ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ጥቅምት 25, 2004 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ በቃል መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከመስከረም 6 እስከ ጥቅምት 25, 2004 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ:- ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-7ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርይ
1. ክርስቲያኖች ሊያከናውኑት ስለሚገባ አንድ ሥራ ለጉባኤው ንግግር ስናቀርብ አዎንታዊ አቀራረብ ማንጸባረቅ የምንችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 203 አን. 2, 3]
2. መደጋገም ሲባል ምን ማለት ነው? አስፈላጊ የሆነውስ ለምንድን ነው? [be ገጽ 206 አን. 1-4]
3. የንግግራችንን ጭብጥ ማዳበር የምንችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 210 አን. 1-5፣ ሣጥኑን]
4. እንድናቀርብ ከተሰጠን ንግግር ውስጥ ዋና ዋናዎቹን ነጥቦች መምረጥ የምንችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 212 አን. 1-4]
5. ዋና ዋና ነጥቦቻችን እንዳይበዙ መጠንቀቅ የሚኖርብን ለምንድን ነው? [be ገጽ 213 አን. 2-4]
ክፍል ቁጥር 1
6. በኖኅ ዘመን የነበሩት ሰዎች በዙሪያቸው ያለው ዓለም በጠቅላላ ሊጠፋ መሆኑን ለመቀበል እንዲከብዳቸው ያደረጉት ከጥፋቱ በፊት የተገኙት የትኞቹ እድገቶች ሊሆኑ ይችላሉ? [w02 3/1 ገጽ 5-6]
7. በዘመኑ የነበሩት ሰዎች ኢየሱስን “መምህር” እንጂ “ፈዋሽ” ብለው አለመጥራታቸው ትኩረት የሚስብ የሆነው ለምንድን ነው? (ሉቃስ 3:12፤ 7:40) [w02 5/1 ገጽ 4 አን. 3፤ ገጽ 6 አን. 5]
8. ምሳሌ 11:24, 25 [የ1954 ትርጉም] በመስክ አገልግሎት የተሟላ ተሳትፎ ማድረግ ያለውን ጥቅም የሚያሳየው እንዴት ነው? [w02 7/15 ገጽ 30 አን. 3-5]
9. በኤደን ገነት የተፈጸመው ዓመጽ ምን ጥያቄ አስነስቷል? ምን ውጤትስ አስከትሏል? (ዘፍ. 3:1-6) [w02 10/1 ገጽ 6 አን. 1, 3, 4]
10. እውነተኛው አምልኮ በኢየሩሳሌም ተመልሶ የተቋቋመበት ዓመት የታወቀው እንዴት ነው? [si ገጽ 285 አን. 5]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. ይሖዋ ለበለዓም ከባላቅ ሰዎች ጋር እንዲሄድ ከነገረው በኋላ በለዓም አብሯቸው ሲሄድ የተቆጣው ለምን ነበር? (ዘኍ. 22:20-22)
12. አንድ ክርስቲያን ባል ሚስቱ የተሳለችውን ስእለት እንዳትፈጽም ሊከለክላት ይችላል? (ዘኍ. 30:6-8)
13. ‘የመማጸኛ ከተማ’ በዛሬው ጊዜ ምን ያመለክታል? (ዘኍ. 35:6) [w95 11/15 ገጽ 17 አን. 8]
14. በዘዳግም 6:6-9 ላይ የአምላክን ሕግጋት “በእጅህ ላይ ምልክት አድርገህ እሰራቸው፤ በግንባርህም ላይ ይሁኑ” የሚለውን ትእዛዝ መረዳት የሚኖርብን ቃል በቃል ነው?
15. “ልብስህ አላለቀም” ሲል እስራኤላውያን ልብሳቸው ሲያልቅ በሌላ ይተካላቸው ነበር ማለቱ ነው? (ዘዳ. 8:4)