ሚያዝያ 14 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሚያዝያ 14 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 37 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
jl ትምህርት 23-25 (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፀአት 11-14 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘፀአት 12:37-51 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ከክርስቶስ መገኘት ጋር የሚያያዙት አንዳንድ ክንውኖች ምንድን ናቸው?—rs ገጽ 343 አን. 3 እስከ ገጽ 344 አን. 1) (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ጦርነት—አምላክ ጦርነቶችን ይደግፋል?—g 8/11 ገጽ 22-23 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
15 ደቂቃ፦ የ2014 የዓመት መጽሐፍን በጥሩ ሁኔታ ተጠቀሙበት። በውይይት የሚቀርብ። “ከበላይ አካል የተላከ ደብዳቤ” የሚለውን ከልስ። ከዓመት መጽሐፉ ላይ አበረታች ሆኖ ያገኙትን ተሞክሮ በአጭሩ እንዲናገሩ ጥቂት አስፋፊዎችን አስቀድመህ አዘጋጅ። በተጨማሪም አድማጮች ከዓለም አቀፉ ሪፖርት ላይ ያስደነቃቸውን ነገር እንዲናገሩ ጋብዝ። ሁሉም የዓመት መጽሐፉን ከዳር እስከ ዳር እንዲያነቡ በማበረታታት ክፍሉን ደምድም።
15 ደቂቃ፦ “በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ጥሩ የአገልግሎት ጓደኛ ሁኑ።” በውይይት የሚቀርብ። ጥሩ ረዳት ያልሆነ የአገልግሎት ጓደኛ ምን እንደሚያደርግ የሚያሳዩ ሁለት አጫጭር ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ከእያንዳንዱ ሠርቶ ማሳያ በኋላ የአገልግሎት ጓደኛው ምን ቢያደርግ የተሻለ ይሆን እንደነበር እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
መዝሙር 45 እና ጸሎት