የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ነሐሴ 14 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 71 (163)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የሐምሌ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የሐምሌ 2006 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ ውይይቱን ለማስቆም “የይሖዋ ምሥክሮችን አልፈልግም” ለሚል ሰው ምን መልስ መስጠት እንደሚቻል የሚያሳይ ይሁን።—ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 17-18ን ተመልከት።
12 ደቂቃ:- “የታማኝነት ምሳሌ ትተዋል።” በንግግር የሚቀርብ። ልዩ አቅኚዎችን አስመልክቶ በጽሑፎቻችን ላይ ከወጡ ተሞክሮዎች መካከል ጥቂቶቹን መርጠህ ተናገር፤ ወይም በጉባኤው ውስጥ እያገለገሉ ላሉ ልዩ አቅኚዎች ቃለ ምልልስ አድርግ።—ከመጠበቂያ ግንብ ጽሑፎች ማውጫ ላይ “Special Pioneers” የሚለውን ተመልከት።
23 ደቂቃ:- የትምህርት ቤት ጓደኝነት ገደቡ እስከ ምን ድረስ መሆን አለበት? በሚያዝያ 2006 ንቁ! መጽሔት ከገጽ 17-19 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ከአድማጮች መካከል በክርስቲያን ቤተሰብ ውስጥ ያደጉ ወጣቶች፣ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ተቋቁመው በትምህርት ቤት ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓት በሥራ ላይ ማዋል እንዲችሉ ወላጆቻቸው የረዷቸው እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ ጋብዝ። ሐሳብ የሚሰጡ አንድ ወይም ሁለት ወጣቶች አስቀድመህ ልታዘጋጅ ትችላለህ።
መዝሙር 72 (164) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ነሐሴ 21 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 29 (62)
8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎችና ከመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 3 እና 4 ላይ የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
12 ደቂቃ:- ከመጠበቂያ ግንብ ጥናት እና ከሕዝብ ስብሰባ ጥቅም ማግኘት። የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ከገጽ 59 እስከ ገጽ 64 ንዑስ ርዕሱ ድረስ ባለው ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።
25 ደቂቃ:- ረዳት አቅኚ ለመሆን ከአሁኑ እቅድ አውጡ! በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በአዲሱ የአገልግሎት ዓመት ቢያንስ ለአንድ ወር ረዳት አቅኚ ሆነው ለማገልገል ግብ እንዲያወጡ አበረታታ። (1 ቆሮ. 9:26) አንዳንዶች ልዩ እንቅስቃሴ በሚደረግባቸው ወይም ሕዝባዊ በዓላት አሊያም አምስት ቅዳሜና እሁዶች ባሏቸው እንደ መስከረም፣ ጥር፣ ሚያዝያና ግንቦት ባሉ ወራት ረዳት አቅኚ ሆነው ለማገልገል ይመርጡ ይሆናል። አድማጮችን እነዚህን ጥያቄዎች ጠይቅ:- “ከዚህ ቀደም ረዳት አቅኚ ሆናችሁ ለማገልገል ስትሉ እንቅፋቶችን የተወጣችሁት እንዴት ነው? ረዳት አቅኚ ሆናችሁ በማገልገላችሁ ምን በረከት አግኝታችኋል? ረዳት አቅኚ ሆኖ የማገልገል ፍላጎት ኖሯችሁ የሚሳካላችሁ መሆኑን ከተጠራጠራችሁ ጉዳዩን በጸሎት ለይሖዋ መንገራችሁ ጥሩ የሚሆነው ለምንድን ነው? (ሥራ 4:29፤ 2 ቆሮ. 4:7፤ ያዕ. 1:5) በዚህ ጉዳይ ላይ ከቤተሰባችሁና ከጉባኤያችሁ አባላት ጋር በተለይ ደግሞ ከእናንተ ጋር በሚመሳሰል ሁኔታ ውስጥ ካሉ አስፋፊዎች ጋር መወያየታችሁ ጥሩ የሆነው ለምንድን ነው? (ምሳሌ 15:22) ረዳት አቅኚ ሆናችሁ ማገልገል የምትፈልጉት መቼ ነው?”
መዝሙር 66 (155) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ነሐሴ 28 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 43 (98)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። አስፋፊዎች የነሐሴ ወር ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በገጽ 4 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆነ ሌላ አቀራረብ በመጠቀም የሐምሌ 15 መጠበቂያ ግንብ እና የሐምሌ 2006 ንቁ! መጽሔቶችን ለመጽሔት ደንበኛ ተመላልሶ መጠየቅ በሚደረግበት ወቅት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
15 ደቂቃ:- የብርታት ምንጭ መሆን ትችላላችሁ። (ሮሜ 1:11, 12) በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በጉባኤያችሁ ውስጥ ስንት የዘወትር አቅኚዎች እንደሚገኙ ተናገር። በማመስገን፣ አቅኚነት ያለውን ጥቅም በመናገር፣ አብረናቸው በማገልገል፣ ምግብ በመጋበዝና በትራንስፖርት ወጪ ረገድ በመደገፍ አቅኚዎችን ማበረታታት እንደምንችል ጥቀስ። የዘወትር አቅኚዎች በሌሎች እንዴት እንደተበረታቱ ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ። ጉባኤው የዘወትር አቅኚዎች ከሌሉት ረዳት አቅኚ ሆነው እያገለገሉ ያሉትን እንዴት ማበረታታት እንደሚቻል ተወያዩበት።
20 ደቂቃ:- በመስከረም ወር ጥናት ለማስጀመር ግብ ልታወጡ ትችላላችሁ? በንግግርና በሠርቶ ማሳያ የሚቀርብ። በመስከረም ወር፣ ሰዎችን በምናነጋግርበት በመጀመሪያው ቀን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በተባለው መጽሐፍ አማካኝነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ልዩ ጥረት እናደርጋለን። ይህም ሲባል መጽሐፉን በምናበረክትበት ወቅት ከቤቱ ባለቤት ጋር ጥቂት አንቀጾችን ለመወያየት ጥረት እናደርጋለን ማለት ነው። ለአገልግሎት ክልሉ የሚስማሙ ርዕሰ ጉዳዮችን በመጠቀም ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። በእያንዳንዱ ሠርቶ ማሳያ ላይ ተመላልሶ መጠየቅ በማድረግ ውይይቱን ለመቀጠል ቁርጥ ያለ ቀጠሮ እንዴት መያዝ እንደሚቻል አሳይ።
መዝሙር 16 (37) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 4 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 23 (48)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ:- “‘መዳናችን ቀርቧል!’ የተባለውን የአውራጃ ስብሰባ ለማስተዋወቅ የሚደረግ ዓለም አቀፍ ዘመቻ።” (የሚያዝያ 2006 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 5ን ተመልከት።) ሁሉንም አንቀጾች አንብባቸው።
20 ደቂቃ:- “ያለ አድልዎ በመስበክ ለሰዎች ልባዊ አሳቢነት አሳዩ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በአንቀጽ ሁለት መጨረሻ ላይ የተጠቀሰውን ሮሜ 1:14ን ስትወያዩበት ጠለቅ ብሎ ማስተዋል (እንግሊዝኛ) ከተባለው መጽሐፍ ጥራዝ 1 ገጽ 255 ላይ “Barbarian” (ባርቤርያን) በሚለው ርዕስ የመጀመሪያ አንቀጽ ውስጥ ያለውን ሐሳብ አክለህ አቅርብ። አንቀጽ 3 ላይ ከተወያያችሁ በኋላ ለሰዎች ሁሉ የሚሆን ምሥራች (እንግሊዝኛ) ከተባለው ቡክሌት ገጽ 2 ላይ የተጠቀሱትን ሦስት ነጥቦች ከልስ። እንዲሁም በጉባኤው የአገልግሎት ክልል ውስጥ የሚገኙ የውጭ አገር ዜጎችን ለማነጋገር ቡክሌቱን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 49 (114) እና የመደምደሚያ ጸሎት።