የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ሰኔ 14 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 74 (168)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን የመግቢያ ሐሳቦች (ለጉባኤያችሁ ክልል የሚስማማ ከሆነ) በመጠቀም የሚያዝያ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የሚያዝያ 2004 ንቁ! መጽሔቶችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ አስፋፊው በንግድ አካባቢዎች ሲያገለግል የሚያሳይ ይሁን። ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ሌሎች መግቢያዎችን መጠቀም ይቻላል።
20 ደቂቃ፦ “ይሖዋ በእርሱ የሚታመኑትን ይረዳቸዋል።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንቀጽ 4ን ስትወያዩ ከመስከረም 2000 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 3, አንቀጽ 3, 4 እና ከአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 67, አንቀጽ 2 ላይ ካለው ሐሳብ ጨምረህ አቅርብ።
15 ደቂቃ፦ አደገኛ ዕፆችን መውሰድ የሌለብን ለምንድን ነው? በማመራመር መጽሐፍ ገጽ 106-9 ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። “ለመዝናናት” ሲባል ዕፅ መውሰድ የተለመደ ሲሆን ብዙዎች እንዲህ ማድረጉ ምንም ጉዳት እንደሌለው ይናገራሉ። እንዲያውም አንዳንዶች ዕፆችን መውሰድ ሕጋዊ መሆን አለበት ብለው ይከራከራሉ። እንደዚህ ያለ አመለካከት ያላቸውን ሰዎች እንዴት ማስረዳት እንደምንችል አብራራ። በታኅሣሥ 1999 ንቁ! ገጽ 10 ላይ ባለው ሣጥን ውስጥ የሚገኘውን ሐሳብ ጨምረህ አቅርብ።
መዝሙር 61 (144) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 21 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 11 (29)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ “መላእክት እየረዱን ነው።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ጊዜ በፈቀደ መጠን አድማጮች በጥቅሶቹ ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።
20 ደቂቃ፦ ላይኛይቱ ጥበብ ምክንያታዊ ናት። (ያዕ. 3:17 NW ) ከአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 251-2 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ምክንያታዊ መሆን ሲባል ምን ማለት ነው? በአገልግሎታችን ምክንያታዊ መሆን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ከሐዋርያው ጳውሎስ ምሳሌ ምን መማር እንችላለን? አስፋፊዎች በክልላቸው ውስጥ የሚገኙትን ሰዎች ሁኔታ ግምት ውስጥ ማስገባት የሚችሉት እንዴት ነው? የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ምክንያታዊ እንዲሆኑ ልንረዳቸው የምንችለው እንዴት ነው? ምክንያታዊ የሆነ አቀራረብ ያለውን ጠቀሜታ የሚያሳዩ ተሞክሮዎች የሚናገሩ አንድ ወይም ሁለት ሰዎች አስቀድመህ አዘጋጅ።
መዝሙር 25 (53) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 28 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 59 (139)
12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። አስፋፊዎች የሰኔ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በገጽ 4 ላይ የቀረቡትን የመግቢያ ሐሳቦች (ለጉባኤያችሁ ክልል የሚስማማ ከሆነ) በመጠቀም የሚያዝያ 15 መጠበቂያ ግንብ እና የሚያዝያ 22 ንቁ! (እንግሊዝኛ) መጽሔቶችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው ውይይቱን ሲጀምር ወዳጃዊ ስሜት የሚያንጸባርቅ አጠር ያለ ሐሳብ እንዲናገር አድርግ። እንደዚህ ማድረጋችን የቤቱ ባለቤት ዘና እንዲል ሊረዳው እንደሚችል ግለጽ።
15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
18 ደቂቃ፦ “የጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት—አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ለአንቀጾቹ በቀረቡት ጥያቄዎች ተጠቀም። በኅዳር 2002 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 1 ላይ ከሚገኘው “ከጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት የበላይ ተመልካቻችሁ ጋር ተባበሩ” ከሚለው ርዕስ ላይ ሐሳብ ጨምረህ አቅርብ።
መዝሙር 81 (181) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሐምሌ 5 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 1 (3)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ ምን ዓይነት አቀራረብ ትጠቀማላችሁ? በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በሐምሌና በነሐሴ ብሮሹሮችን እናበረክታለን። አስፋፊዎች በጉባኤያችሁ ክልል ውስጥ ይበልጥ ውጤታማ ሆነው ያገኟቸው ብሮሹሮች የትኞቹ ናቸው? በሐምሌ 1998 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 8 ወይም ቀደም ብለው በወጡ ሌሎች እትሞች ላይ የቀረቡትን የመግቢያ ሐሳቦች ከልስ። እያንዳንዱ መግቢያ (1) ጥያቄ፣ (2) ጥቅስ እንዲሁም (3) ከብሮሹሩ ላይ የተወሰደ ሐሳብን ያካተተ እንደሆነ ጎላ አድርገህ ግለጽ። በመግቢያ ሐሳቦቹ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳዩ አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ሁሉም አስፋፊዎች ምስራቹን በሚሰብኩበት ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲጠቀሙ አበረታታቸው።
20 ደቂቃ፦ ተስፋ አስቆራጭ በሆኑ ሁኔታዎች ሥር በተስፋ መኖር። በግንቦት 15, 1997 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 22-25 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር።
መዝሙር 89 (201) እና የመደምደሚያ ጸሎት።