የአቀራረብ ናሙናዎች
መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 1
“ጦርነት በሚካሄድበት ወቅት፣ ሁለቱም ወገኖች አምላክ እንደሚረዳቸው ይሰማቸዋል። አምላክ ጦርነትን እንደሚደግፍ ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ መጽሔት አምላክ ጥንት ለሕዝቦቹ የተዋጋበትን ምክንያት እንዲሁም በቅርቡ ጦርነትን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዴት እንደሚያስወግድ ይገልጻል።” መዝሙር 46:9ን አንብብና መጽሔቱን ስጠው።
ንቁ! ኅዳር
“በምድር ዙሪያ የሚኖሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች፣ በሃይማኖት ውስጥ በሚያዩት ግብዝነት እና በዚያ በሚሰጠው አሳሳች ትምህርት ይረበሻሉ። የሃይማኖት የወደፊት ዕጣ ምን ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ መጽሔት በዘመናችን ሰዎች ከሐሰት ሃይማኖት ነፃ እንደሚወጡ ብቻ ሳይሆን ወደፊት ሃይማኖት ፈጽሞ እንደሚጠፋ የሚገልጸውን በራእይ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኘውን አስደናቂ ትንቢት ያብራራል።”