በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—መግቢያ ማዘጋጀት
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? መግቢያችን የመስማት ፍላጎት የሚቀሰቅስ ካልሆነ የምናነጋግረው ሰው ምሥራቹን ሳንነግረው ውይይቱን ሊያቋርጥ ይችላል። በመሆኑም ብዙ አስፋፊዎች በመግቢያቸው ላይ የሚናገሩት የመጀመሪያ ሐሳብ በጣም ወሳኝ እንደሆነ ይሰማቸዋል። የአቀራረብ ናሙናዎችን በመንግሥት አገልግሎታችን እና በማመራመር መጽሐፍ ላይ ማግኘት የሚቻል ቢሆንም እነዚህ አቀራረቦች ሁልጊዜ የተሟላ የመግቢያ ሐሳብ ይይዛሉ ማለት አይደለም፤ ይህም የሆነው መግቢያዎቹን ለክልላችን በሚያመች መንገድ አስተካክለን እንድንጠቀም ነው። አንድ የአቀራረብ ናሙና የተሟላ በሚሆንበት ጊዜም እንኳ አስፋፊዎች በመግቢያው ላይ ማስተካከያ ለማድረግ ወይም የራሳቸውን መግቢያ ለማዘጋጀት ሊመርጡ ይችላሉ። ከዚህ አንጻር፣ የምናነጋግረው ሰው በሩን ሲከፍት ድንገት ወደ አእምሯችን የመጣውን ሐሳብ ከመናገር ይልቅ መጀመሪያ የምንናገረውን ሐሳብ አስቀድመን መዘጋጀታችን የተሻለ ውጤት ያስገኝልናል።—ምሳሌ 15:28
በዚህ ወር እንዲህ ለማድረግ ሞክሩ፦
በቤተሰብ አምልኳችሁ ወቅት የተወሰነ ጊዜ መድባችሁ በመግቢያችሁ ላይ የምትናገሩትን የመጀመሪያ ሐሳብ ለመዘጋጀትና ለመለማመድ ጥረት አድርጉ።
አገልግሎት በምትወጡበት ጊዜ ለአገልግሎት ጓደኛችሁ ልትጠቀሙበት ስላሰባችሁት መግቢያ ንገሩት። (ምሳሌ 27:17) መግቢያችሁ ውጤታማ ካልሆነ ቀይሩት።