ግንቦት 23 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ግንቦት 23 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 39 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
dp ምዕ. 12 አን. 16-22 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መዝሙር 19-25 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ መዝሙር 23:1 እስከ 24:10 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ወደፊት አይሁዳውያን በሙሉ ተለውጠው በክርስቶስ ያምናሉ?—rs ገጽ 223 አን. 2-3 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ሮም 8:21 ፍጻሜውን የሚያገኘው እንዴትና መቼ ነው? (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች። “እባካችሁ ተከታትላችሁ እርዱት (S-43) የተባለውን ቅጽ እንዴት ልንጠቀምበት ይገባል?” በውይይት የሚቀርብ።
10 ደቂቃ፦ ውጤታማ መግቢያዎች ያላቸው ሦስት ገጽታ። በማመራመር መጽሐፍ ገጽ 9 አንቀጽ 1 ላይ ተመሥርቶ በንግግር የሚቀርብ። በአንቀጹ ላይ ከተወያያችሁ በኋላ በሰኔ ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ እንዴት ማስተዋወቅ እንደሚቻል የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
15 ደቂቃ፦ ሞክራችሁታል? በውይይት የሚቀርብ። በቅርቡ በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ በወጡት በሚከተሉት ርዕሶች ውስጥ የተሰጡትን ሐሳቦች በንግግር መልክ በአጭሩ ከልስ፦ “በምታገኙት አጋጣሚ ሁሉ ተጠቀሙበት” (km 12/10) እንዲሁም “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አዲስ አምድ” እና “ቤተሰቦችን ለመርዳት የተደረገ ዝግጅት” (km 1/11)። አድማጮች በእነዚህ ርዕሶች ላይ የቀረቡትን ሐሳቦች እንዴት በተግባር ላይ እንዳዋሉና ምን ጥቅም እንዳገኙ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።
መዝሙር 6 እና ጸሎት