በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—አዲሶችን ማሠልጠን
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? በቅርቡ ኢየሱስን መከተል የጀመሩ አዳዲስ ደቀ መዛሙርት እሱ ‘ያዘዘውን ሁሉ’ መጠበቅ ይኖርባቸዋል፤ ይህ ደግሞ ለሌሎች እውነትን ማስተማርን ይጨምራል። (ማቴ. 28:19, 20) በርካታ አዳዲስ ደቀ መዛሙርት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክፍል ማቅረብ እንዲሁም መደበኛ ባልሆነ መንገድ ለዘመዶቻቸውና ለጓደኞቻቸው መመሥከር ጀምረዋል። ይሁንና ለተማሩት ነገር ያላቸው አድናቆት እየጨመረ ሲመጣና ይሖዋ ሁሉም ሰው ምሥራቹን እንዲሰማ እንደሚፈልግ ሲያውቁ በመስክ አገልግሎት መካፈል እንደሚፈልጉ ይናገራሉ። (ሮም 10:13, 14) አዲሶች ያልተጠመቁ አስፋፊዎች ሆነው እንዲያገለግሉ ሲፈቀድላቸው ጥሩ ሥልጠና ማግኘታቸው መንፈሳዊ እድገት ለማድረግ የሚያስችላቸውን ይህን ኃላፊነት በሚወጡበት ጊዜ የመተማመን ስሜት እንዲኖራቸው ይረዳቸዋል።—ሉቃስ 6:40
በዚህ ወር እንዲህ ለማድረግ ሞክሩ፦
ከጥናታችሁ ጋር ከቤት ወደ ቤት አገልግሉ፤ ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርጉ ወይም ጥናት ስታስጠኑ ይዛችሁት ሂዱ። ጥናት ከሌላችሁ ደግሞ ብዙም ተሞክሮ ከሌላቸው አስፋፊዎች ጋር አብራችሁ አገልግሉ።