ሰኔ 1 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሰኔ 1 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 13 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 19 ከአን. 6-11 (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ሳሙኤል 16-18 (8 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ 2 ሳሙኤል 17:14-20 (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ቦዔዝ—ጭብጥ፦ በሥነ ምግባር ንጹሕ ሁኑ፤ መንፈሳዊ ኃላፊነቶችንም ተቀበሉ—w03 4/15 ገጽ 24-26 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ያሉህን ነገሮች በጥበብ መጠቀም የምትችለው እንዴት ነው?—nwt ገጽ 25 አን. 1-4 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
የወሩ ጭብጥ፦ ሁሉም ዓይነት ሰዎች የእውነትን ትክክለኛ እውቀት እንዲያገኙ እርዷቸው።—1 ጢሞ. 2:3, 4
10 ደቂቃ፦ በሰኔ ወር መጽሔቶችን አበርክቱ። በውይይት የሚቀርብ። በቅድሚያ በዚህ ገጽ ላይ የሚገኙትን ሁለት የአቀራረብ ናሙናዎች በመጠቀም መጽሔቶቹን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ከዚያም በአቀራረብ ናሙናዎቹ ውስጥ የሰፈረውን እያንዳንዱን ሐሳብ ተራ በተራ ተወያዩበት።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ ምን ውጤት አገኘን? በውይይት የሚቀርብ። አስፋፊዎች “በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ሌላ ቋንቋ ለሚናገር ሰው መመሥከር” በሚለው ርዕስ ላይ የቀረቡትን ነጥቦች ተግባራዊ በማድረጋቸው ምን ጥቅም እንዳገኙ ሐሳብ እንዲሰጡ ጠይቃቸው። እንዲሁም ያገኙትን የሚያበረታታ ተሞክሮ እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 25 እና ጸሎት