መኖር ትችላለህ (w00 7/15 ገጽ 28-31)
ቁ. 2፦ሕዝቅኤል 13:1-16
ቁ. 3፦ኢየሱስ ከሃይማኖት መሪዎች እንደ አንዱ ብቻ የሚቆጠር ነውን? (rs ገጽ 211 አን. 3)
ቁ. 4፦አይሁዳውያን በአጠቃላይ ኢየሱስን እንደ መሲሕ አድርገው ያልተቀበሉት ለምን ነበር? (rs ገጽ 212 አን. 1-2)
ነሐሴ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ሕዝቅኤል 17-20
መዝሙር ቁ. 56 (135)
ቁ. 1፦ለሥልጣን አክብሮት ማሳየት ያለብን ለምንድን ነው? (w00 8/1 ገጽ 4-7)
ቁ. 2፦ሕዝቅኤል 17:1-18
ቁ. 3፦ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ራሱ ነውን? (rs ገጽ 213 አን. 1-2)
ቁ. 4፦ዮሐንስ 1:1 ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን ያረጋግጣልን? (rs ገጽ 213 አን. 4–ገጽ 214 አን. 1)
ነሐሴ 19 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ሕዝቅኤል 21-23
መዝሙር ቁ. 39 (86)
ቁ. 1፦አለመግባባቶችን የምትፈቱት እንዴት ነው? (w00 8/15 ገጽ 23-5)
ቁ. 2፦ሕዝቅኤል 22:1-16
ቁ. 3፦በዮሐንስ 20:28 ላይ የተመዘገበው የቶማስ አነጋገር ኢየሱስ በእውነት እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ያረጋግጣልን? (rs ገጽ 214 አን. 2-4)
ቁ. 4፦ኢየሱስ በምድር ላይ ሳለ እግዚአብሔር እንደነበረ ማቴዎስ 1:23 ያሳያልን? (rs ገጽ 215 አን. 1-3)
ነሐሴ 26 የጽሑፍ ክለሳ። የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሕዝቅኤል 24-28
መዝሙር ቁ. 51 (127)
መስከረም 2 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ሕዝቅኤል 29-32
መዝሙር ቁ. 66 (155)
ቁ. 1፦የራስን ጥቅም የመሠዋት መንፈስ ማሳየት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (w00 9/15 ገጽ 21-4)
ቁ. 2፦ሕዝቅኤል 30:1-19
ቁ. 3፦የዮሐንስ 5:18 ትርጉም ምንድን ነው? (rs ገጽ 215 አን. 4-5)
ቁ. 4፦ኢየሱስ የሚሰገድለት መሆኑ እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን ያረጋግጣልን? (rs ገጽ 216 አን. 1-3)
መስከረም 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ሕዝቅኤል 33-36
መዝሙር ቁ. 63 (148)
ቁ. 1፦ወደ አምላክ መቅረብ የምትችልበት መንገድ (w00 10/15 ገጽ 4-7)
ቁ. 2፦ሕዝቅኤል 33:1-16
ቁ. 3፦ኢየሱስ ያደረጋቸው ተአምራት እርሱ እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ያረጋግጣሉን? (rs ገጽ 216 አን. 4–ገጽ 217 አን. 2)
ቁ. 4፦ለመዳን የሚያስፈልገው በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ብቻ ነውን? (rs ገጽ 217 አን. 4)
መስከረም 16 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ሕዝቅኤል 37-40
መዝሙር ቁ. 14 (34)
ቁ. 1፦ስኬትን የምትለካው በምንድን ነው? (w00 11/1 ገጽ 18-21)
ቁ. 2፦ሕዝቅኤል 39:1-16
ቁ. 3፦ኢየሱስ ሰው ከመሆኑ በፊት በሰማይ ይኖር ነበርን? (rs ገጽ 218 አን. 1-2)
ቁ. 4፦ኢየሱስ ሥጋዊ አካሉን ይዞ ወደ ሰማይ ሄዷልን? (rs ገጽ 218 አን. 3-6)
መስከረም 23 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ሕዝቅኤል 41-45
መዝሙር ቁ. 24 (50)
ቁ. 1፦አምላክን በፈቃደኛነት መንፈስ አገልግሉ (w00 11/15 ገጽ 21-3)
ቁ. 2፦ሕዝቅኤል 42:1-20
ቁ. 3፦ኢየሱስ ክርስቶስ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ነውን? (rs ገጽ 219 አን. 1-3)
ቁ. 4፦‘እናንተ በኢየሱስ አታምኑም’ (rs ገጽ 220 አን. 1-3)
መስከረም 30 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ሕዝቅኤል 46-48
መዝሙር ቁ. 47 (112)
ቁ. 1፦ሕዝቅኤል—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 137 አን. 29-33)
ቁ. 2፦ሕዝቅኤል 46:1-15
ቁ. 3፦‘ኢየሱስን እንደ ግል አዳኝህ አድርገህ ትቀበለዋለህን?’ (rs ገጽ 220 አን. 4–ገጽ 221 አን. 1)
ቁ. 4፦‘ኢየሱስን እንደ ግል አዳኜ አድርጌ ተቀብዬዋለሁ’ (rs ገጽ 221 አን. 2)
ጥቅምት 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ዳንኤል 1-4
መዝሙር ቁ. 5 (10)
ቁ. 1፦የዳንኤል መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (si ገጽ 138-9 አን. 1-6)
ቁ. 2፦ዳንኤል 1:1-17
ቁ. 3፦የዛሬዎቹ ሥጋዊ አይሁዳውያን የአምላክ ምርጥ ሕዝብ ናቸውን? (rs ገጽ 221 አን. 3–ገ 223 አን. 1)
ቁ. 4፦ወደፊት አይሁዳውያን በሙሉ ክርስቶስን አምነው ዘላለማዊ መዳን ያገኛሉን? (rs ገጽ 223 አን. 2-3)
ጥቅምት 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ዳንኤል 5-8
መዝሙር ቁ. 85 (191)
ቁ. 1፦“ጥበበኞች” የሚናገሩትን ሁልጊዜ ማመን ይኖርብሃልን? (w00 12/1 ገጽ 29-31)
ቁ. 2፦ዳንኤል 5:1-16
ቁ. 3፦አይሁዳውያን ለመዳን በኢየሱስ ማመን ይኖርባቸዋልን? (rs ገጽ 223 አን. 4–ገጽ 224 አን. 1)
ቁ. 4፦ዛሬ በእስራኤል ምድር የሚታዩት ሁኔታዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ፍጻሜ ናቸውን? (rs ገጽ 224 አን. 2–ገጽ 225 አን. 2)
ጥቅምት 21 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ዳንኤል 9-12
መዝሙር ቁ. 80 (180)
ቁ. 1፦ዳንኤል—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 141-2 አን. 19-23)
ቁ. 2፦ዳንኤል 10:1-21
ቁ. 3፦እስራኤል ተመልሳ እንደምትቋቋም የሚናገሩት ትንቢቶች በዛሬው ጊዜ ፍጻሜያቸውን እያገኙ ነውን? (rs ገጽ 225 አን. 3–226 አን. 2)
ቁ. 4፦የአምላክ መንግሥት እውን የሆነች መስተዳድር ናትን? (rs ገጽ 226 አን. 3–ገጽ 227 አን. 1)
ጥቅምት 28 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ:-ሆሴዕ 1-14
መዝሙር ቁ. 60 (143)
ቁ. 1፦የሆሴዕ መጽሐፍ ማስተዋወቂያና ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 143-5 አን. 1-8, 14-17)
ቁ. 2፦ሆሴዕ 4:1-19
ቁ. 3፦የመንግሥቱ ገዥዎች የሚሆኑት እነማን ናቸው? (rs ገጽ 227 አን. 2-4)
ቁ. 4፦ የአምላክ መንግሥት በሰብዓዊ መስተዳድሮች ላይ ምን ያስከትላል? (rs ገጽ 227 አን. 5-6)
ኅዳር 4 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ኢዩኤል 1-3
መዝሙር ቁ. 73 (166)
ቁ. 1፦የኢዩኤል መጽሐፍ ማስተዋወቂያና ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 146-8 አን. 1-5, 12-14)
ቁ. 2፦ኢዩኤል 1:1-20
ቁ. 3፦የአምላክ መንግሥት የይሖዋን ስም ያስቀድሳል (rs ገጽ 228 አን. 1-3)
ቁ. 4፦የአምላክ መንግሥት ፍጥረታት ሁሉ በአንድ ንጹሕ አምልኮ እንዲጠቃለሉ ያደርጋል (rs ገጽ 228 አን. 4–ገጽ 229 አን. 1)
ኅዳር 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦አሞጽ 1-9
መዝሙር ቁ. 22 (47)
ቁ. 1፦የአሞጽ መጽሐፍ ማስተዋወቂያና ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 148-50 አን. 1-6, 13-17)
ቁ. 2፦አሞጽ 1:1-15
ቁ. 3፦የአምላክ መንግሥት ጦርነትንና ምግባረ ብልሹነትን ያስወግዳል (rs ገጽ 229 አን. 2-5)
ቁ. 4፦የአምላክ መንግሥት ለመላው የሰው ልጅ የተትረፈረፈ ምግብ ያቀርባል እንዲሁም ሕመምን ያስወግዳል (rs ገጽ 229 አን. 6-8)
ኅዳር 18 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦አብድዩ 1–ዮናስ 4
መዝሙር ቁ. 23 (48)
ቁ. 1፦የአብድዩና የዮናስ መጻሕፍት ማስተዋወቂያና ጠቃሚ የሆኑበት ምክንያት (si ገጽ 151-3 አን. 1-5, 10-14፤ ገጽ 153-5 አን. 1-4, 9-12)
ቁ. 2፦አብድዩ 1:1-16
ቁ. 3፦የአምላክ መንግሥት እያንዳንዱ ሰው ቤት እንዲኖረው፣ ሥራ እንዲያገኝና ከማንኛውም አደጋ ነጻ እንዲሆን ያደርጋል (rs ገጽ 230 አን. 1-4)
ቁ. 4፦የአምላክ መንግሥት ጽድቅና ፍትሕ ያሰፍናል (rs ገጽ 230 አን. 5-7)
ኅዳር 25 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ሚክያስ 1-7
መዝሙር ቁ. 58 (138)
ቁ. 1፦የሚክያስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያና ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 155-8 አን. 1-8, 16-19)
ቁ. 2፦ሚክያስ 1:1-16
ቁ. 3፦የአምላክ መንግሥት ሙታንን ያስነሳል (rs ገጽ 231 አን. 1–4)
ቁ. 4፦የአምላክ መንግሥት ሰላምና ስምምነት የሰፈነበት ዓለም እንዲፈጠር ያደርጋል (rs ገጽ 231 አን. 5-7)
ታኅሣሥ 2 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ናሆም 1–ዕንባቆም 3
መዝሙር ቁ. 52 (129)
ቁ. 1፦የናሆምና የዕንባቆም መጻሕፍት ማስተዋወቂያና ጠቃሚ የሆኑበት ምክንያት (si ገጽ 158-60 አን. 1-7, 11-12፤ ገጽ 161-3 አን. 1-5, 12-14)
ቁ. 2፦ናሆም 3:1-19
ቁ. 3፦የአምላክ መንግሥት ምድርን ገነት ያደርጋል (rs ገጽ 232 አን. 1-3)
ቁ. 4፦የአምላክ መንግሥት በመጀመሪያው መቶ ዘመን መግዛት ጀምሯልን? (rs ገጽ 232 አን. 4-6)
ታኅሣሥ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ሶፎንያስ 1-ሐጌ 2
መዝሙር ቁ. 62 (146)
ቁ. 1፦የሶፎንያስና የሐጌ መጻሕፍት ማስተዋወቂያና ጠቃሚ የሆኑበት ምክንያት (si ገጽ 163 አን. 1-6, 10-12፤ ገጽ 166-8 አን. 1-7, 13-16)
ቁ. 2፦ሶፎንያስ 2:1-15
ቁ. 3፦የአምላክ መንግሥት መግዛት እንዲጀምር በመጀመሪያ ዓለም ወደ ክርስትና መለወጥ ይኖርበታልን? (rs ገጽ 233 አን. 1-2)
ቁ. 4፦‘የአምላክ መንግሥት በእኔ ዕድሜ አይመጣም’ (rs ገጽ 233 አን. 4-5)
ታኅሣሥ 16 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ዘካርያስ 1-8
መዝሙር ቁ. 1 (3)
ቁ. 1፦የዘካርያስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ (si ገጽ 168-9 አን. 1-7)
ቁ. 2፦ዘካርያስ 6:1-15
ቁ. 3፦‘በመጨረሻ ቀኖች’ ውስጥ እንደምንኖር የሚጠቁመው ምንድን ነው? (rs ገጽ 234 አን. 1)
ቁ. 4፦ጦርነትና ራብ ‘የምልክቱ’ ክፍል የሆኑት እንዴት ነው? (rs ገጽ 234 አን. 2–ገጽ 236 አን. 1)
ታኅሣሥ 23 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ዘካርያስ 9-14
መዝሙር ቁ. 74 (168)
ቁ. 1፦ዘካርያስ—ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት (si ገጽ 171-2 አን. 23-7)
ቁ. 2፦ዘካርያስ 9:1-17
ቁ. 3፦ሉቃስ 21:11 ከ1914 ወዲህ ፍጻሜውን እያገኘ ያለው እንዴት ነው? (rs ገጽ 236 አን. 2-4)
ቁ. 4፦የዓመፃ መብዛት ምን ያመለክታል? (rs ገጽ 237 አን. 1-2)
ታኅሣሥ 30 የጽሑፍ ክለሳ። የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሚልክያስ 1-4
መዝሙር ቁ. 50 (123)
ጊዜ በፈቀደልህ መጠን የተቃውሞ ሐሳብ ለሚሰነዝሩ ሰዎች የተሰጡ መልሶችን ስታቀርብ ለአካባቢው ይበልጥ ተስማሚ በሆኑት ላይ አተኩር።