በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ሌላ ቋንቋ ለሚናገር ሰው መመሥከር
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ይሖዋ ‘በየትኛውም ብሔር’ ያሉ ሰዎች መንፈሳዊ ደህንነት ያሳስበዋል። (ሥራ 10:34, 35) ኢየሱስ ምሥራቹ “ለብሔራት ሁሉ” እንዲሁም “በመላው ምድር” እንደሚሰበክ መናገሩ ይህን ያሳያል። (ማቴ. 24:14) ዘካርያስ “ከብሔራት ቋንቋዎች ሁሉ የተውጣጡ” ሰዎች ለምሥራቹ ጥሩ ምላሽ እንደሚሰጡ ተንብዮአል። (ዘካ. 8:23) ሐዋርያው ዮሐንስ በተመለከተው ራእይ መሠረት ደግሞ ከታላቁ መከራ የሚተርፉት ሰዎች “ከሁሉም ብሔራት፣ ነገዶች፣ ሕዝቦችና ቋንቋዎች የተውጣጡ” ናቸው። (ራእይ 7:9, 13, 14) ከላይ የተጠቀሱት ሐሳቦች በግልጽ እንደሚያሳዩት በክልላችን ውስጥ ላሉ ሌላ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ምሥክርነት ለመስጠት ጥረት ማድረግ ይኖርብናል።
በዚህ ወር እንዲህ ለማድረግ ሞክሩ፦
በቤተሰብ አምልኳችሁ ወቅት ሌላ ቋንቋ ለሚናገር ሰው መመሥከር የምትችሉት እንዴት እንደሆነ ተለማመዱ።