መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ጥር 1
“አምላክ አካባቢያችን እየተበላሸ መሄዱ የሚያሳስበው ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው፤ ከዚያም ራእይ 11:18ን አንብብ።] ይህ ርዕስ ስለ ምድራችን የወደፊት ሁኔታ ብሩህ አመለካከት እንዲኖረን የሚያደርጉ ቅዱስ ጽሑፋዊ ምክንያቶችን ይዟል።” ገጽ 18 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አሳየው።
ንቁ! ጥር 2009
“ብዙ ሰዎች መከራ ሲደርስባቸው አምላክ እየቀጣቸው እንደሆነ ይሰማቸዋል። እርስዎስ እንደዚህ ተሰምቶዎት ያውቃል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው፤ ከዚያም ያዕቆብ 1:13ን አንብብ።] ይህ ርዕስ የችግሮቻችን ትክክለኛ መንስኤ ምን እንደሆነና የሚደርሱብን መከራዎች በቅርቡ እንደሚወገዱ ሙሉ በሙሉ መተማመን የምንችለው ለምን እንደሆነ ይገልጻል።” ገጽ 28 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አሳየው።
መጠበቂያ ግንብ የካቲት 1
“ሁሉም ሃይማኖቶች በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ኢየሱስ በዚህ ጥቅስ ላይ የተናገረውን ሐሳብ ልብ ይበሉ። [ማቴዎስ 15:8, 9ን አንብብ።] ይህ ርዕስ ሁሉም የአምልኮ ዓይነቶች በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ይኖራቸው እንደሆነና እንዳልሆነ ያብራራል።” ገጽ 9 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አሳየው።
ንቁ! የካቲት 2009
“ምድርን በተመለከተ የተደረሰባቸው ነገሮች በሙሉ ምድር ለሕይወት የምትመች ሆና መሠራቷን የሚጠቁሙ ናቸው። ይህ ሁኔታ እንዲሁ በአጋጣሚ የሆነ ይመስልዎታል ወይስ ፈጣሪ እንዳለው የሚያሳይ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ብዙ ሰዎች ከዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ጋር ይስማማሉ። [መዝሙር 104:24ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ፈጣሪ መኖሩን የሚያሳዩ ሳይንሳዊና ቅዱስ ጽሑፋዊ ማስረጃዎችን ይዟል።”