መጋቢት 24 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መጋቢት 24 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 9 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
jl ትምህርት 14-16 (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 47-50 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘፍጥረት 48:17 እስከ 49:7 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ በክርስቶስ መገኘት ጊዜ የሚከሰቱት ነገሮች በዓመታት የሚቆጠር ጊዜ ይፈጃሉ—rs ገጽ 340 አን. 1-2 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ አቢሜሌክ—ትዕቢት ለውድቀት ይዳርጋል—w08 2/15 ገጽ 9 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ የነህምያን ምሳሌ ተከተሉ። በውይይት የሚቀርብ። የነህምያን ምሳሌ መከተላችን የወንጌላዊነት ሥራችንን ስናከናውን የሚጠቅመን እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
10 ደቂቃ፦ በጥያቄዎች ተጠቅሞ ጥሩ አድርጎ ማስተማር—ክፍል 1። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 236 እስከ ገጽ 237 አንቀጽ 2 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። ከቀረቡት ነጥቦች መካከል ቢያንስ አንዱን በመጠቀም አንድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ የይሖዋ ጆሮዎች የጻድቃንን ምልጃ ለመስማት የተከፈቱ ናቸው። (1 ጴጥ. 3:12) በ2013 የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) ገጽ 66 ከአንቀጽ 1-3 እና ከገጽ 104-105 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። አድማጮች ምን ትምህርት እንዳገኙ ጠይቅ።
መዝሙር 6 እና ጸሎት