የ2005 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም
መመሪያ
የ2005 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት በሚከተሉት ዝግጅቶች መሠረት ይከናወናል።
ክፍሎቹ የሚቀርቡባቸው ጽሑፎች፦ መጽሐፍ ቅዱስ [አ.መ.ት]፣ መጠበቂያ ግንብ [w-AM]፣ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም [be-AM]፣ “ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ በአምላክ መንፈስ አነሣሽነት የተጻፈና ጠቃሚ ነው” (የ1990 እትም) [si] እና ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር [rs-AM]።
ትምህርት ቤቱ ልክ በሰዓቱ በመዝሙር፣ በጸሎትና አጠር ባለ ሰላምታ ከተከፈተ በኋላ በሚከተለው መመሪያ መሠረት ይከናወናል:-
የንግግር ባሕርይ፦ 5 ደቂቃ። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች፣ ረዳት ምክር ሰጪው ወይም ጥሩ ችሎታ ያለው ሌላ ሽማግሌ ከአገልግሎት ትምህርት ቤት መማሪያ መጽሐፍ ላይ በአንድ የንግግር ባሕርይ ላይ የተመሠረተ ክፍል ያቀርባል። (በቂ ሽማግሌዎች በሌሉባቸው ጉባኤዎች ውስጥ ጥሩ ችሎታ ያለው የጉባኤ አገልጋይ ይህን ክፍል ሊያቀርብ ይችላል።) ተጨማሪ መግለጫ ካልተሰጠ በስተቀር ለሳምንቱ በተመደቡት ገጾች ውስጥ የሚገኙት ሣጥኖች በንግግሩ ውስጥ መካተት ይኖርባቸዋል። መልመጃዎቹ ተማሪው በግሉ እንዲለማመድባቸውና በግል ምክር ለመስጠት ታስበው የተዘጋጁ ስለሆኑ በክፍሉ ውስጥ መካተት አይኖርባቸውም።
ክፍል ቁ. 1፦ 10 ደቂቃ። ይህ ክፍል በአንድ ብቃት ያለው ሽማግሌ ወይም የጉባኤ አገልጋይ መቅረብ ይኖርበታል። ክፍሉ በመጠበቂያ ግንብ፣ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም ወይም “ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ በአምላክ መንፈስ አነሣሽነት የተጻፈና ጠቃሚ ነው” በተባሉት መጽሐፎች ላይ የተመሠረተ ይሆናል። ለአሥር ደቂቃ እንደ ማስተማሪያ ንግግር የሚቀርብ ሲሆን የክለሳ ጥያቄ አይኖረውም። ዓላማው በትምህርቱ ተግባራዊ ጠቀሜታ ላይ በማተኮር ለጉባኤው ጠቃሚ የሆነውን ሐሳብ ለማጉላት እንጂ የተመደበውን ክፍል ለመሸፈን ብቻ አይደለም። በፕሮግራሙ ላይ የተሰጠውን ጭብጥ መጠቀም አስፈላጊ ነው። ይህንን ንግግር እንዲያቀርቡ የተመደቡት ወንድሞች ክፍላቸውን በተወሰነው ጊዜ ውስጥ አቅርበው መጨረስ ይኖርባቸዋል። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በግል ምክር ሊሰጣቸው ይችላል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጎላ ያሉ ነጥቦች፦ 10 ደቂቃ። በመጀመሪያ ጥሩ ችሎታ ያለው ሽማግሌ ወይም የጉባኤ አገልጋይ ለስድስት ደቂቃ ያህል ትምህርቱን ጉባኤው ከሚያስፈልጉት ነገሮች ጋር እያዛመደ ያቀርበዋል። ጎላ ያሉ ነጥቦችን የሚያቀርበው ወንድም ለሳምንቱ ከተመደበው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ውስጥ በፈለገው ምዕራፍና ቁጥር ላይ ሐሳብ መስጠት ይችላል። ክፍሉ ለሳምንቱ የተመደቡትን ምዕራፎች በመከለስ ብቻ መቅረብ አይኖርበትም። ዋናው ዓላማ አድማጮች ትምህርቱ ለምን እና እንዴት እንደሚጠቅም እንዲገነዘቡ መርዳት ነው። ተናጋሪው ለእርሱ የተመደበለትን ስድስት ደቂቃ ብቻ በመጠቀም አድማጮች ተሳትፎ የሚያደርጉበትን አራት ደቂቃ ላለመንካት መጠንቀቅ ይኖርበታል። ቀጥሎ አድማጮች ከሳምንቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ልባቸውን የነካውንና ጠቃሚ ሆኖ ያገኙትን ሐሳብ በአጭሩ (በ30 ሴኮንድ ወይም ከዚያ ባነሰ ጊዜ) እንዲናገሩ ይጋብዛል። ከዚያም የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በሁለተኛው አዳራሽ ውስጥ ክፍል የሚያቀርቡ ተማሪዎች መሄድ እንደሚችሉ ያስታውቃል።
ክፍል ቁ. 2፦ 4 ደቂቃ። ይህን ክፍል አንድ ወንድም በንባብ ያቀርበዋል። ንባቡ አብዛኛውን ጊዜ የሚቀርበው ከመጽሐፍ ቅዱስ ይሆናል። በወር አንድ ጊዜ ክፍሉ ከመጠበቂያ ግንብ ይቀርባል። ተማሪው መግቢያ እና መደምደሚያ ማዘጋጀት ሳያስፈልገው ክፍሉን እንዲሁ በንባብ ብቻ ያቀርበዋል። በየሳምንቱ የሚነበበው ክፍል ርዝመት በተወሰነ መጠን የሚለያይ ቢሆንም ክፍሉ በአራት ደቂቃ ወይም ከዚያ ባነሰ ጊዜ ውስጥ መሸፈን ይኖርበታል። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች የተማሪውን ዕድሜና ችሎታ ግምት ውስጥ ማስገባት እንዲችል ክፍሉን ከመስጠቱ በፊት ትምህርቱን ማንበብ ይኖርበታል። በተጨማሪም ተማሪዎቹ ክፍሉን በሚገባ ተረድተው፣ በቅልጥፍና፣ ቁልፍ ቃላትን በተገቢው ሁኔታ በማጥበቅ፣ ድምፅን በመለዋወጥ፣ በተገቢው ቦታ ቆም በማለትና የራስን ተፈጥሯዊ አነጋገር በመጠቀም እንዲያነብቡ ለመርዳት ጥረት ያደርጋል።
ክፍል ቁ. 3፦ 5 ደቂቃ። ይህ ክፍል ለአንዲት እህት ይሰጣል። ይህን ክፍል እንዲያቀርቡ የተመደቡ ተማሪዎች በአገልግሎት ትምህርት ቤት መማሪያ መጽሐፍ ገጽ 82 ላይ ከተዘረዘሩት መቼቶች መካከል አንዱን መምረጥ ይችላሉ፤ ወይም የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ክፍላቸውን የሚያቀርቡበትን መቼት ይሰጣቸዋል። ተማሪዋ በፕሮግራሙ ላይ የሚገኘውን ጭብጥ መጠቀምና ክፍሉን ለጉባኤው የአገልግሎት ክልል በሚስማማ መንገድ ማቅረብ ይኖርባታል። ጭብጡ ብቻ በሚሰጥበት ጊዜ ተማሪዋ ታማኝና ልባም ባሪያ ባዘጋጃቸው ጽሑፎች ላይ ምርምር በማድረግ ለክፍሉ የሚስማሙ ነጥቦችን ማሰባሰብ ይኖርባታል። አዳዲስ ተማሪዎች ጭብጡ ብቻ የተሰጠባቸውን ክፍሎች ማቅረብ አይኖርባቸውም። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ተማሪዋ የተሰጣትን ጭብጥ እንዴት እንደምታዳብርና የቤቱ ባለቤት የጥቅሶቹን ትርጉምና የክፍሉን ዋና ዋና ነጥቦች እንዲገነዘብ የምትረዳበትን መንገድ ለማየት ይፈልጋል። ይህን ክፍል እንድታቀርብ የተመደበችው እህት ማንበብ የምትችል መሆን አለባት። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች አንድ ረዳት ይመድብላታል።
ክፍል ቁ. 4፦ 5 ደቂቃ። ተማሪው የተሰጠውን ጭብጥ ማዳበር ይኖርበታል። ጭብጡ ብቻ በሚሰጥበት ጊዜ ተማሪው ታማኝና ልባም ባሪያ ባዘጋጃቸው ጽሑፎች ላይ ምርምር በማድረግ ለክፍሉ የሚስማሙ ነጥቦችን ያሰባስባል። ይህ ክፍል ለአንድ ወንድም በሚሰጥበት ጊዜ የጉባኤውን አድማጭ ግምት ውስጥ በማስገባት በንግግር መልክ ያቀርበዋል። ሆኖም ክፍሉ ለአንዲት እህት ከተሰጠ ለክፍል ቁጥር 3 በተሰጠው መመሪያ መሠረት መቅረብ ይኖርበታል። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ተገቢ ሆኖ ባገኘው ጊዜ ክፍል ቁጥር 4ን ለአንድ ወንድም ሊሰጥ ይችላል። የኮከብ ምልክት ያለባቸው ክፍሎች በንግግር መልክ መቅረብ ያለባቸው ስለሆኑ ለወንድሞች ብቻ መሰጠት ይኖርባቸዋል።
ጊዜን መጠበቅ፦ ክፍል የሚያቀርቡትም ሆኑ ምክር ሰጪው የተመደበላቸውን ጊዜ ማሳለፍ አይኖርባቸውም። ከቁጥር 2 እስከ 4 ያሉትን ክፍሎች የሚያቀርቡት ወንድሞች የተመደበላቸው ጊዜ ሲሞላ በዘዴ እንዲያቆሙ ማድረግ ያስፈልጋል። ስለ ንግግር ባሕርይ የሚናገረው የመክፈቻ ንግግር፣ ክፍል ቁጥር 1 ወይም ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የተገኙ ጎላ ያሉ ነጥቦችን የሚያቀርቡ ወንድሞች ሰዓት ካሳለፉ በግል ምክር ሊሰጣቸው ይገባል። ሁሉም ሰዓታቸውን በሚገባ መጠበቅ አለባቸው። ጸሎትንና መዝሙርን ሳይጨምር ጠቅላላው ፕሮግራም 45 ደቂቃ ይፈጃል።
ምክር፦ 1 ደቂቃ። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከእያንዳንዱ የተማሪ ንግግር በኋላ የንግግሩን ገንቢ ጎኖች አንስቶ አስተያየት ለመስጠት ከአንድ ደቂቃ የበለጠ ጊዜ መውሰድ አይኖርበትም። ዓላማው “ጥሩ ነው” ብሎ ለማለፍ ብቻ መሆን የለበትም። ከዚህ ይልቅ የተማሪው አቀራረብ ጥሩ የሆነበትን ምክንያት ለይቶ መጥቀስ ያስፈልገዋል። የእያንዳንዱን ተማሪ ችሎታ ግምት ውስጥ በማስገባት ከስብሰባው በኋላ ወይም በሌላ ጊዜ ገንቢ የሆነ ተጨማሪ ምክር በግል መስጠት ይችላል።
ረዳት ምክር ሰጪ፦ የሽማግሌዎች አካል ከትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በተጨማሪ ረዳት ምክር ሰጪ ሆኖ የሚያገለግል ጥሩ ችሎታ ያለው ሽማግሌ ሊመርጥ ይችላል። በጉባኤው ውስጥ በርካታ ሽማግሌዎች ካሉ በየዓመቱ ብቃት ያላቸው ሽማግሌዎች እየተቀያየሩ ይህን ኃላፊነት ሊይዙ ይችላሉ። የዚህ ወንድም ኃላፊነት ንግግር ቁጥር 1ን እና ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የተገኙ ጎላ ያሉ ነጥቦችን ለሚያቀርቡ ወንድሞች አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በግል ምክር መስጠት ይሆናል። ይህ ሲባል ግን እነዚህን ክፍሎች የሚያቀርቡ ሽማግሌዎች ወይም የጉባኤ አገልጋዮች ንግግራቸውን ባቀረቡ ቁጥር ምክር ይሰጣቸዋል ማለት አይደለም። ይህ ዝግጅት በ2005ም ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ከዚያ በኋላ ማስተካከያ ሊደረግበት ይችላል።
ምክር መስጫ ነጥቦችን የያዘ ቅጽ፦ በመማሪያ መጽሐፉ ውስጥ ይገኛል።
የቃል ክለሳ፦ 30 ደቂቃ። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በየሁለት ወሩ የሚደረገውን የቃል ክለሳ ይመራል። ክለሳው የሚደረገው የንግግር ባሕርይና ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የተገኙ ጎላ ያሉ ነጥቦች ከላይ በተሰጠው መመሪያ መሠረት ከቀረቡ በኋላ ይሆናል። ክለሳው የሚሸፍነው፣ የክለሳውን ሳምንት ጨምሮ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ የቀረቡትን ትምህርቶች ይሆናል። የቃል ክለሳው በሚደረግበት ሳምንት ጉባኤያችሁ የወረዳ ስብሰባ ወይም የወረዳ የበላይ ተመልካች ጉብኝት ካለው በታኅሣሥ 2003 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 5 ላይ የወጣውን መመሪያ ተከተሉ።
ፕሮግራም
ጥር 3 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢያሱ 16-20መዝ. 3 (6)
የንግግር ባሕርይ፦ በቀላሉ የሚገባ (be ገጽ 226 አን. 1–ገጽ 227 አን. 1)
ቁ. 1፦ እግዚአብሔርን ፍራ (be ገጽ 272 አን. 1–ገጽ 273 አን. 1)
ቁ. 2፦ ኢያሱ 16:1 እስከ 17:4
ቁ. 3፦ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ብቻ በቂ የማይሆነው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 327 አን. 2-3)
ቁ. 4፦ በዛሬው ጊዜ አንድ ሰው ሃብታም ወይም ድሃ መሆኑ አምላክን የሚፈራ ለመሆኑ ምልክት ይሆናል?
ጥር 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢያሱ 21-24መዝ. 13 (33)
የንግግር ባሕርይ፦ እንግዳ የሆኑ ቃላትን ትርጉም ማስረዳት (be ገጽ 227 አን. 2–4)
ቁ. 1፦ የአምላክን ስም ማሳወቅ (be ገጽ 273 አን. 2–ገጽ 274 አን. 1)
ቁ. 2፦ ኢያሱ 23:1-13
ቁ. 3፦ ትክክለኛው ሃይማኖት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ከመሆኑም በላይ የአምላክን ስም ያሳውቃል (rs ገጽ 327 አን. 4-5)
ቁ. 4፦ ኢየሱስን ማምለክ ተገቢ ነው?
ጥር 17 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መሳፍንት 1-4መዝ. 49 (114)
የንግግር ባሕርይ፦ በቂ ማብራሪያ መስጠት (be ገጽ 228 አን. 1-2)
ቁ. 1፦ የስሙ ባለቤት የሆነው አምላክ (be ገጽ 274 አን. 2-5)
ቁ. 2፦ መሳፍንት 2:1-10
ቁ. 3፦ ትክክለኛው ሃይማኖት በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እውነተኛ እምነት እንዳለው በተግባር ያሳያል (rs ገጽ 328 አን. 1)
ቁ. 4፦ ጎጂ ከሆኑ የሙዚቃ ፊልሞች ራስህን መጠበቅ የምትችለው እንዴት ነው?
ጥር 24 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መሳፍንት 5-7መዝ. 22 (47)
የንግግር ባሕርይ፦ የልብ ዝንባሌ ወሳኝ ነው (be ገጽ 228 አን. 3–5)
ቁ. 1፦ የአምላክ ስም “ጽኑ ግንብ ነው” (be ገጽ 274 አን. 6–ገጽ 275 ንዑስ ርዕስ)
ቁ. 2፦ መሳፍንት 6:25-35
ቁ. 3፦ መጽሐፍ ቅዱስ የመምረጥ ነጻነታችንን እንዴት ሊነካው ይገባል?
ቁ. 4፦ ትክክለኛው ሃይማኖት በውጫዊ የአምልኮ ሥርዓቶች ላይ የተመሠረተ ሳይሆን የሕይወት መንገድ ነው (rs ገጽ 328 አን. 2)
ጥር 31 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መሳፍንት 8-10መዝ. 77 (174)
የንግግር ባሕርይ፦ ግንዛቤ የሚያሰፋ (be ገጽ 230 አን. 1-6)
ቁ. 1፦ ስለ ኢየሱስ መመሥከር (be ገጽ 275 ከንዑስ ርዕሱ –ገጽ 276 አን. 1)
ቁ. 2፦ w03 1/15 ገጽ 19-20 አን. 16-18
ቁ. 3፦ የእውነተኛው ሃይማኖት ተከታዮች እርስ በርስ ይዋደዳሉ እንዲሁም ከዓለም የተለዩ ናቸው (rs ገጽ 328 አን. 3-4)
ቁ. 4፦ ፍቅረ ነዋይ ሀብት ከማካበት የበለጠ ነገርን ያመለክታል
የካ. 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መሳፍንት 11-14መዝ. 92 (209)
የንግግር ባሕርይ፦ ምርምር በማድረግ ግንዛቤ የሚያሰፋ ንግግር ማቅረብ (be ገጽ 231 አን. 1-3)
ቁ. 1፦ ኢየሱስ ቤዛ በመሆን የተጫወተውን ሚና ማጉላት (be ገጽ 276 አን. 2-3)
ቁ. 2፦ መሳፍንት 12:1-15
ቁ. 3፦ የይሖዋ ምሥክሮች አንድነት ሊኖራቸው የቻለው ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ የእውነተኛው ሃይማኖት ተከታዮች ስለ አምላክ መንግሥት በትጋት ይመሠክራሉ (rs ገጽ 328 አን. 5)
የካ. 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መሳፍንት 15-18መዝ. 44 (105)
የንግግር ባሕርይ፦ ጥቅሶችን ማብራራት (be ገጽ 231 አን. 4-5)
ቁ. 1፦ ኢየሱስ ሊቀ ካህንና የጉባኤው ራስ በመሆን የሚጫወተውን ሚና ማጉላት (be ገጽ 277 አን. 1-2)
ቁ. 2፦ መሳፍንት 15:9-20
ቁ. 3፦ #አንድ ሰው ‘በኢየሱስ እስካመንህ ድረስ የየትኛውም ቤተ ክርስቲያን አባል ብትሆን ለውጥ የለውም’ ቢልስ? (rs ገጽ 331 አን. 3)
ቁ. 4፦ ክርስቲያኖች ስለ ሂፕኖቲዝም ሊኖራቸው የሚገባው አመለካከት ምንድን ነው?
የካ. 21 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መሳፍንት 19-21መዝ. 25 (53)
የንግግር ባሕርይ፦ የቃላትን ፍቺ መግለጽ (be ገጽ 232 አን. 1)
ቁ. 1፦ ኢየሱስ ንጉሥ በመሆን የሚጫወተውን ሚና ማጉላት (be ገጽ 277 አን. 3-4)
ቁ. 2፦ w03 2/1 ገጽ 17-18 አን. 18-21
ቁ. 3፦ #አንድ ሰው ‘ትክክለኛ የሆነ አንድ ሃይማኖት ብቻ አለ ለማለት የሚያበቃችሁ ምንድን ነው?’ ቢልስ? (rs ገጽ 331 አን. 4)
ቁ. 4፦ ‘ከእግዚአብሔር ጥልቅ ነገሮች’ መካከል አንዳንዶቹ ምንድን ናቸው? (1 ቆሮ. 2:10)
የካ. 28 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሩት 1-4መዝ. 69 (160)
የንግግር ባሕርይ፦ ጥቅሱን ከጉዳዩ ጋር ማዛመድ (be ገጽ 232 አን. 2-4)
የቃል ክለሳ
መጋ. 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ሳሙኤል 1-4መዝ. 99 (221)
የንግግር ባሕርይ፦ አድማጮችህን የሚጠቅም ሐሳብ መምረጥ (be ገጽ 233 አን. 1-5)
ቁ. 1፦ ክርስቶስን መሠረት አድርግ (be ገጽ 278 አን. 1-4)
ቁ. 2፦ 1 ሳሙኤል 2:1-11
ቁ. 3፦ ኢየሱስ ሥጋዊ አካል ለብሶ ወደ ሰማይ አልሄደም (rs ገጽ 333 አን. 2-4)
ቁ. 4፦ እውነተኛ ክርስቲያኖች በኮከብ ቆጠራ የማይካፈሉት ለምንድን ነው?
መጋ. 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ሳሙኤል 5-9መዝ. 64 (151)
የንግግር ባሕርይ፦ የተመደበልህን ጽሑፍ መጠቀም (be ገጽ 234 አን. 1–ገጽ 235 አን. 3)
ቁ. 1፦ ይህ የመንግሥት ወንጌል (be ገጽ 279 አን. 1-4)
ቁ. 2፦ 1 ሳሙኤል 5:1-12
ቁ. 3፦ ኢየሱስ ሥጋዊ አካል ለብሶ የታየው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 334 አን. 1-4)
ቁ. 4፦ ከይሖዋ ጋር ያለንን ወዳጅነት ማጠናከር የምንችለው እንዴት ነው?
መጋ. 21 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ሳሙኤል 10-13መዝ. 73 (166)
የንግግር ባሕርይ፦ ጥያቄዎችን በጥሩ ሁኔታ መጠቀም (be ገጽ 236 አን. 1-5)
ቁ. 1፦ ስለ አምላክ መንግሥት ማብራራት (be ገጽ 280 አን. 1-5)
ቁ. 2፦ 1 ሳሙኤል 10:1-12
ቁ. 3፦ ክርስቲያኖች እምነታቸውን የማይጋሩ ዘመዶቻቸውን እንዴት ሊይዟቸው ይገባል?
ቁ. 4፦ ከክርስቶስ ጋር ለመግዛት የሚነሡት እንደ እርሱ ይሆናሉ (rs ገጽ 335 አን. 1–5)
መጋ. 28 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ሳሙኤል 14-15መዝ. 76 (172)
የንግግር ባሕርይ፦ ቁልፍ የሆኑ ነጥቦችን ለማስተዋወቅ በጥያቄዎች መጠቀም (be ገጽ 237 አን. 1-2)
ቁ. 1፦ የአምላክ መንግሥት ሕይወታችንን እንዴት እንደሚነካው ማብራራት (be ገጽ 281 አን. 1-4)
ቁ. 2፦ w03 3/15 ገጽ 19-20 አን. 17-21
ቁ. 3፦ ክርስቲያኖች ግብር የሚከፍሉት ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ ትንሣኤ ለሰው ልጆች በአጠቃላይ ምን ትርጉም ይኖረዋል? (rs ገጽ 336 አን. 1–4)
ሚያ. 4 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ሳሙኤል 16-18መዝ. 10 (27)
የንግግር ባሕርይ፦ በጉዳዩ ላይ እንዲያመዛዝኑ ለመርዳት በጥያቄዎች መጠቀም (be ገጽ 237 አን. 3–ገጽ 238 አን. 2)
ቁ. 1፦ ትምህርት ለክርስቲያኖች አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (w03 3/15 ገጽ 10 አን. 1–ገጽ 11 አን. 5)
ቁ. 2፦ 1 ሳሙኤል 17:41-51
ቁ. 3፦ ከሞት የሚነሱ ሰዎች በቀድሞ ሕይወታቸው በሠሩት ነገር የማይፈረድባቸው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 337 አን. 2)
ቁ. 4፦ የምንወስዳቸው እርምጃዎች የሚያስከትሉትን ውጤት ማሰባችን መልካም የሆነውን እንድንወድና መጥፎውን እንድንጠላ ይረዳናል
ሚያ. 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ሳሙኤል 19-22መዝ. 4 (8)
የንግግር ባሕርይ፦ ስሜቱን እንዲገልጽ ለማበረታታት በጥያቄዎች መጠቀም (be ገጽ 238 አን. 3-5)
ቁ. 1፦ ወጣቶች መንፈሳዊ እድገት ማድረግ የሚችሉት እንዴት ነው? (w03 4/1 ገጽ 8-10)
ቁ. 2፦ 1 ሳሙኤል 20:24-34
ቁ. 3፦ ልክን ማወቅ ተወዳጅ ባሕርይ የሆነው ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ “የቀሩቱ ሙታን” በምድር ላይ ትንሣኤ የሚያገኙት እንዴት ነው? (rs ገጽ 337 አን. 3–ገጽ 338 አን. 3)
ሚያ. 18 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ሳሙኤል 23-25መዝ. 47 (112)
የንግግር ባሕርይ፦ አጽንኦት ለመስጠት በጥያቄዎች መጠቀም (be ገጽ 239 አን. 1-2)
ቁ. 1፦ በፍጹም ልብህ በይሖዋ ታመን (w03 11/1 ገጽ 4-7)
ቁ. 2፦ w03 5/1 ገጽ 17 አን. 11-14
ቁ. 3፦ ምድራዊ ትንሣኤ የሚያገኙት እነማን ናቸው? (rs ገጽ 338 አን. 4–ገጽ 339 አን. 4)
ቁ. 4፦ ይሖዋ ከአብርሃም ጋር ቃል ኪዳን ያደረገው ለምንድን ነው?
ሚያ. 25 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ሳሙኤል 26-31መዝ. 97 (217)
የንግግር ባሕርይ፦ የተሳሳተ አመለካከትን ለማጋለጥ በጥያቄዎች መጠቀም (be ገጽ 239 አን. 3-5)
የቃል ክለሳ
ግን. 2 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ሳሙኤል 1-3መዝ. 34 (77)
የንግግር ባሕርይ፦ ትምህርት አዘል ምሳሌዎች (be ገጽ 240 አን. 1–ገጽ 241 አን. 1)
ቁ. 1፦ የትምህርት ዓላማ ሥራ ለማግኘት ብቻ አይደለም (w03 3/15 ገጽ 11 አን. 6–ገጽ 14 አን. 6)
ቁ. 2፦ 2 ሳሙኤል 2:1-11
ቁ. 3፦ በክርስቶስ መገኘት ወቅት የሚከሰቱት ነገሮች ሲፈጸሙ በዓመታት የሚቆጠር ጊዜ ይወስዳሉ (rs ገጽ 340 አን. 1-2)
ቁ. 4፦ ሐቀኛ መሆን የሚያስገኛቸው በርካታ ጥቅሞች
ግን. 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ሳሙኤል 4-8መዝ. 82 (183)
የንግግር ባሕርይ፦ ምሳሌዎችን መጠቀም (be ገጽ 241 አን. 2-4)
ቁ. 1፦ ይሖዋ ለወጣቶች ከልብ ያስባል (w03 4/15 ገጽ 29 አን. 3–ገጽ 31 አን. 3)
ቁ. 2፦ 2 ሳሙኤል 5:1-12
ቁ. 3፦ የሕጉ ቃል ኪዳን ምን አከናውኗል?
ቁ. 4፦ የክርስቶስ መመለስ በሰብዓዊ ዓይን አይታይም (rs ገጽ 341 አን. 1-3)
ግን. 16 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ሳሙኤል 9-12መዝ. 65 (152)
የንግግር ባሕርይ፦ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ምሳሌዎች (be ገጽ 242 አን. 1-2)
ቁ. 1፦ ይሖዋ የምታደርገውን በቁም ነገር ይመለከተዋልን? (w03 5/1 ገጽ 28-31)
ቁ. 2፦ 2 ሳሙኤል 9:1-13
ቁ. 3፦ ኢየሱስ የሚመለስበት ሁኔታ፤ ዓይኖች ሁሉ የሚያዩት እንዴት ነው? (rs ገጽ 341 አን. 5–ገጽ 343 አን. 2)
ቁ. 4፦ የአምላክ ቃል ሕያው የሆነው በምን መንገድ ነው? (ዕብ. 4:12)
ግን. 23 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ሳሙኤል 13-15መዝ. 28 (58)
የንግግር ባሕርይ፦ አድማጮች ምሳሌውን በቀላሉ ይረዱታል? (be ገጽ 242 አን. 3–ገጽ 243 አን. 1)
ቁ. 1፦ ኖኅ ካሰፈረው የግል ማስታወሻ ምን ትምህርት እናገኛለን? (w03 5/15 ገጽ 4-7)
ቁ. 2፦ 2 ሳሙኤል 13:10-22
ቁ. 3፦ በዮሐንስ 11:25, 26 ላይ የሰፈረው ሐሳብ ትርጉም ምንድን ነው?
ቁ. 4፦ ከክርስቶስ መገኘት ጋር የሚዛመዱ ነገሮች (rs ገጽ 343 አን. 3-ገጽ 344 አን. 1)
ግን. 30 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ሳሙኤል 16-18መዝ. 54 (132)
የንግግር ባሕርይ፦ የተለመዱ ነገሮችን ምሳሌ አድርጎ መጠቀም (be ገጽ 244 አን. 1-2)
ቁ. 1፦ ትክክለኛ አስተሳሰብ በመያዝ የጥበብ እርምጃ ውሰዱ (w03 7/15 ገጽ 21-23)
ቁ. 2፦ w03 5/15 ገጽ 16-17 አን. 8-11
ቁ. 3፦ ክርስቲያኖች ሰንበትን የማክበር ግዴታ የለባቸውም (rs ገጽ 344 አን. 3–ገጽ 345 አን. 4)
ቁ. 4፦ ትሕትና የድክመት ምልክት አይደለም
ሰኔ 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ሳሙኤል 19-21መዝ. 74 (168)
የንግግር ባሕርይ፦ ለአድማጮችህ የሚስማሙ ምሳሌዎች (be ገጽ 244 አን. 3–ገጽ 245 አን. 4)
ቁ. 1፦ የተግሣጽን ዓላማ መረዳት (w03 10/1 ገጽ 20 አን. 1–ገጽ 21 አን. 6)
ቁ. 2፦ 2 ሳሙኤል 19:1-10
ቁ. 3፦ አንድ ክርስቲያን ወደ አምላክ እረፍት ሊገባ የሚችለው እንዴት ነው?
ቁ. 4፦ አዳም ሰንበትን እንዳከበረ የሚገልጽ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ የለም (rs ገጽ 345 አን. 5–ገጽ 346 አን. 2)
ሰኔ 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ሳሙኤል 22-24መዝ. 56 (135)
የንግግር ባሕርይ፦ የሚታዩ ነገሮችን ተጠቅሞ ማስተማር (be ገጽ 247 አን. 1-2)
ቁ. 1፦ ለመማር ፈቃደኞች ሁኑ፤ አንደበታችሁን ጠብቁ (w03 9/15 ገጽ 21 አን. 1–ገጽ 22 አን. 4)
ቁ. 2፦ 2 ሳሙኤል 24:10-17
ቁ. 3፦ ኢየሱስ የሙሴን ሕግ “የሥነ ሥርዓት” እና “የሥነ ምግባር” ሕግጋት ብሎ አልከፋፈለውም (rs ገጽ 346 አን. 3–ገጽ 347 አን. 1)
ቁ. 4፦ አንድ ክርስቲያን ከዓለም የተለየ መሆን ያለበት በምን መንገዶች ነው?
ሰኔ 20 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ነገሥት 1-2መዝ. 58 (138)
የንግግር ባሕርይ፦ ኢየሱስ በሚታዩ ነገሮች ተጠቅሞ ያስተማረው እንዴት ነው? (be ገጽ 247 አን. 3)
ቁ. 1፦ ያለኝ ይበቃኛል የማለትን ምስጢር መማር (w03 6/1 ገጽ 8-11)
ቁ. 2፦ w03 6/1 ገጽ 12-13 አን. 1-4
ቁ. 3፦ ከአሥርቱ ትእዛዛት መካከል በተለይ አሥረኛው ሕግ አስፈላጊ የነበረው ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ የሙሴ ሕግ ሲሻር አሥርቱ ትእዛዛትም ተሽረዋል (rs ገጽ 347 አን. 2-3)
ሰኔ 27 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ነገሥት 3-6መዝ. 20 (45)
የንግግር ባሕርይ፦ በሚታዩ ነገሮች ተጠቅሞ ማስተማር የሚቻለው እንዴት ነው? (be ገጽ 248 አን. 1-3)
የቃል ክለሳ
ሐምሌ 4 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ነገሥት 7-8መዝ. 23 (48)
የንግግር ባሕርይ፦ በካርታዎች፣ በትላልቅ ስብሰባዎች ፕሮግራም እንዲሁም በቪዲዮ ክሮች ተጠቅሞ ማስተማር (be ገጽ 248 አን. 4–ገጽ 249 አን. 2)
ቁ. 1፦ አረጋውያን ወንድሞችና እህቶችን አክብሩ (w03 9/1 ገጽ 30-31)
ቁ. 2፦ 1 ነገሥት 8:1-13
ቁ. 3፦ ኢየሱስ ዓለምን ያሸነፈው እንዴት ነበር?
ቁ. 4፦ አሥርቱ ትእዛዛት ቢሻሩም የሥነ ምግባር ገደቡ የማይሻረው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 348 አን. 1-2)
ሐምሌ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ነገሥት 9-11መዝ. 85 (191)
የንግግር ባሕርይ፦ በሚታዩ ነገሮች ተጠቅሞ ለብዙ አድማጮች ማስረዳት (be ገጽ 249 አን. 3–ገጽ 250 አን. 2)
ቁ. 1፦ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ እንደኖረ የሚያረጋግጥ ማስረጃ (w03 6/15 ገጽ 4-7)
ቁ. 2፦ 1 ነገሥት 9:1-9
ቁ. 3፦ ሰንበት ለክርስቲያኖች ምን ትርጉም አለው? (rs ገጽ 348 አን. 3–ገጽ 350 አን. 1)
ቁ. 4፦ የመጽሐፍ ቅዱስን መመሪያዎች በመከተል ከአደገኛ መድኃኒቶችና ዕፆች ሱስ መላቀቅ ይቻላል
ሐምሌ 18 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ነገሥት 12-14መዝ. 70 (162)
የንግግር ባሕርይ፦ አሳማኝ በሆነ መንገድ መናገር አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (be ገጽ 251 አን. 1-3)
ቁ. 1፦ አሳብ ወደ ድርጊት፤ ድርጊት ወደ ውጤት ይመራል (w03 1/15 ገጽ 30 አን. 1-3)
ቁ. 2፦ 1 ነገሥት 12:1-11
ቁ. 3፦ እምነት ፈተና ሲደርስብን በጽናት እንድንወጣ የሚረዳን እንዴት ነው?
ቁ. 4፦ መጽሐፍ ቅዱስ ቅዱሳን ብሎ የሚጠራው እነማንን ነው? (rs ገጽ 351 አን. 1-3)
ሐምሌ 25 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ነገሥት 15-17መዝ. 95 (213)
የንግግር ባሕርይ፦ ንግግራችንን ከየት እንጀምር? (be ገጽ 251 አን. 4–ገጽ 252 አን. 3)
ቁ. 1፦ ‘የጌታ ፈቃድ ምን እንደሆነ ማስተዋል’ የምንችለው እንዴት ነው? (w03 12/1 ገጽ 21 አን. 3–ገጽ 23 አን. 3)
ቁ. 2፦ w03 7/15 ገጽ 19 አን. 15-17
ቁ. 3፦ ወደ “ቅዱሳን” የማንጸልየው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 352 አን. 1-3)
ቁ. 4፦ መንፈስ ቅዱስ ክርስቲያኖችን የሚያጽናናቸው እንዴት ነው?
ነሐሴ 1 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ነገሥት 18-20መዝ. 91 (207)
የንግግር ባሕርይ፦ ምክንያታዊ መሆን የሚያስፈልግበት ጊዜ (be ገጽ 252 አን. 4–ገጽ 253 አን. 2)
ቁ. 1፦ ወጣቶች፣ ለይሖዋ እንደሚገባ ተመላለሱ (w03 10/15 ገጽ 23 አን. 1–ገጽ 24 አን. 1)
ቁ. 2፦ 1 ነገሥት 18:1-15
ቁ. 3፦ ሁሉም ክርስቲያኖች ብዙ ፍሬ ማፍራት ይችላሉ
ቁ. 4፦ ‘የቅዱሳንን’ ምስሎችና ይጠቀሙባቸው ነበር የሚባልላቸውን ዕቃዎች በተመለከተ እውነታው ምንድን ነው? (rs ገጽ 353 አን. 1–ገጽ 354 አን. 1)
ነሐሴ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ነገሥት 21-22መዝ. 42 (92)
የንግግር ባሕርይ፦ ጥያቄ መጠየቅና በምክንያት ማስረዳት (be ገጽ 253 አን. 3–ገጽ 254 አን. 2)
ቁ. 1፦ ድህነት ለዘለቄታው ይወገዳል (w03 8/1 ገጽ 4-7)
ቁ. 2፦ 1 ነገሥት 21:15-26
ቁ. 3፦ እውነተኛ ክርስቲያኖች የሆኑ ቅዱሳን ከኃጢአት የነጹ አይደሉም (rs ገጽ 354 አን. 2)
ቁ. 4፦ ደፋሮች መሆን የሚገባን ለምንድን ነው? ይህንን ባሕርይ ማዳበር የምንችለውስ እንዴት ነው?
ነሐሴ 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ነገሥት 1-4መዝ. 83 (187)
የንግግር ባሕርይ፦ በአምላክ ቃል ላይ የተመሠረተ አሳማኝ ማስረጃ ማቅረብ (be ገጽ 255 አን. 1–ገጽ 256 አን. 2)
ቁ. 1፦ በነጻ የተቀበላችሁትን በነጻ ስጡ (w03 8/1 ገጽ 20-22)
ቁ. 2፦ 2 ነገሥት 3:1-12
ቁ. 3፦ ከጥፋት ውኃ በፊት ሰዎች ለረጅም ዓመታት ይኖሩ የነበረው ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ መጽሐፍ ቅዱስ አጠቃላይ የሆነ መዳን እንደሚኖር አይናገርም (rs ገጽ 355 አን. 2)
ነሐሴ 22 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ነገሥት 5-8መዝ. 86 (193)
የንግግር ባሕርይ፦ ሐሳብህን ለመደገፍ ተጨማሪ ማስረጃዎች አቅርብ (be ገጽ 256 አን. 3-5)
ቁ. 1፦ ዘዴኛ የመሆንን ጥበብ ማዳበር (w03 8/1 ገጽ 29-31)
ቁ. 2፦ w03 8/1 ገጽ 19 አን. 18-22
ቁ. 3፦ የሰው ልጆች በሙሉ በመጨረሻ ይድናሉ? (rs ገጽ 356 አን. 1)
ቁ. 4፦ የትኞቹን የዮናስ መልካም ባሕርያት መኮረጅ እንችላለን?
ነሐሴ 29 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ነገሥት 9-11መዝ. 52 (129)
የንግግር ባሕርይ፦ በቂ ማስረጃ ማቅረብ (be ገጽ 257 አን. 1–4)
የቃል ክለሳ
መስ. 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ነገሥት 12-15መዝ. 78 (175)
የንግግር ባሕርይ፦ ልብን ለመንካት መጣር (be ገጽ 258 አን. 1-5)
ቁ. 1፦ ይሖዋን ከልብ እየፈለግኸው ነውን? (w03 8/15 ገጽ 25-28)
ቁ. 2፦ 2 ነገሥት 12:1-12
ቁ. 3፦ የዋህነትን ማዳበር ያለብን ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ ‘ሁሉም ዓይነት ሰዎች’ ይድናሉ (rs ገጽ 356 አን. 2)
መስ. 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ነገሥት 16-18መዝ. 80 (180)
የንግግር ባሕርይ፦ በአድማጮችህ ልብ ውስጥ ያለውን ሐሳብ ማስተዋል (be ገጽ 259 አን. 1-3)
ቁ. 1፦ ሰዎች ኢየሱስን የሚያስታውሱት በየትኞቹ ባሕርያቱ ነው? (w03 8/15 ገጽ 6 አን. 5–ገጽ 8 አን. 6)
ቁ. 2፦ 2 ነገሥት 16:10-20
ቁ. 3፦ መጽሐፍ ቅዱስ ፈጽሞ የማይድኑ ሰዎች እንዳሉ ይናገራል (rs ገጽ 357 አን. 1-3)
ቁ. 4፦ ጌታን ደስ የሚያሰኘውን መመርመር የምንችለው እንዴት ነው?
መስ. 19 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ነገሥት 19-22መዝ. 41 (89)
የንግግር ባሕርይ፦ የአድማጮችን ስሜት መቀስቀስ (be ገጽ 259 አን. 4–ገጽ 260 አን. 1)
ቁ. 1፦ ‘የጤናማውን ቃል ምሳሌ ያዝ’ (w03 1/1 ገጽ 29 አን. 3–ገጽ 30 አን. 4)
ቁ. 2፦ 2 ነገሥት 19:20-28
ቁ. 3፦ አንድ ጊዜ የዳነ ሰው ለሁልጊዜ ድኗል ማለት አይደለም (rs ገጽ 357 አን. 4–7)
ቁ. 4፦ በጥንቷ ሰምርኔስ ከነበሩት ክርስቲያን ወንድሞቻችን ምን ትምህርት እናገኛለን?
መስ. 26 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ነገሥት 23-25መዝ. 24 (50)
የንግግር ባሕርይ፦ ሰዎች ፈሪሃ አምላክ እንዲያዳብሩ መርዳት (be ገጽ 260 አን. 2-3)
ቁ. 1፦ መጽሐፍ ቅዱስና በውስጡ የተካተቱት ቅዱሳን መጻሕፍት ዝርዝር—ክፍል 1 (si ገጽ 299 አን. 1-6)
ቁ. 2፦ w03 8/15 ገጽ 20 አን. 6-10
ቁ. 3፦ ስለ ወደፊቱ ጊዜ ብሩሕ ተስፋ አለን
ቁ. 4፦ እምነት በሥራ መደገፍ ያለበት ለምንድን ነው? (rs ገጽ 357 አን. 8-358 አን. 3)
ጥቅ. 3 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ዜና መዋዕል 1-4መዝ. 9 (26)
የንግግር ባሕርይ፦ አምላክ በምናደርገው ነገር ያዝናል ወይም ይደሰታል (be ገጽ 260 አን. 4–5)
ቁ. 1፦ መጽሐፍ ቅዱስና በውስጡ የተካተቱት ቅዱሳን መጻሕፍት ዝርዝር—ክፍል 2 (si ገጽ 300-302 አን. 7-16)
ቁ. 2፦ 1 ዜና መዋዕል 4:24-43
ቁ. 3፦ ዲያብሎስ መኖሩን እንዴት እርግጠኞች መሆን እንችላለን? (rs ገጽ 360 አን. 1–ገጽ 361 አን. 1)
ቁ. 4፦ ይሖዋ በግለሰብ ደረጃ ይወደናል
ጥቅ. 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ዜና መዋዕል 5-7መዝ. 87 (195)
የንግግር ባሕርይ፦ ሰዎች ራሳቸውን እንዲመረምሩ መርዳት (be ገጽ 261 አን. 1-3)
ቁ. 1፦ መጽሐፍ ቅዱስና በውስጡ የተካተቱት ቅዱሳን መጻሕፍት ዝርዝር—ክፍል 3 (si ገጽ 302-305 አን. 17-26)
ቁ. 2፦ 1 ዜና መዋዕል 5:18-26
ቁ. 3፦ ስለ ‘እግዚአብሔር ቀን’ ምን የምናውቀው ነገር አለ?
ቁ. 4፦ ሰይጣን በሰዎች ውስጥ ያለ የክፋት ባሕርይ አይደለም (rs ገጽ 361 አን. 2–ገጽ 362 አን. 1)
ጥቅ. 17 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ዜና መዋዕል 8-11መዝ. 89 (201)
የንግግር ባሕርይ፦ ሰዎች በሙሉ ልብ የማገልገል ዝንባሌ እንዲያዳብሩ መርዳት (be ገጽ 261 አን. 4-ገጽ 262 አን. 2)
ቁ. 1፦ የቅዱሳን ጽሑፎች የዕብራይስጥ ጽሑፍ—ክፍል 1 (si ገጽ 305-306 አን. 1-5)
ቁ. 2፦ 1 ዜና መዋዕል 10:1-14
ቁ. 3፦ ዲያብሎስ የመጣው ከየት ነው? (rs ገጽ 362 አን. 2)
ቁ. 4፦ ዘዴኛ መሆን የሚገባን ከእነማን ጋር ባለን ግንኙነት ነው?
ጥቅ. 24 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ዜና መዋዕል 12-15መዝ. 79 (177)
የንግግር ባሕርይ፦ የሰዎችን ልብ በመንካት ረገድ ከይሖዋ ጋር መተባበር (be ገጽ 262 አን. 3)
ቁ. 1፦ የቅዱሳን ጽሑፎች የዕብራይስጥ ጽሑፍ—ክፍል 2 (si ገጽ 306-307 አን. 6-9)
ቁ. 2፦ w03 11/1 ገጽ 10-11 አን. 10-13
ቁ. 3፦ በይሖዋ ስም መሄድ ሲባል ምን ማለት ነው?
ቁ. 4፦ ሰይጣን እንዳመፀ አምላክ ወዲያው ያላጠፋው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 362 አን. 3–ገጽ 363 አን. 1)
ጥቅ. 31 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ዜና መዋዕል 16-20መዝ. 52 (129)
የንግግር ባሕርይ፦ በሰዓቱ መጨረስ (be ገጽ 263 አን. 1–ገጽ 264 አን. 4)
የቃል ክለሳ
ኅዳር 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ዜና መዋዕል 21-25መዝ. 96 (215)
የንግግር ባሕርይ፦ ልብ የሚነካ ምክር (be ገጽ 265 አን. 1-3)
ቁ. 1፦ የቅዱሳን ጽሑፎች የዕብራይስጥ ጽሑፍ—ክፍል 3 (si ገጽ 307-310 አን. 10-16)
ቁ. 2፦ 1 ዜና መዋዕል 22:1-10
ቁ. 3፦ የዲያብሎስን ኃይል አቅልለህ አትመልከት (rs ገጽ 363 አን. 2–ገጽ 364 አን. 1)
ቁ. 4፦ *የጋብቻን ጥምረት ማጠናከር የሚቻለው እንዴት ነው?
ኅዳር 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ዜና መዋዕል 26-29መዝ. 15 (35)
የንግግር ባሕርይ፦ ምክር የምንሰጠው በፍቅር መሆን አለበት (be ገጽ 266 አን. 1-4)
ቁ. 1፦ የቅዱሳን ጽሑፎች የዕብራይስጥ ጽሑፍ—ክፍል 4 (si ገጽ 310-312 አን. 17-25)
ቁ. 2፦ 1 ዜና መዋዕል 29:1-9
ቁ. 3፦ የይሖዋ አገልጋዮች የሚሰደዱት ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ ከሰይጣን ክፉ ተጽዕኖ የምንገላገልበት ጊዜ ቀርቧል (rs ገጽ 364 አን. 3–ገጽ 365 አን. 2)
ኅዳር 21 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ዜና መዋዕል 1-5መዝ. 21 (46)
የንግግር ባሕርይ፦ በቅዱሳን ጽሑፎች ላይ የተመሠረተ ምክር (be ገጽ 267 አን. 1-2)
ቁ. 1፦ የቅዱሳን ጽሑፎች የዕብራይስጥ ጽሑፍ—ክፍል 5 (si ገጽ 312-314 አን. 26-31)
ቁ. 2፦ 2 ዜና መዋዕል 2:1-10
ቁ. 3፦ የተግሣጽን ዓላማ መገንዘብ
ቁ. 4፦ aየጾታ ግንኙነት በአጠቃላይ ኃጢአት ነው? (rs ገጽ 366 አን. 1–ገጽ 367 አን. 1)
ኅዳር 28 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ዜና መዋዕል 6-9መዝ. 45 (106)
የንግግር ባሕርይ፦ ‘የመናገር ድፍረት’ ይኑራችሁ (be ገጽ 267 አን. 3-4)
ቁ. 1፦ የቅዱሳን ጽሑፎች የግሪክኛ ጽሑፍ—ክፍል 1 (si ገጽ 315-316 አን. 1-7)
ቁ. 2፦ w03 12/1 ገጽ 15-16 አን. 3-6
ቁ. 3፦ በይሖዋ ደስ እንደሚለን እንዴት ማሳየት እንችላለን?
ቁ. 4፦ bመጽሐፍ ቅዱስ ስለ ግብረ ሰዶም ምን ይላል? (rs ገጽ 367 አን. 3–5)
ታኅ. 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ዜና መዋዕል 10-14መዝ. 66 (155)
የንግግር ባሕርይ፦ ንግግራችን የሚያበረታታ መሆኑ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (be ገጽ 268 አን. 1-3)
ቁ. 1፦ የቅዱሳን ጽሑፎች የግሪክኛ ጽሑፍ—ክፍል 2 (si ገጽ 316-317 አን. 8-16)
ቁ. 2፦ 2 ዜና መዋዕል 12:1-12
ቁ. 3፦ ይገባናል የማንለው የአምላክ ደግነት የሚያስፈልገን ለምንድን ነው?
ቁ. 4፦ አምላክን ማስደሰት የሚፈልጉ ሰዎች ሊያደርጓቸው የሚገቡ ለውጦች (rs ገጽ 368 አን. 1-3)
ታኅ. 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ዜና መዋዕል 15-19መዝ. 27 (57)
የንግግር ባሕርይ፦ ሰዎች ይሖዋ ያደረጋቸውን ነገሮች መለስ ብለው እንዲያስቡ ማድረግ (be ገጽ 268 አን. 4–ገጽ 269 አን. 1)
ቁ. 1፦ የቅዱሳን ጽሑፎች የግሪክኛ ጽሑፍ—ክፍል 3 (si ገጽ 317-319 አን. 17-25)
ቁ. 2፦ 2 ዜና መዋዕል 19:1-11
ቁ. 3፦ ፍጹም የሆነ ሰው እንዴት ኃጢአት ሊሠራ ይችላል? (rs ገጽ 370 አን. 1–ገጽ 371 አን. 1)
ቁ. 4፦ ከኢየሱስ ቤተሰብ ምን መማር እንችላለን?
ታኅ. 19 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ዜና መዋዕል 20-24መዝ. 29 (62)
የንግግር ባሕርይ፦ ይሖዋ ሕዝቡን እንዴት እንደረዳ መግለጽ (be ገጽ 269 አን. 2-4)
ቁ. 1፦ የቅዱሳን ጽሑፎች የግሪክኛ ጽሑፍ—ክፍል 4 (si ገጽ 319-320 አን. 26-32)
ቁ. 2፦ w03 12/15 ገጽ 16-17 አን. 13-15
ቁ. 3፦ ያለኝ ይበቃኛል የማለትን ምስጢር መማር የሚያስገኛቸው ጥቅሞች
ቁ. 4፦ ኃጢአት የሚባል ነገር መኖሩን የምንቀበለው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 371 አን. 3–ገጽ 372 አን. 3)
ታኅ. 26 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ዜና መዋዕል 25-28መዝ. 36 (81)
የንግግር ባሕርይ፦ አምላክ እያደረገልን ባለው ነገር እንደምንደሰት ማሳየት (be ገጽ 269 አን. 5–ገጽ 271 አን. 1)
የቃል ክለሳ
[የግርጌ ማስታወሻዎች]
a ለወንድሞች ብቻ የሚሰጥ።
b የተቃውሞ ሐሳብ ለሚሰነዝሩ ሰዎች የሚሆኑ መልሶችን ስታቀርብ ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ለአካባቢው ይበልጥ ተስማሚ በሆኑት ላይ አተኩር።