ነሐሴ 2 የሚጀምር ሳምንት
ነሐሴ 2 የሚጀምር ሳምንት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ነገሥት 18-20
ቁ. 1፦ 1 ነገሥት 18:21-29
ቁ. 2፦ ሰማይና ምድር ያልፋሉ ሲባል ምን ማለት ነው? (ራእይ 21:1)
ቁ. 3፦ ልናስወግዳቸው የሚገቡን በራስ የመመራት ዝንባሌዎች የትኞቹ ናቸው? (rs ገጽ 190 አን. 3 እስከ ገጽ 191 አን. 3)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ አገልግሎትህን ማስፋት የምትችልባቸው መንገዶች—ክፍል 4። የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ገጽ 116 አንቀጽ 1-4 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። በመንግሥት አዳራሽ ግንባታ ለተሳተፉ ወይም በቤቴል ላገለገሉ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች ከዚህ የአገልግሎት ዘርፍ በጣም የወደዱት ምኑን እንደሆነ ቃለ ምልልስ አድርግላቸው።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን በማስጀመር ረገድ የተገኙ ተሞክሮዎች። ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲጀምሩ በምንጋብዝበት ልዩ ቀን በክልላችሁ ውስጥ ስለተከናወኑ ነገሮች ተናገር። አድማጮች ያገኙትን ተሞክሮ እንዲናገሩ ጋብዝ። አንድ ወይም ሁለት ግሩም ተሞክሮዎችን በሠርቶ ማሳያ መልክ እንዲቀርቡ ማድረግ ትችላለህ። ሰዎችን በምናነጋግርበት በመጀመሪያው ቀን እንዴት ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ በማድረግ ክፍልህን ደምድም።