የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/07 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ሚያዝያ 9 የሚጀምር ሳምንት
  • ሚያዝያ 16 የሚጀምር ሳምንት
  • ሚያዝያ 23 የሚጀምር ሳምንት
  • ሚያዝያ 30 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 7 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
km 4/07 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ሚያዝያ 9 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 89 (201)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች “በመከራ በተሞላው በዚህ ዓለም ውስጥ ያለ ስጋት መኖር ትችላላችሁ!” በሚል ርዕስ እሁድ ዕለት በሚቀርበው ልዩ የሕዝብ ንግግር ላይ እንዲገኙ ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች እንዲጋብዙ አስታውሳቸው። ሁሉም በሚቀጥለው ሳምንት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለምንወስደው ክፍል የወጣቶች ጥያቄ—ሕይወቴን እንዴት ብጠቀምበት ይሻላል? የሚል ርዕስ ባለው ዲቪዲ ላይ ያለውን ድራማ አይተው እንዲመጡ አበረታታ። ዲቪዲው ዋና ማውጫ (Main Menu) እንዳለው ግለጽና በዚህ አማካኝነት በዲቪዲው ላይ የተካተቱትን የተለያዩ ክፍሎች እንዴት ማየት እንደሚቻል አብራራ። በገጽ 8 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የመጋቢት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የመጋቢት 2007 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ አስፋፊው በተመላልሶ መጠየቅ ወቅት መልስ የሚሰጥበትን ጥያቄ ሲጠይቅ የሚያሳይ ይሁን።

15 ደቂቃ:- “አዳዲስ ደቀ መዛሙርትን በማፍራቱ ሥራ ሁሉም አስተዋጽኦ ማበርከት ይችላል።”* በአንቀጽ 4 ላይ ስትወያዩ ወንድሞችና እህቶች ከመጠመቃቸው በፊት የጉባኤው አባላት እንዴት እንዳበረታቷቸው እንዲናገሩ ጋብዝ። ሐሳብ የሚሰጡ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎችን ቀደም ብለህ ማዘጋጀት ትችላለህ።

20 ደቂቃ:- “በዓመፃ ገንዘብ ወዳጆችን አብጁ” በሚለው ክፍል ከአንቀጽ 1 እስከ 14 ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። አንደኛ ዜና መዋዕል 29:14, 17ን አንብብ። አንቀጽ 10 ላይ ስለተጠቀሰው መበለቲቱ ስላደረገችው መዋጮ ሐሳብ ስጥ። በዚህ ክፍል ቀሪ አንቀጾች ላይ የዛሬ ሁለት ሳምንት ውይይት እንደሚደረግ ተናገር።

መዝሙር 19 (43) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሚያዝያ 16 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 58 (138)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የተመረጡ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ።

15 ደቂቃ:- “የአምላክን ቃል ያለ ፍርሃት ተናገር።”* ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ በተጠቀሱ ጥቅሶች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ።

n20 ደቂቃ:- “በሕይወታችሁ ምን ለማድረግ አስባችኋል?”—ክፍል 1።* በአንቀጽ 1 እና 2 ላይ ተመሥርተህ አጭር የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ ለአንቀጽ 3 እና 4 በቀረቡት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ። አንቀጽ 3 ውስጥ በሚገኘው ጥያቄ 4 ላይ ስትደርሱ ሁለቱም ጥቅሶች እንዲነበቡ አድርግ። መደምደሚያህ ላይ ዋና ማውጫውን (Main Menu) በተመለከተ ሐሳብ ስጥ። ሁሉም በሚቀጥለው ሳምንት የአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለምንወስደው ክፍል በዲቪዲው ላይ ያለውን “Interviews” (ቃለ ምልልስ) እና “Supplementary Material” (ተጨማሪ ክፍል) የሚሉትን አይተው እንዲመጡ አበረታታ።

መዝሙር 91 (207) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሚያዝያ 23 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 96 (215)

8 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የመጋቢት 15 መጠበቂያ ግንብ እና የሚያዝያ 2007 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።

17 ደቂቃ:- “በዓመፃ ገንዘብ ወዳጆችን አብጁ” በሚለው ክፍል ከአንቀጽ 15 እስከ 23 ላይ ተመሥርቶ የሚደረግ ውይይት። ክፍሉን አንድ ሽማግሌ ያቀርበዋል። መዋጮ ማድረግን በተመለከተ ሊኖረን ስለሚገባው ተገቢ አመለካከት ጎላ አድርገህ ተናገር።

20 ደቂቃ:- “በሕይወታችሁ ምን ለማድረግ አስባችኋል?”—ክፍል 2።* ከአንቀጽ 5-7 ላይ በቀረቡት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ። ክፍሉን አንቀጽ 8 ላይ በሚገኘው ማሳሰቢያ መሠረት ሞቅ ባለ ስሜት ደምድም።

መዝሙር 76 (172) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሚያዝያ 30 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 7 (19)

12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የሚያዝያ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በጥቅምት 1999 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 7 ላይ “የመኖሪያ ቦታ ልትቀይር ነውን?” በሚለው ርዕስ ሥር ያሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ከልስ። እንዲሁም በግንቦት 1999 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 2 ላይ ባለው የጥያቄ ሣጥን ውስጥ የሚገኙትን ጠቃሚ ነጥቦች ጨምረህ አቅርብ።

13 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

20 ደቂቃ:- በመንፈሳዊ በደንብ ትመገባለህ? በሚያዝያ 15, 1997 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 28-31 ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። የክለሳ ጥያቄዎችን አዘጋጅ።

መዝሙር 22 (47) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ግንቦት 7 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 72 (164)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ:- ለአምልኮ ቦታዎች የሚደረጉ ዝግጅቶች። የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 11 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።

20 ደቂቃ:- “ሰዎች ቤታቸው ባይገኙ ምን ማድረግ እንችላለን?”* በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ።

መዝሙር 43 (98) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

[የግርጌ ማስታወሻዎች ]

አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ