በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ጥሩ የአገልግሎት ጓደኛ ሁኑ
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? በምንሰብክበት ወቅት የአገልግሎት ጓደኛ መኖሩ ጠቃሚ እንደሆነ ኢየሱስ ተገንዝቦ ነበር። በመሆኑም 70ዎቹን ለስብከት ሲልካቸው ሁለት ሁለት አድርጎ መድቧቸዋል። (ሉቃስ 10:1) አንድ የአገልግሎት ጓደኛ፣ አብሮት የሚያገለግለው አስፋፊ አስቸጋሪ ሁኔታ ሲያጋጥመው ወይም ለቤቱ ባለቤት ምን መልስ መስጠት እንዳለበት እርግጠኛ በማይሆንበት ጊዜ ሊረዳው ይችላል። (መክ. 4:9, 10) በተጨማሪም በወንጌላዊነቱ ሥራ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ተሞክሮውን ሊያካፍለው ወይም አልፎ አልፎ ጠቃሚ ሐሳቦችን ሊነግረው ይችላል። (ምሳሌ 27:17) እንዲሁም ከአንዱ ቤት ወደ ሌላው ሲሄዱ የሚያንጽ ጭውውት በማድረግ ሊያበረታታው ይችላል።—ፊልጵ. 4:8
በዚህ ወር እንዲህ ለማድረግ ሞክሩ፦
አገልግሎት ከጨረሳችሁ በኋላ የአገልግሎት ጓደኛችሁ የተናገረውን ወይም ያደረገውን ነገር ጠቅሳችሁ እንዴት ጥሩ ረዳት እንደሆነላችሁ ግለጹለት።