የካቲት 28 የሚጀምር ሳምንት
የካቲት 28 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 5 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
dp ምዕ. 9 አን. 20-27 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ አስቴር 1-5 (10 ደቂቃ)
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ (20 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ መልእክቱ ምንጊዜም አዎንታዊ እንዲሆን አድርጉ። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 202 ከአንቀጽ 1-3 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። አንድ አስፋፊ አንቀጽ 3 ላይ በተሰጠው ሐሳብ ላይ ተመርኩዞ በሚቀጥለው ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ሲያበረክት የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር ከተባለው ቡክሌት ጥቅም ማግኘት። ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር—2011 በተባለው ቡክሌት መቅድም ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። ሁሉም በየቀኑ የዕለት ጥቅስ እንዲያነቡ አበረታታ። የዕለቱን ጥቅስ ስለሚያነቡበት ፕሮግራምና እንዲህ ማድረጋቸው ያስገኘላቸውን ጥቅም እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ። በ2011 የዓመት ጥቅስ ላይ አጠር ያለ ሐሳብ ስጥ። “ከአሁን በኋላ የመስክ ስምሪት ስብሰባዎችን ለመምራት በዕለት ጥቅስ አንጠቀምም” በሚለው ላይ ውይይት አድርጉ።
10 ደቂቃ፦ በመጋቢት ወር መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። በውይይት የሚቀርብ። በአንድ ወይም በሁለት ደቂቃዎች ውስጥ የመጽሔቶቹን አንዳንድ ርዕሰ ትምህርቶች ከልስ። ከዚያም ሁለት ወይም ሦስት ርዕሰ ትምህርቶችን ምረጥና እነዚህን ርዕሶች ተጠቅሞ መጽሔቶቹን ለማስተዋወቅ ምን ጥያቄ ማንሳት እንዲሁም የትኛውን ጥቅስ ማንበብ እንደሚችሉ አድማጮችን ጠይቅ። እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 33 እና ጸሎት